>

ጀዋር ሙሃመድ በላስቬጋስ ከተናገረው መሀከል የሚከተለውን በጥሞና መርምሩ!!! (ታዬ ቦጋለ)

ጀዋር ሙሃመድ በላስቬጋስ ከተናገረው መሀከል የሚከተለውን በጥሞና መርምሩ!!!
ታዬ ቦጋለ
1. “… ወያኔን የታገልነው ጨቋኝ ስለነበረ ነው። እኛ  ከትግራይ ህዝብ ጋር አብረን እየኖርን ነው። ለወደፊትም እንኖራለን።” የሚለውን እንፈትሽ
*
አስተውሉ፦ ወያኔ ጨቋኝ ከነበረ አሁን የሚሞዳሞደው ምን ተገኝቶ ነው?!  ይህ ጠወልዋሌ እንዴት ድራማ እንደሚሠራና ጧት የተናገረውን ከሰአት እንደማይደግም!!!
2. “ኦሮሞ ገዳይ ነው በሚል አለምን ለማሳሳት የሚሞክሩ…”
ከሚለው አነጋገሩ ውስጥ እውነታውን ስንመዝን ሰልፈኞቹ ያንፀባረቁት መልዕክት፦
‘ጃዋር ገዳይ ነው። Jawar is ISIS, Jawar is terrorist… የሚል እንጂ ‘ኦሮሞ ገዳይ ነው’ የሚል አይደለም። ዓላማው ኦሮሞን ከሌላው ወገን ጋር የማባላት አጀንዳ ነው። ጃዋር አንድ ወይም ጥቂት ግለሰቦች ቀጥሮ ኦሮሞን በማሰደብ ጭምር ለግጭት ሊጠቀምበት ይችላል። ማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን ህዝብን አይወክልም። ጃዋር ዒላማ የሚያደርጋቸው በገዛ ሀገራቸው ቀና ብለው እንኳ መራመድ የተሳናቸውን ምስኪኖች ነው።
3. “… ጉዳዩን ወደ ሀይማኖት ለመጎተት ይፈልጋሉ። ሀሰተኞች ናቸው ሀይማኖታቸውን እራሱ አያከብሩትም። ሃይማኖቱን የሚያከብር በሃይማኖት አይዋሽም። ለመስጂድ ክብር ያለው፣ ለቤተክርስቲያን ክብር ያለው በነዚህ አይዋሽም። ያልተቃጠለውን ተቃጥሏል ብሎ አይዋሽም። በሌላ አገር የተደረገውን በአገራችን እንደሆነ አስመስሎ አያቀርብም!” ብሏል።
*
እዚህ ላይ ልብ ብለን የምንመለከተው ጉዳይ ጃዋር ከሠላሳ በላይ የተቃጠሉ ቤተክርስቲያኖችን ሽምጥጥ አድርጎ በአደባባይ መካዱን፤ እያወቀ ለማንሳት አለመድፈሩ ድብቅ አጀንዳውን ማሳየቱ እና በሌላ ሀገር የተቃጠሉ ቤተክርስቲያኖችን ምስል ለማሳሳት የለቀቁት የጃዋር ሰዎች = አስቀድሞ ለታቀደው ዓላማ፤ ሊሆኑ መቻላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የምስሉ ስህተት እኛም ብንሆን ልክ አይደለም ብለን የገሰፅነው ቀለል ያለ ስህተት ሆኖ፤ የውሸት ምስል የተቃጠሉ ሦስት ደርዘን አብያተ ክርስቲያናትን እውነት አይሸፍነውም። ከዋናው ጉዳይ ውሸት እየለቀቁ ማዘናጋት የፌስቡክ የጅል ‘ሙድ’ ሆኗል።
4. ይቀጥልና፦  “ኦሮሞ በሃይማኖት የማይለያይ አንድ ሆኖ እስቸገራቸው። ለዚህ ነው በሃይማኖት ለመከፋፈል የሚጥሩት።” እያለ ያፌዛል።
ለመሆኑ የተቃጠሉት ቤተክርስቲያኖች የሁሉም ኦርቶዶክሶች የጋራ ማምለኪያ አይደሉምን?! ከፊሉ ኦሮሞስ ኦርቶዶክስ አይደለምን?!
“ስትራቴጂስቱ የቀዩ የነጩና የጥቁሩ በሬ” አካሄድህን፤ ያልበሰለ ህዝብ ላይ አድርገው። ኦሮሞ ጠንቅቆ ያውቅሀል። ጀሌዎችህ ያልገባቸው ይተዉሀል። በእኩይ ዓላማ የሚገድሉት አንድ ቀን ይበሉሀል። የኢትዮጵያ ህዝብም እስከወዲያኛው በቸልታ ይመለከተኛል ብለህ አታስብ!
በስተመጨረሻም፦
‘ጃዋር ጃዋር ጃዋር እያላችሁ አገነናችሁት፤ ዝም በሉ’ የምትሉን ድንዙዛን ወድኩማን፤ ዝም ቢባል ይህ ሰው መዳረሻው የት ነው?!
አሁን በማጋለጣችን  እየነቃበት ያለ ህዝብ ብዛት ምን ያህል ነው?!
*
ለመሆኑ የአፄ ምኒልክ ያልሠሩት ወንጀል ተደጋግሞ መነገሩ ምኒልክን ለኦሮሞ ወጣት አቀረባቸው ወይስ ሰይጣን አድርጎ ዐሳያቸው?! በተመሳሳይ – የጃዋር እኩይ ሥራዎች አለመገለጣቸውና በክፋት መቀጠሉ ዝም ይባል ካላችሁ – ያውናላችሁ። ፕሮፓጋንዳ በአፀፋ ፕሮፓጋንዳ ካልተመታ አውዳሚነቱን – በየተራ ደርሶ ሲያቃጥላችሁ ብቻ ትገነዘቡታላችሁ።
Filed in: Amharic