>
5:14 pm - Saturday April 20, 7365

ኢትዮጵያ የቆሸሸችው መቼ ነው?  (አቻምየለህ ታምሩ)

ኢትዮጵያ የቆሸሸችው መቼ ነው? 
አቻምየለህ ታምሩ
በዐቢይ አሕመድ ይሁንታ በሚያሰማራው የጥላቻ ሠራዊት ከአንድ መቶ በላይ ንጹሐን ኢትዮጵያውያን በነገድና በሃይማኖታቸው እየተለዩ እንዲፈጁ ያደረገው ጃዋር መሐመድ እንዳስፈለፈላቸው ጫጩቶች ለሚቆጥራቸው ተከታዮቹ  ፊት ባሳላፍነው ቅዳሜ በዋሽንግተን ዲሲ ባደረገው ንግግር «[እነሱ] ለ150 ዓመታት በአለም አቀፍ ደረጃ ታሪኳን ያቆሸሽቱን ኢትዮጵያን እኛ በገዳ ስርዓት በዲሞክራሲ እናጥባታለን» ሲል ደስኩሯል። ራሱን እንዳለማቀፍ ፖለቲከኛና ምሑር አድርጎ የሚቆጥረው ጃዋር መሐመድ  ይህንን ዲስኩሩን  የተናገርሁትን ሁሉ ያምኑኛል ብሎ በሚንቃቸው ተከታዮቹ ፊት እንጂ ማሰብ በጀመሩ ሰዎች መድረክ ቀርቦ ሊናገረው  ከቶ አይደፍርም።
ለመሆኑ ኢትዮጵያ የቆሸሸችው መቼ ነው? የግራኝና የኦሮሞ ገዢ መደብ  የጥፋት  ወረራ ከመካሄዱ በፊት ስለነበረችው ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ስልጣኔና ታላቅነት ኦነጋውያን ደብተራ የሚሏቸው የኢትዮጵያ ጸሐፍት ብቻ ሳይሆን እልቆቢስ የአውሮፓ፣ የአረብና የምስራቁ ዓለም ተመራማሪዎች በዘመናቸው በአለም ፊት መስክረዋል። በምንኖርበት ዘመንም   የአውሮፓ፣ የአረብና የምስራቁ ዓለም  ጸሐፍትና ተመራማሪዎች የግራኝና የኦሮሞ ገዢ መደብ የድምሰሳ ወረራዎች  ከመካሄዱ በፊት ስለነበረችው ጥንታዊት ኢትዮጵያ ብልጽግና፣ የስነ ጽሑፍ፣ የኪነ ጥበብና የባህል ሥልጣኔ ተመራምረውና   ጽፈው አልጠገቡም።
በምንኖርበት ዘመን የግራኝና የኦሮሞ የጥፋት ወረራ ከመካሄዱት በፊት ስለነበረችዋ የአባቶቻችን ኢትዮጵያ ባደረገው ጥናት በአለም የታሪክ ተመራማሪዎች  የተደነቀው  እንግሊዛዊው  ፕሮፌሰር ማቲው ሳልቫዶሬ ነው።  ፕሮፌሰር ማቲው ሳልቫዶሬ እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም.   ባሳተመው በአይነቱ ልዩ የሆነና የአውሮፓና የአፍሪካን ታሪካዊ ግንኙነት በሚመለከት  ለዘመናት የቆየውን አመለካከት ከመሰረቱ በለወጠውና  “The African Prester John and the Birth of Ethiopian-European Relations, 1402-1555” በሚል ባሳተመው መጽሐፉ እንደጻፈው በአውሮፓ ሥልጣኔ ውስጥ ዛሬ ለደረሱበት እድገት መነሻ  የሆነው የሕዳሴ ዘመን የተጀመረው «የካህኑ ንጉሥ ዮሐንስ አገር»  የሚሏትን ታላቋን ኢትዮጵያ ለማወቅ፣  ከጥንካሬዋ ለመማር፣ የመወዳጀት፣ ሥልጣኔዋን ወደ አውሮፓ ለማስገባት ሲሉ ወደሷ በመጡ ጊዜ  መሆኑን በዋናነት የአውሮፓውያንን በተለይም የጣሊያንና የፖርቱጋል  መዘክሮችን በርብሮ  ያገኛቸውን የዘመኑን  ድንቅ ዶሴዎች በማጠልፈፍ ባቀረበው ጥልቅ  ምርምር አረጋግጧል።
ፕሮፌሰር ማቲው  ሳልቫዶር  በዚህ  በአይነቱ ልዩ በሆነው ጥናቱ  በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ በጣም የተማሩ እና የተከበሩ አፍሪካውያን ኢትዮጵያውያን ብቻ እንደነበሩ፣  ይህም አውሮፓውያን ኢትዮጵያን ለማግኘት እንዲተጉና በዘመኑ  ወደአፍሪካ ያደረጓቸው ጉዞዎች የዚህን ኃያል ምሁራንና የካህኑ  ንጉሥ ዮሐንስን  አገር ለማግኘትና መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማጥናት  እንደነበር አስረድቷል።
ባጭሩ የፕሮፌሰር ማቲው ሳልቫዶር ምርምር  ከግራኝና የኦሮሞ ገዢ መደብ  የድምሰሳ ወረራ ከመካሄዱ  በፊት የነበረችዋ ጥንታዊቷ ባሊን፣ ዳሞትን፣ እናርያን፣ ወጂን፣ ፈጠጋርን፣ ዘይላን፣ ጋሞን፣ ወላይታን፣ ሲዳሞን፣ ሐረርን፣ ሐድያን፣ ከምባታን፣ ጎጃምን፣ በጌምድርን፣ ስሜንን፥ ሸዋን፣ ትግሬን፣ ባሕር ምድርን፣ አዳልን፣ ሸዋን፣ ወዘተ ያቀፈችዋ ኢትዮጵያ እንዴት አድርጋ  አውሮፓን shaped እንዳደረገች በሚያስደንቁ ማስረጃዎች አስደግሞ ይነግረናል።
ይቺ አውሮፓውያን የተደነቁባትና የሕዳሴ ዘመን የጀመሩባት ኢትዮጵያ የፈረሰችው በግራኝና የኦሮሞ ገዢ መደብ አጥፊ ወረራዎች አማካኝነት ነው። ከዐፄ ገላውዲዮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የነበሩት የኢትዮጵያ ነገሥታት ሲደክሙ የኖሩት አውሮፓውያንን shaped ያደረገችዋን፣ በግራኝና የኦሮሞ ገዢ መደብ  ባካሄዱትት አጥፊ ወረራዎች  የተለያዩትን  ጥንታዊ  የኢትዮጵያ አውራጃዎች  መልሶ አንድ በማድረግ ወደቀድሞው ገናናነቷ ለመመለስ ነው።
ይህቺ ያባቶቻችን  የመካከለኛው ዘመን ኢትዮጵያ በንጹሐን አስከሬን የቆሸሸቸው ከባሌ በታች የተነሳው የኦሮሞ የገዢ መደብ በገዳ ወታደራዊ ሥርዓት እየተመራ ነባር ኢትዮጵያውያን በመግደል፣ በመስለብና ከርስታቸው በማፍለው የሴቶች፣ የሕጻናትና የአቅመ ደካሞች የሬሳ ክብር ሲያደርጋት ነው።
በ1514 ዓ.ም. ወረራ ከጀመረው ከመጀመሪያው ሉባ መልባ እስከ አምስተኛው ሉባ ምችሌ ድረስ ከባሌ በታት ተነስቶ ነበሮቹን የኢትዮጵያ ነገዶች ድምጥማጣቸውን እያጠፋ፣ ማንነታቸውን እየቀየረ፣ ቋንቋቸውን እየደመሰሰ፣ በመሬታቸው ላይ ጭሰኛ እያደረገ፣ የነበራቸውን ቁሳዊና መንፈሳዊ ሥልጣኔ እያወደመ፣ የኢትዮጵያን ምድር የሰው ልጅ ግዳይ ክምርና የደም ጎርፍ የሚፈስበት ገሀነም በማድረግ እንደ ዋርካ  የተንሰራፋው የኦሮሞ ገዢ መደብ የዘር ማጥፋት ሥርዓት ናፋቂዎች ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ  እንድንረሳው ያደረጉንን የአራት መቶ ዓመታት ግፍና መከራ እያስታወሱ በነሱ ተብሶ  የመንፈስ አባቶቻቸው ያቆሸሹትን አገር አያቶቻች በአባቶቻቸው ባድማ ላይ የተራገፈውን ቆሻሻ  ሳይጠርጉ  በወረራ በያዙት የሰው አገር ላይ ባለርስት ስላደረጓቸው ሰብዓዊ የነበሩትን አባቶቻችን  በማቆሸሽ «ያቆሸሽቱን  በገዳ ስርዓት በዲሞክራሲ እናጥበዋለን»  እያሉ  ሊቀናጡብን  ይቃጣቸዋል።
ለመሆኑ ገዳና ዲሞክራሲ ምን አገናኝቷቸው ነው ቆሸሸ የተባለውን «በገዳ ሥርዓት  በዲሞክራሲ እናጥበዋለን» የሚሉን?   የገዳን ሥርዓት ዲሞክራሲ ስርዓት ነው ወይ?  እስቲ እንመርምረው! የዴሞክራሲ መርኅ ናቸው ከሚባሉት መካከል ዋናው «የብዙሐን አገዛዝ እና የጥቂቶች መብት» ወይም በእንግሊዝኛ «Majority Rule and minority Right» የሚለው ጽንሰ ሀሳብ ነው። በዚህ የዲሞክራሲ መርኅ የገዳ ሥርዓትን ስንመዝነው ገዳ የዲሞክራሲ ፍጹም ተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን። ላስረዳ!
በኦሮሞ ስነ ቃል ውስጥ Salgan Borana, sagaltamman Garba [Nine are the Borana [pure Oromo] and ninety the Garba [the assimilated] የሚል ታዋቂ ትውፊት አለ። ምንጭ፡ 1ኛ. G.W.B Huntingford (1955). The Galla of Ethiopia. London: International African Institute፥ ገጽ 46; 2ኛ. Cerulli, E. (1933). Etiopia Occidentale (Dallo Scioa alla frontiera del Sudan): note del viaggio 1927-1928. Sindacato Italiano Arti Grafiche. Vol. I ገጽ 33]።
ይህ ትውፊት ኦሮምኛ ከሚናገረው ውስጥ «ገርባዎች ዘጠና፤ ቦረናዎች ግን ዘጠኝ ናቸው» ማለት ነው። ይህ ትውፊት ኦሮምኛ የሚናገረው ማኅበረሰብ ቦረናዎች [እውነተኛ ኦሮሞ] እና ገርባዎች [ተገዶ ማንነቱን የቀየረ] ተብሎ በሁለት እንደሚከፈል የሚገልጽ ነው። ከአስር ኦሮምኛ ተናጋሪዎች መካከል «ዘጠኙ ገርባ [ኦሮሞ ያልሆነ] አንዱ ኦሮሞ» ነው ከሚለው የኦሮሞ ትውፊት ውስጥ ኦሮሞ የሆነው በቁጥር እጅግ ጥቂት እንደሆነና ገርባው ደግሞ በቁጥር እጅግ አብዝሐ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
የገዳ ሥርዓት መርኅ ናቸው ከሚባሉት መካከል ዋናው ማንነቱን እንዲቀይር የተደረገው ወይም ገርባው እንኳን መሪ ሆኖ ሊመረጥ የገዳ ስርዓት በሚካሄድበት አካባቢ ድርሽ እንዳይል ማድረግ ነው። በገዳ ሥርዓት መሰረት መሪ ወይም አባዱላ የሚሆነው ሰው የሚሰየመው እውነተኛ ኦሮሞ ወይም ቦረና ከሆኑት ብቻ የበለጠ የገደለውና ብዙ የወረረው ነው። በቁጥር አናሳ ከሆኑት እውነተኛ ኦሮሞዎች ወይም ቦረናዎች መካከል የበለጠ የገደለና ብዙ ገርባ ያስገበረ ጦረኛ አባ ዱላ ሆኖ ይሰየማል። ይህ የገዳ ስርዓት መርኅ ነው።
በርካምበር እንዳጠናው አርሲ ውስጥ ሁለት ሶስተኛው ሕዝብ የሐድያ ነገድ አባል የሆነና ኦሮምኛ የተጫነበት ነው። ሆኖም ግን አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውት የነበሩት ጥቂቶቹ የቦረና ኦሮሞዎች ናቸው። በርካምበር እንደሚለው « አርሲ ውስጥ የኦሮሞ ጎሳ ከሆነው ከቦረና በስተቀር ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚቆጠሩት የሐድያ ጎሳዎች እንዲያስተዳድሩ አይፈቀድላቸውም፤ መሶሻል ስታተስም የሀድያ ጎሳ የሆኑ አርሲዎች ከኦሮሞ ጎሳ ያነሰ ቦታ ይሰጣቸው ነበር» ምንጭ፡Braukämper, U. (1980). Geschichte der Hadiya Sud-Athiopiens. A. Schröder፡ ገጽ 431።
የበርካምበት ጥናት የሚያሳየው የገዳ ሥርዓት አብዝሐነት የሆኑትን ገርባዎችን ለመግዛት በቁጥር አናሳ ከሆኑት ቦረናዎች መካከል በብዛት የገደለውና የወረረው አባ ዱላ ሆኖ በመሪነት የሚሰየምበት ሥርዓት እንደሆነ ነው። ዲሞክራሲ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ዲሞክራሲ ብዝሐ ቁጥር ያላቸው ተገዥዎች ሙሉ በሙሉ ተገልለው ጥቂት ቁጥር ያላቸው ገዢዎች ብቻ እየተፈረራረቁ ተገዢዎችን ገርባና ባሪያ የሚያደርጉበት ስርዓት አይደለም። ገዳ የአንድ ኅብረተሰብ ግማሽ አካል የሆኑትን ሴቶችን ሙሉ በሙሉ እንደሚያገልል ስናስብ ደግሞ ስርዓቱ «የብዙሐን አገዛዝ እና የጥቂቶች መብት» የሚለውን ዋናውን የዲሞክራሲ መርኅ ጥርሱን እንዳረገፈው ማሰብ አይከብድም።
ባጭሩ ዲሞክራሲ «የብዙሐን አገዛዝ እና የጥቂቶች መብት»የሚከበርበት ስርዓት ነው። ገዳ ግን አብዝሐ ቁጥር ያላቸውን ገርባዎችን በገዳ ስርዓት ሙሉ በሙሉ እንዳይሳተፉ አግዶ በቁጥር አናዛ ከሆኑት እውነተኛ ኦሮሞዎች መካከል አብዝሐውን ለመግዛት በአባ ዱላነት የሚሰየሙበት ሥርዓት ነው።
ለዚህም ነው ጥቂቶቹ እውነተኛ ኦሮሞዎች አብዝሐ ቁጥር ያላቸውን ገርባዎች እንዲገዙ ተደርጎ የተዋቀረው የገዳ ስርዓት በኦነጋውያንና ደቂቆቻቸው እንደሚደሰኮረው እንኳን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ እንኳን መንግሥታዊ ሥርዓት ፖለቲካዊ ሥርዓትም አልነበረም የወረራ ሥርዓት እንጂ። ባጭሩ የገዳ ሥርዓት ምንም አይነት ዲሞክራሲያዊነት የሌለበት ፍጹም የሆነ ወታደራዊ ሥርዓት ነው።
የገዳ ሥርዓት የዲሞክራሲ ስርዓት ነው የሚል ቢኖር Salgan Borana, sagaltamman Garba የሚለውን የኦሮሞ ትውፊት መሰረት አድርጎ የገዳ ስርዓት የዴሞክራሲ መርኅ ናቸው ከሚባሉት መካከል ዋና የሆነውን «የብዙሐን አገዛዝ እና የጥቂቶች መብት» [Democracy is based on both majority rule and minority rights] እንደሚያሟላ ያስረዳ!
እንግዲህ! ጃዋር  ቆሸሸ ያለውን አጥቦ ዲሞክራሲያዊ እንደሚያደርግ እየነገረን ያለው ዲሞክራሲ ምን አይነት ሥርዓት መሆን እንደሌለበት በማስተማሪያነት ብቻ ሊቀርብ በሚገባውና  በንጹሐን ደም ሲቆሸሽ በኖረው  ገዳ በሚባለው  የኦሮሞ ገዢ መደብ የወረራ ሥርዓት ነው። ለነገሩ ለሕጻን እንኳ የማይወራ የጅል ፈጠራ እየፈጠረ  የሚነግረውን ሁሉ እንደወረደ የሚቀበልና ሌላው መሳቂያ መሳለቂያ ቢያደርገውም ኦሮሞ  ግን የፈለገኝን ብነግረው ያምነኛል  የሚል እምነት  ኦሮሞን  ጅል አድርጎ የማሰብ ንቀት ስላለበትና ሳይመረምር የሚያስተጋባ ተቀባይ ስላለው ለምን ይጨነቃል!
Filed in: Amharic