>

ሰዓቱ ደርሷል! (አብርሀ በላይ)

ሰዓቱ ደርሷል!
አብርሀ በላይ
ሁለት አይነት ትግራዮች እንዳሉ ማወቅ አለብን። አንደኛው በትግራይ ተወልዶ የኢትዮጵያ መበታተን የሚመኝ ትግርኛ ተናጋሪ ነው። አንደኛው ደግሞ ኢትዮጵያን እንደ ወላጅ እናቱ አይቶ የሚሳሳላት፣ ህይወቱም የሚሰጥላት ነው።
የኢትዮጵያ ጠላት የሆነው ትግርኛ ተናጋሪ የህወሃትን አመራር ከተቆጣጠሪ ከ40 አመት በላይ ሆኖታል።  ኢትዮጵያን አፍቃሪ የሆነው ትግራዋይ ደግሞ የፖለቲካ መብቱ ተገፎ፣ በሁሉም መስክ ተዳክሞ ይገኛል። እንዳውም ለመኖር ሲል፣ የባንዳዎች ስርዓት ደጋፊ መስሎ ይኖራል።
በርግጥ፣ የአሉላ ልጆች የሆኑት የዓረና ትግራይ ጀግኖች አሉ። ግን በሰፊው ህዝብ ካልተደገፉ እነዚህ ጥቂት ነብሮች ብቻቸውን የት ይደርሳሉ?
የትህነግ አመራር አባላት ኢትዮጵያ ምናቸውም አይደለችም። በርግጥ፣ ሀብት እንደልብ የሚዝቁባት ሀገር ሆና ስላገኝዋት፣ “ገዢዎች” መስለው ለመኖር ሞክረዋል። 27 አመት መቆመርም ቀላል አይደለም።
የአሁኑ ከአብይ ጋር የሚያደርጉት ውህደት ግን አይኖርም። በጭራሽ አይኖርም። አብይም ውህደት፣ ውህደት የሚለው ሰብሰብ አርጎ፣ ወቅቶ ለመግዛት እንዲያመቸው ነው እንጂ የህግ የበላይነት የተከበረባት ኢትዮጵያ ተመኝቶ አይደለም።
ሌላውን እየደፈጠጠች የኖረችው ትህነግም በአብይ መደፍጠጥ ቀርቶ “መደመር” ተፈጥሮዋ አይፈቅድም። ስለዚህ ትህነግን የሚያጠፋ የተደራጀ ኃይል ስለሌለ፣ የትህነግ የመጨረሻ እርምጃ እንዳይንዋ ብሌን ስትንከባከበው የኖረችውን አንቀጽ 39 ተጠቅማ ትግራይን ይዛ መገንጠል ነው።
በጠላት ስንገዛ እንደኖርን ለማናውቅ ይህ ተራ ፅሁፍ ሊመስል ይችላል። ለአዋቂው ግን የኖረ ሀቅ ነው። በርግጥ የትግራይ ህዝብና ኢትዮጵያዊነት የሚነጣጠሉ አይደሉም። ግን 40 አመት የተቀጠቀጠ ህዝብ የት ይደርሳል? የትም! ወገን፣ አትዘናጋ። ሰዓቱ ደርሷል። ህዝብህን አደራጅ!
Filed in: Amharic