>

የኒውዮርኩ"ፌስ ቱ ፌስ አፍሪካ" ስለ ቄሮ መንጋ እና ስለ አብይ ዘረኝነት ጽፏል!!! (ቅዱስ ማህሉ)

የኒውዮርኩ Face2face Africa – ስለ ቄሮ መንጋ እና ስለ አብይ ዘረኝነት ጽፏል!!!”
ቅዱስ ማህሉ
 
 ባድመን ለኤርትራ ለመስጠት መስማማቱንም በሰፊው አትቷል!!! 
 አብይ አህመድ ገድለው አስከሬን የሚጎትቱትን ቄሮ የሚባሉትን የኦሮሞ መንጋዎች እና የሚገደሉትን ሰዎች እኩል አውግዟል በማለት ዘረኛ መሆኑን ያትታል። ጽሁፉ ጃዋር መሐመድ በውሸት የፌስቡክ ጽሁፍ ሰዎችን እንዲገደሉ ማድረጉን እና ጥቃቱ መጤ በሚሏቸው አማራዎች ላይ የተነጣጠረ ቢሆንም ግድያዎቹ ሃይማኖታዊም ጭምር መሆናቸውን ገልጿል።  በጽሁፉ ኦሮሞ የሆኑ ክርስቲያኖችም ጭምር መገደላቸውን ገልጿል። ከአማራ በተጨማሪ የወላይታ፣ የዶርዜ፣የጉራጌ እና ጋሞ ሰዎች በኦሮሞ የቄሮ መንጋ በመጥረቢያ እየተመቱ መገደላቸውን አስፍሯል። ይህ ሁሉ ሲሆን ኖቤል የተሸለመው አብይ አህመድ ድርጊቱን በማውገዝ ፋንታ ቄሮዎቹን ይረዳሉ በሚባሉት የኦሮሞ ክልል አስተዳደር እና እራሱ በሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የውሸት ቁጥር ቀምረው ብዙ ኦሮሞዎች የሞቱ በማስመሰል ለአጥቂዎቹ እና ገዳዮቹ ኦሮሞዎች ሽፋን ሰጥቷል በማለት ኮንኗል። አብይ አህመድ ከጎሳ ወገንተኝነት ወጥቶ ህግና ስርዓት ለማስከበር ካልቻለ በኢትዮጵያ ከሰላም እጦት በተጨማሪ ኢኮኖሚውም ጭምር መናጋቱ እንደማይቀር እና በየቦታው ሁሉም  ጉልበተኛ ሆኖ እንደሚነሳ ጽፏል። መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው ፌስ ቱ ፌስ አፍሪካ በጽሁፉ ውስጥ አብይ አህመድን ለኖቤል ሽልማት አብቅቶታል የተባለው ከኤርትራ ጋር የተደረገው ስምምነት  ባድመን ለኤርትራ አሳልፎ መስጠት መሆኑንም ጠቁሟል።
ከኤርትራ ጋር የተደረገው “የሰላም ስምምነት” ለህዝብ ይፋ ያልተደረገባቸው ከዚህም በላይ ሌሎች ብዙ ሚስጥሮች ይኖሩታል። በጣም የሚያሳዝነው ዛሬ የብልጽግና ፓርቲ በሚባለው የአዲሱ ኢህአዴግ መመሪያ አንድ አንቀጽ ላይ “ፓርቲው በሃገር እና በህዝብ ላይ ከባድ ተጽእኖ የሚያሳርፉ ውሳኔዎችን በሚወስን ጊዜ ውሳኔውን የሚያሳልፉት የፓርቲው አመራሮች በሚስጥር ይይዛሉ” ይላል። ይህ አንቀጽ አብይ በግሉ የወሰናቸውን እንዲህ ያሉ ውሳኔዎችን በአዲሱ ፓርቲ የህጋዊነት ሽፋን ሰጥቶ  ለማጸደቅ የተዘጋጀ እንጅ የአንድ ሃገር ፓርቲ በህዝብና በአገር ላይ ከባድ ተጽእኖ የሚያሳርፉ ውሳኔዎችን ሲወስን ሚስጥር ያድርግ የሚባል አሰራር የለም። እንደዚያ ዓይነት ከባድ ውሳኔዎች ሲጀመር መወሰን የለባቸውም። ልብ አድርጉ አብይ አህመድ ባድመን አሳልፎ የሰጠው ኢትዮጵያዊያን ህወሃትን  ስለጠሉት ያን ባደርግም “እሰይ” ይላሉ ብሎ ነው። ይህ ያደረገው ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በድምጹ ሳይመርጠው እና ህጋዊ የህዝብ ውክልና እንኳ ሳይሰጠው ነው። ለባድመ 70ሽህ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን ገብረዋል። ምንም ይሁን ማን ኢትዮጵያዊያን ሳያውቁ ለማንም ስንዝር መሬት የመስጠት መብት የለውም። እስኪ ባድመን ለመስጠት ሲፈራረም አሰብን ለማስመለስ ያደረገውን ጥረት ምን ይሆን? ለማንኛውም ከኤርትራ ጋር የተደረገው ስምምነት በጊዜ ይፋ ካልተደረገ ወደፊት ትልቅ ችግር ማስከተሉ አይቀሬ ነው።
ሙሉ ጽሁፉን እዚህ አንብቡ!
Filed in: Amharic