>

የባላአደራ ምክር ቤት በአፄ ምኒልክ  ሐዉልት አደባባይ ውስጥ ታጥሮ የተቀመጠው የቆርቆሮ ቤት እንዲፈርስ  አሳሰበ!!!

የባላአደራ ምክር ቤት በአፄ ምኒልክ  ሐዉልት አደባባይ ውስጥ ታጥሮ የተቀመጠው የቆርቆሮ ቤት እንዲፈርስ  አሳሰበ!!!
ጉዳዩ፡- በአጼምኒልክ አደባባይ ስለተሰራው ቆርቆሮ ቤት
 
       በምኒልክ አደባባይ የታላቁ ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መታሰቢያ  ሀውልት  ቆሞ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ሀውልቱ የአዲስ አበባ መለያ ሆኖ ከመቆየቱም ባሻገር፣ ከአድዋ ድል ጋር በተሳሰረ የመላ አፍሪካዊያንም ኩራት መገለጫ ሆኖል፡፡ በዚህም ሳቢያ፣ በመላ ኢትዮጵያዊያን ዘንድም ሆነ በአፍሪካዊያን ዘንድ በታላቅ ከበሬታ የሚታይ ነው፡፡
   ሆኖም፣ ቀላል ለማይባል ጊዜ ሀውልቱ በሚገኝበት አደባባይ  ህገ ወጥ የቆርቆሮ ቤት ተገንብቶ ይገኛል፡፡ ይህ ህገ ወጥ ቆርቆሮ ቤት የታላቁን ንጉሰ ነገስት ክብር ለመንካት ሆን ተብሎ ከመቆሙም ባሻገር፣ የከተማዋን መልካም ገፅታ በእጅጉ አበላሽቶታል፡፡
   ይህን አስመልክቶ ህዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረበ የሚገኝ በመሆኑ፣ በህዝቡ ጥያቄ መሰረት ህገ ወጡ ቆርቆሮ ቤት እንዲፈርስና በአደባባዩ ላይ ምንም ዓይነት ህገ ወጥ ግንባታ እንዳይደረግ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ በትህትና እንጠይቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር 
 
እስክንድር ነጋ 
የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት ሰብሳቢ
አዲስ አበባ
—–
በቆርቆሮ ቤቷ ውስጥ እንዲሁም በግቢዉ ውስጥ የሚታየው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ
የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሐዉልት በቅርብ ጊዜ እድሳት ተደርጎ ከተጠናቀቀ በኃላ ለእረጅ ጊዜ ታጥሮ የተሰራዉ የቆርቆሮ ቤት እንዲሁም በግቢዉ ውስጥ የሚታየው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ልብስ እያጠቡ የሚያሰጡ ግለሰቦች መኖራቸው በተደረገዉ ማጣራት ከህዝብ በመጣ ጥቆማ ለመታዘብ ተችሏል፡፡
///
 ባለአደራዉ ይህን የህዝብ ጥያቄ ከግምት በማስገባት የሚታዩ ስጋቶችን ለመቅረፍ የተሰራው ቤት በፍጥነት እንዲፈርስ በውስጡ የሚታየዉን የፅዳት መጓደል እንዲስተካከል ለአራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ዘርፍ በደብዳቤ አሳስቧል፡፡
ይህን ጥያቄ የተቀበሉት የአራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ በአጭር ጊዜ ከአመራሩ ጋር በመነጋገር መልሳቸዉን እንደሚያሳውቁ በቃል አስረድተዋል፡፡
Filed in: Amharic