>
5:13 pm - Wednesday April 18, 9218

ስደት ወደ አዲስ አበባ ተጀምሯል!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

ስደት ወደ አዲስ አበባ ተጀምሯል!!!
ዘመድኩን በቀለ
ይህንን አሳፋሪ የሆነ መንግስታዊ  ሴራ ፋናና ኢቲቪ፣ ኦ.ኤም.ኤንና ዋልታ… እንደሁ አይዘግቡልህም! በል ነህ በእኔ ብለህ ለወገንህ ድረስ!!!
 
~ ስደት ሩቅ የመሰለህ አዲስ አበቤ መታወቂያቸው ብቻ ዐማራ ስለሚል በማንነታቸው እየተለቀሙ በቄሮ የተባረሩ ተማሪዎችን ጠዋት ዳቦ ይዘህ ሄደህ ጠይቃቸው።
 
•••
ከኢትዮጵያዋ ሶሪያ የአሁኗ ( ኦሮሚያ አሌፖ ) የዐማራ ነገድ በዘራችሁ ያለና ከዐማራ ክልል የመጣችሁ፣ የትምህርት ሚንስትር የመደባችሁ ተማሪዎች ከኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲ  ለቃችሁ ውጡልን ተብለው ፖሊስ እያየ፣ መከላከያም እየተመለከተ አልሸባብ ቄሮ ያባረረቻቸውን የኢትዮጵያ የዐማራ ስደተኛ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ አሁን ምሽቱን መግባት ጀምረዋል።
•••
 በ5 አውቶቡስ የተሳፈሩ በቁጥር 250 የሚሆኑ  ከጅማና ከአምቦ እንዲወጡ የተደረጉ የመጀመሪያዎቹ የዐማራ ስደተኛ ተማሪዎች ዛሬ ምሽት 2:00 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ከተማ ገብተዋል። በመርካቶ አውቶቡስ ተራ በሚገኘው አዲሱ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንም ተጠልለዋል። የአጥቢያው ምዕመናን፣ የደብሩ ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም የሰንበት ተማሪዎችም ስደተኛ የዐማራ ተማሪዎችን ተቀብለው ራት አብልተው በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ አሳድረዋቸዋል።
•••
የአዲሱ ሚካኤል ምእመናን ለስደተኞቹ ምግቡን፣ እንጀራውን ከየቤታቸው በማዋጣት፣ በርበሬና ጨው ሽሮም በማምጣት እዚያው በቤተ ክርስቲያኑ ጊቢ ውስጥ እያዘጋጁና እየሠሩ ነው ስደተኞቹን ተማሪዎችን እየመገቡዋቸው የሚገኙት። የአዲሱ ሚካኤል አጥቢያ የተዋሕዶ ልጆች ስደተኛ ተማሪዎቹን ተራ ገብተው በመጠበቅም ላይም ይገኛሉ።
•••
እነዚህ ዛሬ ከጅማና ከአምቦ የመጡት ተማሪዎች ኢንተርቪያቸውን እንደሰማሁት ከሆነ የአምቦ ከተማ ህዝብ ምንም ዓይነት በደል እንዳላደረሰባቸው፣ የሸዋ ኦሮሞ አቅፎ እንደያዛቸው፣ ነገር ግን እስላም ኦሮሞዎቹ፣ የባሌ፣ የአሩሲና የጅማዎቹ ዐማራ ሲያዩ እንደ አበደ ውሻ እንደሚያደርጋቸው፣ የወለጋዎቹ ደግሞ ፌሮና ድንጋይ አጣና ይዘው ተማሪ ብቻ ሳይሆን እረፉ የሚሏቸውን የመከላከያ ሠራዊት አባላት ካልደበደብን እያሉ እንደሚገለገሉ ነው የሚናገሩት።
•••
አስገድዶ መድፈርና ጠለፋውም ለጉድ ነው ይላሉ ተማሪዎቹ። መዳ ወላቡ፣ ድሬደዋና ናዝሬት በጭንቅ ላይ ናቸው። ድሬደዋ አንዷን ተማሪ አስገድደው ከደፈሯት በኋላ የዩኒቨርሲቲው ኃላፊ ምስጢር እንዳይወጣ ይዟት ወጥቶ የት እንዳደረሳት አይታወቅም ይላሉ ተማሪዎቹ። ሐረር ሆስፒታል የገቡ ተማሪዎች አሉ። ደምቢዶሎ የዐማራ ተማሪ መግደል እንደ ጽድቅ ይቆጠራል። የዛሬዋ ኢትዮጵያ ለኦርቶዶክስና መታወቂያው ዐማራ ለሆነ ሙስሊም ይሁን ጴንጤ ኦሮሚያ የምድር ሲዖል ሆናበታለች።
•••
እንደኔ እንደኔ ዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ቢቀር ይሻላል ባይ ነኝ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በሪፐብሊካን ጋርድ እየተጠበቀ አራት ኪሎ ተቀምጦ አንደሞዴል ተቀባብቶ፣ እንደ አክተር የሚያነበንበውን መነባንብ ወደ ጎን ትቶ የተማሪዎች ህይወት ሳይጠፋ በሰላም ሀገሪቷ መንግሥት እስኪኖራት ቢዘጋ መልካም ነው። እንዲያ ቢሆን የሰላም ኖቤል ሽልማቱም ትክክለኛውን ስፍራ ያገኝ ነበር።
•••
የሚገርመው ነገር ኦሮሚኛ የሚናገሩ ነገር ግን መታወቂያቸው ዐማራ የሆኑ በሙሉ ናቸው የተባረሩት። አባራሪው እኮ ዩኒቨርሲቲው አይደለም። አባራሪው ወታደሩ አይደለም። አባራሪው የኦነግ ቄሮ ነው። መከላከያውማ የወለጋው ኦነግ ኦቦ ለማ መገርሳ አርፈህ ተቀመጥ ስላለው ከተማሪው ጋር አብሮ ያለቅሳል። ትእዛዝ አልተሰጠን ምን እንርዳችሁ ይላቸዋል። ሲያሳዝን መከላከያ።
•••
በዐማራ ክልል የተመደቡ የኦሮሞ ተማሪዎች ይውጡልን ነው የሚሉት አሉ እነዚህ የአህመዲን ጀበልና የጃዋር አህመድ ቡችሎች። በዐማራ ክልል የተመደቡ የኦሮሞ ልጆች ደግሞ በጎንደር ጸሎት ላይ ናቸው። በባህርዳር ጣና ሀይቅ ዳር ዘና፣ ፈታ ብለው እያጠኑ ነው። ማርቆስ ደብረታቦር ዓለማቸውን እየቀጩ ነው። ወልድያም ፀቡ ህዝቡን የሚመለከት አይደለም። ደሴ ኮምቦልቻም የከሚሴ ኦነግና የወለጋ ቄሮ ለመበጥበጥ ቢሞክሩም እስከ አሁን አልተሳካም። ዐማራ ክልል ያሉ ኦሮሞዎች እንውጣ፣ ተበድለናል ሳይሉ የኦሮሚያ ቀሬናቄሮ በግድ ካልወጡ ማለት የጤና አይመስልም። ይሄ ምቀኝነት ነው። የዐማራ ህዝብ ግን አንዲት ነገር በደጅህ ኮሽ እንዳትል። ኬላዎችን፣ መግቢያ መውጪያ በሮችን በዐይነቁራኛ ጠብቅ። ጠብቅ ነቅተህ። ተንከባክበህ ያዝ ። አንድም ተማሪ እንዳታስከፋ። ወዳጄ ፍቅር ያሸንፋልን በተግባር አሳይ። ያኔ ታሸንፋለህ። ምክሬ ነው።
•••
ለማንኛውም አዲስ አበባ ስደተኞችን ተቀብለሽ አስተናግጂ፣ አብዛኛዎቹ ሻወር ያልወሰዱ፣ ልብስ የሌላቸው፣ የተራቡም ጭምር ናቸው። እናም ነግ በእኔ ነውና አስተናግዷቸው። የሴቶችን ገመና ለመሸፈን ከሴቶች በላይ የሚያውቅ የለምና ጎብኟቸው። የትራንስፖርት አዋጥታችሁ ሸኟቸው። አደራ፣ አደራ፣ አደራ፣
•••
አቢቹ ቅድም ሲበጠረቅ ሰምቼው በሳቅ ስፈርስ ነበር። ያለ በቂ ጥናት አጥር እንኳን የሌላቸውን በገጠር የሚገኙ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎችን ”ኮምፒዩተራይዝድ የአሻራ መለያ ቴክኖሎጂ መግቢያ በራቸው ላይ እንዲገጠምላቸው ይደረጋል፡፡” አለልኛ አባ መበጥረቅ፣ የእኔ ቀዳዳ። ጉድ እኮ ነው። ዩኒቨርሲቲዎቹ መጀመሪያ በር ሲኖራቸው አይደል እንዴ ፓስተርዬ። ወይስ አጠገባችን ያለውን ነካ አድርገን በቃ ከነገ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲዎቻችን አጥር በአጥር ይሆናሉ እንበል? አንተን ቶሎሳን ሳይሆን አንተን ነበር “ አፍራሽ ” ማለት። አፍራሽ  !! ሃሌሉያ  !!
ወንድሜ ያሬድ ሹመቴ በደንብ ተዘጋጅ። ነገም ከምሥራቅ ኢትዮጵያ በገፍ የሚገቡ ምስኪን ዐማሮችን ለመጎብኘት ሞክር። አደራ ወንድም ዓለም።  
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ህዳር 5/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic