>

በአገራችን የተከሰተው የአምበጣ መንጋው ትልቅ  ስጋት ደቅኗል!!! (ኡስታዝ አቡበከር)

በአገራችን የተከሰተው የአምበጣ መንጋው ትልቅ  ስጋት ደቅኗል!!!
ኡስታዝ አቡበከር
ሰሞኑን በአፋርና በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ አሁን ደግሞ በወሎ አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ ተስፋፍቶ የአርሶ አደሩ የልፋት ውጤት ላይ አደጋ ደቅኗል። በአካባቢው ያሉ አርሶአደሮች እና ነዋሪው በራሳቸው አቅም ለመከላከል የሚያደርጉት ጥረት የአንበጣ መንጋውን ሊከላከለው አለመቻሉን መረጃዎች እየደረሱን ነው።
ባለው መረጃ ገና ከመጀመሪያው አምበጣው የደ/ወሎ የአርሶ አደሩ ምርት 20% አውድሟል።
ይሄ ደካማና የተሰሩ ልማቶችንና ሰብአዊ ፍጡር ሲያልቅ የማይሞቀው የማይበርደው መንግስት በባለፈው ሳምንት በግብርና ሚንስትሩ በኩል ብቅ ብሎ ” አምበጣው ምርት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ከምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አምበጣ መከላከያ ጋር በመቀናጀት ከ8ወራት በፊት ቀድመን በመዘጋጀታችን አምበጣውን 95% ተቆጣጥረነዋል” ብሎን ነበር።አምበጣው መሬት ላይ እንደማይታይ በወረቀት ላይ እንደሚዋሹት መስሏቸው ነበር።እነሆ የወሎ ገበሬዎች የደከሙበት ምርት እስከ 20% መውደሙን የደ/ወሎ ግብርና መምሪያ ም/ሀላፊው ገለፀዋል።
በመሆኑም መንግስትም ሆነ ሌሎች የማህበረሰብ ስብስቦች የጋራ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ህዝባችን እየተጋፈጣቸው ያሉ ችግሮች ሁሉ የጋራ ጥረታችንን ይፈልጋሉ።
አንበጣ በቁርአን የተገለፀበት መንገድ…
 
አላህ በቁርአን ውስጥ አንበጣን እንደ ምሳሌ የተጠቀመው የትንሳኤ ቀን (የውመል ቂያማ) የሰው ልጆችን ሁኔታ ለመግለፅ ነው፡፡ 
“ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ኾነው፤ ፍጹም የተበተነ አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወጣሉ፡፡” ሱረት አል ቀመር 54፡7
 
አንበጣን እንደ ምሳሌ መጠቀም ለምን አስፈለገ?
 
በሚወለዱበት ጊዜ ከምድር ከወጡ በኋላ በጣም በከፍተኛ ቁጥር በሚልዮኖች በመሆን መሰባሰብ ይጀምራሉ፡፡ ልክ እኛ አላህ ፊት ስንቆም እንደምንሰበሰበው፡፡ ከ40 እስከ 80 ሚልዮን የሚሆኑ አንበጣዎች አንድ መቶ ሄክታርን ይሸፍናሉ፡፡ የተለያዩ የአንበጣ ቡድኖች አንድ ላይ ሲሰበሰቡ ደግሞ እስከ አንደ መቶ ሃያ ሺህ ሄክታር ይሸፍናሉ፡፡ በአንድ ቦታ ላይ ሲከሰቱም በሚያስፈራ ብዛት በመሆኑ የአካባቢው ሰማይ ሊሞሉት ይችላሉ፡፡ 
 
በሀገራችንም ይሁን በየተኛውም የዓለም ዳርቻ ይህ የእህል ፀር የሆነ ፍጥረት በእንዲህ ያለ አስፈሪ ቁጥር ሲከሰት አላህ ፊት የምንቆምበትን ቀን እናታውስ፡፡ ከክፋቶች ታቅበንም ወደ አላህ እንመለስ፡፡ ጉዳቱ የደረሰባቸው አካባቢ ወገኖቻችንንም እናግዝ፡፡ አላህ ሆይ ምድራችንን ሰላም አድርግልን፡፡ ከመጣብን ፈተናም አንተ ጠብቀን፡፡
Filed in: Amharic