>

ታሪክ እራሱን ሲደግም፤ KIL እና KIS፤ ኢሳት እና ኢትዮ360!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ታሪክ እራሱን ሲደግም፤ KIL እና KIS፤ ኢሳት እና ኢትዮ360!!!
ያሬድ ሀይለማርያም
የኢትዮጵያን አንድነት የሚያቀነቅነው ኃይል ሁሌም አገሪቷ ክፉ ቀን ሲገጥማት እና ጭንቅ ቀን ሲመጣ ጎራ ለይቶ መፋለም እና እርስ በርሱ ማዶና ማዶ ቆሞ መወነጃጀል ይጀምራል። ይህ የተለመደ መገለጫው ሆኗል። ለምን ይሆን?
የቅንጅት አመራሮችን መታሰር ተከትሎ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ KIL እና KIS በሚል ጎራ እራሱን ፈርጆ ሲወነጃጀል፣ ሲነቃቀፍ፣ ሲፈራረጅ፣ አንዳንድ ቦታም ሲቧቀስ በምርጫው ሰሞን ተሰባስቦ የነበረው ለአገር ተቆርቋሪ ኃይል ከፈፈለም በታተነም። የዛ ጠባሳ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ግንኙነት ላይ ቀላል የማይባል ጠባሳ አሳረፈ። የአደባባዩን ጭቅጭቅ የጠለ ጨዋዎች እራሳቸውን በብዙ ማይልስ ከፖለቲካው አራቁ፤ የቀረውም ማዶና ማዶ ቅራቀኝ ተሰልፎ ሲሰዳደብ እና እርስ በርሱ ሲናጭ ለወያኔ ሌላ የሃያ አመት እድሜ ጨመረላት።
ዛሬም ያው አብሾ ተነስቶብን ነው መሰል የKIL እና የKIS ገመድ ጉተታ እና ግጭት በኢሳት እና በኢትዮ360 በኩል እየተደገመ ነው። ከእዚህ እርግማን ይሁን ሸር የጠለፈው የፖለቲካ ስንክሳር መች ይሆን የምንላቀቀው? መች ይሆን ኢትዮጵያ በምትፈልገን ወሳኝ ጊዜ እጃ አንድ ላይ ቆመን በጋራ ለጥሪዋ ምላሽ የምንሰጠው?
ልክ እኮ አንድ ሰው እሳት እየተቃጠለ እያየነው አንዳችን እሳቱ በውሃ ነው መጥፋት ያለበት፤ ሌላችን ደግሞ አይ ውሃ መጠቀም የለብንም ሌላ ዘዴ እንጠቀም በሚል ሙግት ገጥመን እሳት አጥፊዎቹ እርስ በርስ ስንቧቀስ ሰውየው አመድ ይሆናል። በአገር ጉዳይም የቁርጥ ቀን ሲመጣ የምናሳየው ባህሪ ከዚህ ጋር ይመሳሰልብኛል። ምን ሆነን ነው?
በተቃራኒው ብሔርት ተኮር ኃይሎችን ያያችው እንደሆነ በደናው ጊዜ ተበታትነው ይቆዩና በእኔ ብሔር ላይ አደጋ ተፈጥሯል ብለው ሲያስቡ ቶለ ብለው ወደ አንድ ክብ ይሰባሰባሉ። የአንድነት ኃይሉ ደግሞ በአደጋ ግዜ ሰላሳ ክቦች ይፈጥርና በየጎራው ተወሽቆና በቧድኖ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል።
ያኔ ለአቅመ ፖለቲካ ያልደረሳችው እና KIL እና KIS ምንድናቸው ለምትሉ ይችን ማስፈንጠሪያ ተከትላችሁ የተፈጠረውን አንብቡ። የተሟላ መረጃ ባይሆንም ግንዛቤ ይሰጣችኋል። http://www.sudantribune.com/spip.php?article18494
Filed in: Amharic