>

ክርስቲያን የኦሮሞ ባለሥልጣናትን መረሸኑ ከወለጋ ተነስቶ ምዕራብ ሸዋ ደርሷል!!!  (ዘመድኩን በቀለ )

ክርስቲያን የኦሮሞ ባለሥልጣናትን መረሸኑ  ከወለጋ ተነስቶ ምዕራብ ሸዋ ደርሷል!!! 
        ዘመድኩን በቀለ 
* ሁኔታውን በአንክሮ ላየው ኦነጎች ከምርጫው በፊት ኦህዴድን እያጸዱ ይመስላል!
 
* ቀይ ሽብር ተመልሳ መጣች እንዴ? ገዳዮቹ ሥም ዝርዝር ይዘው የሚዞሩ ነው የሚመስሉት። ገዳዮቹ ደግሞ አይያዙም። ፖሊስም ለፈልጋቸውም የሚደክም አይመስልም። የግድያ ዜናውም ወደ ውጭ እንዲወጣ አይፈለግም። 
•••
አሁን ደግሞ ተረኛው ተረሻኝ የጀልዱ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የነበሩት ኦቦ ረጋኔ ከበበ እና የጎጆ ከተማ የፖለቲካ ዘረፍ ኃላፊ የነበሩት ኦቦ ተስፋዬ ገረመው በጎጆ ከተማ ማክሰኞ ምሽት 12 ሰዓት አካባቢ በጥይት እሩምታ ተደብድበው ተገድለዋል።
•••
በ OMN የማይዘገብ፣ በጋዲሳ ሮባ የማይተነተን፣ እነ ፀጋዬ አራርሳ፣ እነ ሕዝቅኤል ጋቢሳ ትንፍሽ የማይሉትን ዜና ነው ይሄ። የኦህዴድ ባለሥልጣናትን ርሸና ምዕራብ ሸዋ ደርሷል ማለት ነው። ወደ ሸገር አዲስ አበባም እየቀረበ ነው። ኦነጎች ከምርጫው በፊት ኦህዴድን እያጸዱ ይመስላል። የሚረሸኑት የኦህዴድ ባለሥልጣናት በሙሉ ደግሞ ክርስቲያኖች ናቸው ተብሏል።
•••
ለማስታወስ ያህል ባለፈው ወር የኢትዮ ቴሌኮም የምዕራብ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገመቺስ ታደሰን በነቀምት ከተማ በመኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ ላይ በታጠቁ ኃይሎች መረሸናቸው፣
•••
ባለፈው ሳምንት ደግሞ የኦሮሚያ መንገዶች ባለሥልጣን አማካሪ የሆኑት አቶ ቶሎ ገዳ (Tolaa Gadaa) ለመስክ ሥራ በወጡበት በኦነግ ሸኔ ኃይሎች ተረሽነው መሞታቸው፣
•••
በዚሁ ሳምንት ደግሞ የነቀምቴ ከተማ የወንጀል ምርመራ ፖሊስ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ጫላ ደጋጋ “ያልታወቁ ኃይሎች” የሚል የዳቦ ስም በተሰጠው ፍረጃ በዚያው በወለጋዋ ነቀምት በአደባባይ ተረሽነዋል።
•••
የዛሬ ዓመትም ደግሞ የውጭ ሀገር ዜጎችንና የራሱ የጃዋር ጓደኛ የሆነ የማዕድን ባለሙያ በዚሁ በኦነግ ጦር ተረሽነው፣ አስከሬናቸው ከነመኪናቸው በእሳት መጋየቱ ይታወሳል።
•••
እደግመዋለሁ የኦሮሞ እስላሞች ኔትወርክ ወይም በእንግሊዝኛ አጠራሩ (OMN) ም ሆኑ ለኦሮሞ ባዳ ኔትወርክ ( OBN ) ይህን መሰሉን ዜና አይዘግብቱም። አልዘገቡትምም። ዐቢይ አህመድ ወደ ወለጋ አልሄድም እዚያ ሄጄ ብገደል የኦሮሞ አንድነት ይፈርሳል ያለው ከመሬት ተነስቶ እንዳልሆነ እሙን ነው።
•••
ኦነግ ማለት ጠላቴ የሚለውን ዐማራውን ከሚገድለው በላይ የገዛ ወገኖቹ የሆኑትን ኦሮሞዎችን የሚገድለው ይበልጣል። እንዲያውም አሁን አሁን በብዛት እያረደና እየገደለ የሚገኘው ኦሮሞውን ነው። ያውም የኦሮሞ ጴንጤና ኦርቶዶክስ የሆነውን ኦሮሞ። እሱን እየገደለ ነው። እየረሸነ ነው። ወዳጄ ኦነግ ነፍሰ በላ ቡድን ነው። ኢሊሊ ሆቴል ተቀምጦም እየረፈረፋቸው ነው። ነገርየው ርሸናው የሚቀጥል ይመስላል።
•••
አሁንም ዛሬም እደግመዋለሁ። ይሄ ግድያ ግን እንኳንም ዐማራ ክልል ያልሆነ። እንኳንም በትንታም ቢሆን በዐማራ ክልል አልሞቱ። ይሄኔ የጌታ ምፅአት የደረሰ ይመስል እነ ኢቲቪ፣ እነ ራድዮ ፋና፣ እነ ዋልታ፣ እነ ኤልቲቪ ወዘተ ሀገሪቷን በአንድ እግሯ ባቆሟት ነበር። የመንግሥት ግልበጣም ነው ተብለው በባሌ ገጠር ውስጥ የሚኖር ምስኪን ገበሬ ዘብጥያ በወረደ ነበር። የዐማራ አንቂዎች ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ሁሉ በባትሪ ተፈልገው፣ በወረንጦ እየተለቀሙ በሽብር አንቀጽ በተከሰሱ ነበር። ምድረ አቃጣሪ ሁላም ተደርቦ አፉን በከፈተ ነበር።
•••
በራሱ በኦሮሞ የተረሸኑትን የኦሮሞ ልጆች ነፍሳቸውን ይማር። ለቤተሰባቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን።
•••
ሻሎም !    ሰላም !  
ህዳር 18/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic