>
5:13 pm - Saturday April 19, 9614

“ ቀበሮ ዳኛ ሆኖ በተሰየመበት ችሎት የበጎች ዕጣ ፈንታ የታወቀ ነው።.... !!!” ( ዘመድኩን በቀለ )

ዛሬ ደግሞ ተረኛዋ ተዋናይ ኬሬያ ኢብራሂም ነች!!!
ዘመድኩን በቀለ 
 መንግሥታዊ ሽብር ስለሆነ መፍትሄ የለውም።
 “ ቀበሮ ዳኛ ሆኖ በተሰየመበት ችሎት የበጎች ዕጣ ፈንታ የታወቀ ነው። ሳይታለም የተፈታም ነው!!!”
•••
የመጀመሪያው ዕርድ ከፈጸሙብን በኋላ ዐቢይ አህመድ ቤተ መንግሥት ጠርቶ አላገጠባቸው። ቀጥሎ ደግሞ አክራሪዋ የሰላም ሚንስትትር ሙፈሪያት ካሚል መጥታ ፎጋግራ ተመለሰች።
•••
በቅርቡ ደግሞ መርዘኛውና ተደብቆ ነዳፊው እስላሙ ደመቀ መኮንን፣ ጴንጤው ለማ መገርሳና “ ኢንሻላህ ዓለም በሙሉ በቅርቡ ኢስላምን ይቀበላል በማለት በግልጽ የምትሰብከዋን አክራሪዋ ሙፈሪያት ሆነው ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከእንግዲህ ቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ ጥፋት አይደገምም በማለት ቀልደውባቸው ሄደዋል።
•••
አሁን ደግሞ ትናንት ሐረርጌ ላይ ቤተ ክርስቲያንን ችቦ ደመራ አድርገው ካቃጠሉና ካወደሙ በኋላ ቶሎ ብለው በፌዴሬሽን ምክር ቤት በኩል ቤተ ክርስቲያን ስትቃጠል፣ ምዕመናን ሲታረዱ ምንም የማይተነፍሱትንና ከሁሉም የኃይማኖት መሪዎች የተውጣጡትን ውስጠ ዝዎችን ስብሰባ ጠርተው ፓትሪያርኩንና ሊቃነ ጳጳሳቱን እንደ ህጻን ልጅ በቅቤ ምላሳቸው እያደነዘዙዋቸው ነው። የሚገርመው የዚሁ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ሰብሳቢዋ ደግሞ ኤርትራዊቷ  ኬሪያ ኢብራሂም የተባለች እስላም ናት። ምክትሎቿ ደግሞ ጴንጤዎች ናቸው። የምትነደውና የምትቃጠለው ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት።
•••
ዐቢይ አህመድ፣ ደመቀ መኮንንና ለማ መገርሳ ግን ተደብቀው ይስቃሉ። ሙፈሪያት ደግሞ ይሄኔ ሌላ ፕላን ከነ ጃዋር ጋር እየነደፈች ነው። ጃዋር ደግሞ ለቤንዚንና ለገጀራ መግዢያ የሚሆን ገንዘብ ሊያሰባስብ ወጣ ብሏል። ድራማው ይቀጥላል። ቃጠሎውም ይቀጥላል።
•••
አቃጣዩ ራሱ መንግሥት ሆኖ ሳለ የሃይማኖት መሪዎቹን ሰብስቦ መነዝነዝ ምን የሚሉት ነው? መንግሥቱ ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ አልፈለገም። አልቻለምም። ደግሞም በደሴው ስብሰባ ገና ወደፊትም ይቀጥላል እኮ ብሏል ሰውዬው።
•••
ሻሎም  !   ሰላም  !  
ህዳር 4/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic