>

«ኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እስር ቤት» የነበረችው  መቼ ነው?!? ( አቻምየለህ ታምሩ)

«ኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እስር ቤት» የነበረችው  መቼ ነው?!?
አቻምየለህ ታምሩ
ደቂቀ ዋለልኝ  መኮንን በመንፈስ አባታቸው በኩል የተላለፈውን  የሻዕብያ ፈጠራ የኢትዮጵያ እውነት እንደነበር አድርገው ድርሰቱ የተጻፈበትን 50ኛ ዓመት ሲያከብሩ ሲሰነብቱ ዶክተርና ፕሮፌሰር የሚባሉት ሁሉ  አንዴም እንኳ ምሑራዊ አእምሯቸው ተጣልቷቸው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የነበረውን የኢትዮጵያ ገጽታ የሚያሳየውን ከታት በታተመው  የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጽሔት ላይ  የሚታየውን አይነት የኢትዮጵያ መልክ፤ የዘመኑ መንግሥትና አየር መንገዱ ኢትዮጵያ ለአለም ያስተዋወቁበትን ታሪክ ሊያወሱት አይሹም!
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀመሮ ባለ ብዙ ቋንቋ፣ ባለ ብዙ ባሕል፣ ባለብዙ ሃይማኖት አገር ነበረች። ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች የሚባሉትን የምትጨፈልቅና የምታጠፋ ቢሆን ኖሮ ከሶስት ሺህ  ዓመታት በላይ በቆየው የመንግሥትነት ታሪክ ውስጥ ሁሉን ድምጥማጡን አጥፍታ ለወሬ ነጋሪ እንኳ የሚተርፍ አልነበረም። እውነታው ግን  ብሔር፣ ብሔረሰብ የሚባሉትን ሰብስባ የኦሮሞ ገዢ መደብና ግራኝ ባካሄዱት ወረራና የማንነት ድምሰሳ ጨርሰው እንዳይጠፉ ያደረገችው ኢትዮጵያ ናት።
የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ መንግሥታት ጠብቀው ካቆዩዋቸው የኢትዮጵያ  ቋንቋዎች መካከል ወደ ሰላሳ የሚጠጉት የአገራችን ቋንቋዎች የጠፉት የኦሮሞ የገዢ መደብ በገዳ  ወታደራዊ ዘመቻ እየተመራ ባካሄደው ወረራ፣ ማፈናቀ፣ ማፍለስ፣ማንነትና ሃይማኖትን በግድ ማስለወጥ፣ መዋጥና  የዘር ማጥፋት  እንቅስቃሴ ነው።
ኢትዮጵያ «የብሔር ብሔረሰቦች እስር ቤት» የነበረችው የኦሮሞ ገዢ መደብ በገዳ እየተመራ በተከተለው የባህል ድምሰሳ፣ ከርስት ማፍለስና ቋንቋን የመጨፍለቅ ፖሊሲ ነበር። የኦሮሞ የገዢ መደብ  ከባሌ በታች ተነስቶ ሲስፋፋ የተከተለው የመስፋፋትና የወረራ ፖሊሲው «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል ነበር።  «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚለው የኦሮሞ የገዢ መደብ  ሲወር ይከተለው የነበረው ፖሊሲ ትርጉም «ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ”» እንደ ማለት ነው።
ብሔር፣ ብሔረሰቦች የሚባሉት እስር ቤት  የነበሩት «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል ፖለሲ የሚያራምድ የኦሮሞ የገዢ መደብ ከርስታቸው ሲያፈልሳቸው፣ ማንነታቸውን በሞጋሳ ቀይሮ ሌላ ሰው ሲያደርጋቸውና  ቋንቋቸውን ጨፍልቆ ገርባ ሲያደርጋቸው ነው።
ባጭሩ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች የሚባሉት እስር ቤት የነበረችው  «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል የገዳ ፖሊሲ ሲታወጅባት ነው። ዳግማዊ ምኒልክ ደርሰው  ብሔር ብሔረሰቦች የሚባሉትን የኦሮሞ የገዢ መደብ  ይከተለው ከነበረው ከዚህ ጨፍላቂ ወረራና የቋንቋና ባህል ድምሰሳ ፕሮግራም ባይታደጓቸው ኖሮ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የብዙ ነገዶች አገር ሳትሆን «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”»  የሚለውን  የኦሮሞ ገዢ መደብን የድምሰሳ ፕሮግራም መቋቋም የቻሉ የጥቂት ነገዶች  አገር ብቻ ትሆን ነበር!
ከታች የታተመው ሰነድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 25ኛ አመቱን ባከበረበት ወቅት ያወጣው የአየር መንገዱ  ሰላምታ መጽሔት ሽፋን  ነው። በዚህ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በታተመው የአየር መንገዱ መጽሔት  ላይ የወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ የብዙ ባሕሎች፣ ቋንቋዎች፣ ሃይማኖቶችንና ማንነቶች አገር፣  አቃፊና አካታች መሆኗን  የሚያሳይ ነው።
Filed in: Amharic