>
5:13 pm - Friday April 19, 6633

የአረብ ሊግ ፓርላማ ለግብጽ ወግኖ   ለጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ደብዳቤ ጻፈ

የአረብ ሊግ ፓርላማ ለግብጽ ወግኖ  ለጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ደብዳቤ ጻፈ
ዘመድኩን በቀለ
~ አሜሪካ፤ በግብጽ የተዋጊ ጀቶች ሽመታ ተቆጣች!!
•••
የአረብ ሊግ ፓርላማ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ፓርላማ አፈጉባኤ ደብዳቤ መጻፉን የግብጹ አህራም ኦንላይን ዘግቦታል፡፡ ፓርላማው በደብዳቤው ከሱዳንና ግብጽ ጎን እንደሚቆም አመልክቷል፡፡
•••
የግብጽና የሱዳን የውኃ ጥቅም መነካት እንደሌለበት የጠቀሰው ፓርላማው በህዳሴ ግድብ ሙሌት ዙሪያ ፍትሀዊ ስምምነት ሦስቱ ሀገራት እንዲያደርጉ ማሳሰቡን ዜናው ይገልጻል፡፡
•••
የሊጉ ፓርላማ አፈጉባኤ ፋህም አል-ሰላሚ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይህንኑ የደብዳቤ ልውውጥ ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚሁ ትዊታቸው ላይ ኢትዮጵያ የግብጽንም ሆነ የሱዳንን ጥቅሞች እንድትጠብቅ በዳብዳቤያቸው ላይ ማስፈራቸውን አመልክተዋል፡፡
•••
በተያያዘ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ግብጽ ከራሽያ 20 የተዋጊ ጀቶችን ልትገዛ ነው መባሉን ተከትሎ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ መስጠቷ ተሰምቷል። ግብጽ በሁለት ቢሊዮን ዶላር ወጪ 20 ተዋጊ ጀቶችን (Sukhoi Su-35 ) ከሩስያ ልትገዛ በዝግጅት ላይ መሆንዋ መሰማቱ የአሜሪካ መንግሥትን አስቆጥቷል። ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው የግብጽ እርምጃ በሁለቱ አገሮች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ወታደራዊ ግንኙነትና ትስስር የሚጎዳ ነው ብለዋል ነው የተባለው።
•••
ሲጠቃለል ዐረቦቹ ሊውጡን አሰፍስፈዋል። የባሌና የአሩሲ የኦሮሞ አክራሪ እስላሞች በጃዋር በኩል መናከሳቸው ሳያንስ አሁን ደግሞ ጭራሽ አረብ ሊግ ያስፈራራን ጀምሯል። አንዱ ሀጂ ጃዋር መሐመድ ዐቢይ አህመድን [ ወራዳ ነው ] እያለ እየሰደበው ሲያሽቆጠቁጠው ሲያዩ፣ በዚያ ላይ 3 ቢልየን ብር ጉርሻ በዐቢይ በኩል ለኦሮሞ ቄሮ የሚደርስ ጉርሻ ሲሰጠው ሲያዩ የልብ ልብ ሳያገኙ አልቀረም።
•••
ቱርክ ግን ሐረርጌ ውስጥ ምን እየሠራች ነው። ዳግማዊ የግራኝ አሕመድ ዘመን ሊመጣ ያለ ይመስላል። ማረዱ እንደሁ ያው በእነ አህመዲን ጀበል በይፋ ተጀምሯል።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ህዳር 9/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic