>

ኢትዮጵያውያን በቬጋስ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ በአገር ቤት የተፈጸመውን ጥቃት እና ግድያ አወገዙ ! (ህብር ራድዮ)

ኢትዮጵያውያን በቬጋስ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ በአገር ቤት የተፈጸመውን ጥቃት እና ግድያ አወገዙ !
ህብር ራድዮ
* ጃዋር መሐመድን ጨምሮ ከጀርባው ያሉ ባለስልጣናት ለሕግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል
* ጃዋር ተደብቆ በጓሮ ገብቶ በጓሮ ወጣ
በቬጋስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገር ቤት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሀይማኖት እና ብሄር ላይ አነጣጥሮ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ ሕይወታቸውን በግፍ ላጡ ወገኖች ድምጽ ለመሆን በከፍተኛ ቁጥር አደባባይ ወጥተው ጃዋር መሐመድ የሚመራውን ስብሰባ በመቃወም እሱና ተከታዮቹ ጥቃት ለፈጸሙባቸው ንጹሃን ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።ለሰዓታት በዝናብ ላይ ቆመው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
     ጃዋር መሐመድ የኢትዮጵያውያኑን ጠንካራ ተቃውሞ ፈርቶ በመሰብሰቢያ አዳራሹ ጀርባ ተደብቆ ገብቶ ተደብቆ የወጣ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ በከፍተኛ ድምጽ ጃዋር የሙስሊሙንም ህብረተሰብ  ሆነ የኦሮሞን ሕዝብ የማይወክል፣ገንዘብ ሰብስቦ ለሽብር የሚያውል ነጋዴ በመሆኑ አሜሪካ ከዚህ መሰሉ አሸባሪ ከለላ አትስጪ አትርጂ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
      በኢትዮጵያ ለተፈጸመው ጥቃት ጃዋር ብቻ ሳይሆን ከጠቅላይ ሚ/,ር አብይ ጋር ያሉ ባለስልጣናት ጭምር ስላሉበት ጉዳዩ እንዲመረመር አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ በስፍራው ከተገኙት የሀይማኖት አባቶች አንዱ አባ ዳንኤል ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግፈኞችን መጨረሻ ስልት ስለሞቱት ንጹሃን ሲሉ ፍትህን እንዲያሰፍኑ ይህ ካልሆነ ግን ነገ ከነገ ወዲያ ይህ ጥቃት በሳቸውን ቤተሰብ ሊመጣ ይችላል ሲሉ ገልጸዋል።
     ዘማሪ ቀሲስ ወንደሰን በበኩላቸው በኢትዮጵያውያን መካከል ሃይማኖትን መሰረት አድርጎ ቤተ ክርስቲያን ማቀጠል፣ክርስቲያኖችን መግደል፣ለሴቶች እና ህጻናት የማይራራ አመለካከት ያላቸውን ጃዋራው ያን እግዚአብሔር ያስታግስልን ሲሉ ገልጸዋል።
     የኢትዮጵያ መንግሥት ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጥቃት የፈጸሙ ሁሉ በቁጥጥር ስር እንዲውል ለህግ እንዲቀርቡ ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ አቶ አዱኛ ባነበቡት የሰልፈኞቹ አቁዋም ገልጸዋል።
    ለሰዓታት ብርድ እና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ጠንካራ ተቃውሞ ያቀረቡት ኢትዮጵያውያን በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ እና ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲያደርጉ ጥበቃ አድርገዋል።
    በከተማው ከሚገኙ ታላላቅ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሁለቱ በስፍራው ተገኝተው የኢትዮጵያውያኑን ጠንካራ ተቃውሞ ሽፋን ሰጥተዋል። “ተቃውሞው ለአንድ ግለሰብ አይደለም አብሮት የተሰለፈው ሀይል አሸባሪ ነው።” በማለት ቅሬታቸውን ያቀረቡት ሰልፈኞች ጃዋርን ከሽብርተኛ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ጋር በማገናኘት ጸረ ክርስቲያን እና ቤተ ክርስቲያን አቋሙን እንዲያቆን፣ህጻናት እና ሴቶችን ሳይቀር መግደል እንዲያበቃ ጠይቀዋል።
 
Filed in: Amharic