>

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያለው ግድያ ባለ ሁለት ስለት ሰይፍ ሆኗል!!! (ቅዱስ ማህሉ)

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያለው ግድያ ባለ ሁለት ስለት ሰይፍ ሆኗል!!!
ቅዱስ ማህሉ
 
* ብሄር እና ሃይማኖት ቢሆንም የሚያጠቃው ግን ሃይማኖትን ለይቶ ነው!!!
 
ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ጉራጌም፣ ትግሬም፣ ወላይታም፣ጋሞም ሆነ ኦሮሞ በአካባቢው አማራ በሚል የጅምላ ስያሜ  ለቆንጨራ ይዳረጋል!!!
 
 ብሄር እና ሃይማኖት የሚለው ሁለት ስለት አሁን ጭፍጨፋ በሚደረግባቸው በባሌ፣አርሲ እና ሃረርጌ  አካባቢዎች  ትርጉም ብዙዎቻችን እንደሚመስለን አማራ የሚባለው አማራነት ሳይሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ ክርስቲያን ማለት ነው። ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ጉራጌም፣ ትግሬም፣ ወላይታም፣ጋሞም ሆነ ኦሮሞ በአካባቢው አማራ ይባላል። አማራ ያልሆነውን ለምሳሌ አብሬ ኖሬ ባየኋቸው አንዳንድ የሀረርጌ እና የአርሲ አካባቢዎች ኦሮሞ ክርስቲያኖች ክርስቲያን ያልሆኑትን ጋላ እያሉ ነው የሚጠሯቸው። ይህ ማለት በብሄር እና በሃይማኖት ያተኮረው ጥቃት ሁለት መምቻ ምክንያት እንጅ አጠቃላይ ጭፍጨፋው ሃይማኖታዊ ነው። ምክንያቱም ከነዛ አካባቢ ውጭ ላለ ሰው አማራ ማለት ትርጉሙ እስላም እና ክርስቲያንን ጨምሮ ይመስለዋል። ግን እደዚያ አይደለም። አሁን በቴክርስቲያን በሚቃጠልባቸው አካባቢዎች አማራ ማለት ትርጉሙ ክርስቲያን ማለት ነው። ባንድ ወቅት ሂርና ውስጥ ያጋጠመኝን ከወራት በፊት ጽፌላችሁ ነበር። በነዚያ አካባቢዎች አማራ እና ጋላ ማለት ክርስቲያን እና እስላም ማለት ነው። በነዚያ አካባቢዎች አማራ ገደልን ካሉ ሌላ ቦታ እንደሚታሰበው ጎንደሬ እስላም አማራ ወይም ጎጃሜ አማራ ገደልን እያሉ አይደለም። ክርስቲያን ከሆነ ኦሮሞ ይሁን ወላይታ ወይም ትግሬ ይሁን ጉራጌ ለነሱ አማራ ነው። የገደሉት ክርስቲያን ነው። ትርጉሙ ይሄው ነው።
Filed in: Amharic