>
5:13 pm - Monday April 19, 7199

ይድረስ ለጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ!!! (ሀብታሙ አያሌው)

ይድረስ ለጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ!!!
ሀብታሙ አያሌው
አስቀድሜ ጥያቄዬ በጨዋነት በውስጥ መስመር እንዲደርስዎ አድርጌ ፍትህን ለማገዝ ብሞክር  እርስዎ የመፅሐፍ ቅዱሱ የኦሮዮንን መንገድ በመምረጥዎ በይፋ ለመፃፍ ተገድጃለሁ።  አሁንም መረጃው እንዴት እሱ ጋር ደረሰ የሚለውን ውትወታ ትተው በማንኛውም መንገድ ቀጥተኛ ምላሽ ይስጡኝ !!
ጀነራል ሰዓረ ከመገደሉ ከሦስት ወራት በፊት ከእርስዎ ጋር ስለነበረው ከፍተኛ ውዝግ በተለይም እርስዎ የመከላከያ ቁልፍ መምሪያዎች በምክትሉ እንዲታዘዙ በማድረግዎ ጀነራል ሰዓረ እና ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የተካረረ ፀብ እና አለመግባባት ውስጥ ገብተው እንደነበረ የሚክዱ አይመስለኝም።  ይህንን ዛሬ ቢክዱ ህያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ነገ በአደባባይ ያፍሩበታል።
ጀነራል ሰዓረ ከመሞቱ ከሁለት ሳምንታት ቀደም ብሎ የደህንነት ኃላፊ የነበረው ጀነራል አደም የመከላከያ ኢታማዦር ሹም ልሆን ነው ብሎ ቢሮውን ያን ጊዜ የአገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ ለነበረው ለደመላሽ እያስረከበ ነበር። እርስዎና ጀነራል ሰዓረ ከተቃቃሩበት ቀን ጀምሮ በሄዱበት ሁሉ ጀነራል ሰዓረን የቅርብ ጓደኛዎ አስመስለው ወደ ሚዲያ ይዘው እየመጡ ሲያሳዩአቸው፤ በርካታ ፎቶዎች አቅፈዋቸው እየተነሱ በሶሻል ሚዲያ ሲያስለቅቁ የተወሰኑ ሚስጥሮችን በጥንቃቄ ይዤ በእኔ ዙሪያ ላሉ የሰራ ባልደረቦቼ እና ጓደኞቼ እንዲያውቁት ሳደርግ ነበር።
በጥቅሉ ጀነራል ሰዓረ ከመገደላቸው ከሁለት ሳምንታት ቀደም ብሎ በላያቸው ላይ በሚስጥር የተሾመው ጀነራል አደም ከላይ እንደጠቀስኩት የደህንነት ቢሮውን እንዳስረከበ ልደብቅህ ቢሉት የማይደበቅ ሃቅ ነው።  የኔ ጥያቄ ጀነራል አደም ሲሾም ጀነራል ሰዓረ ላይ ምን ወስናችሁ ነበር ?  እንዲገደሉ ወይስ ሌላ ቦታ እንዲሾሙ ?  ጀነራል አሳምነው ፅጌንስ  እዚህ ውስጥ ምን አምጥቶ ባህርዳርን እና አዲስ አበባን አገናኛቸው ?
Filed in: Amharic