>

የሚያብረቀርቅ-ፖለቲካ ሁሉወርቃዊ-ሀሳብ እንዳልሆነ በድንግርግሮሽ ወይስ በወፍ-ማስፈራሪያ   ላረጋግጥልዎት? (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ...)

የሚያብረቀርቅ-ፖለቲካ ሁሉወርቃዊ-ሀሳብ እንዳልሆነ በድንግርግሮሽ ወይስ በወፍ-ማስፈራሪያ  ላረጋግጥልዎት?

 

  ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
 እምዬ፡ምኒልክ፡/፡

በቅሎ፡ስጠኝ፡ብዬ፡/፡እኔ፡አልለምንኽም፤
ካባ፡ስጠኝ፡ብዬ፡/፡እኔ፡አልለምንኽም፤
ብርም፡ስጠኝ፡ብዬ፡/፡እኔ፡አልለምንኽም፤
አምና፡ነበር፡እንጂ፥/፡ዘንድሮ፡የለኽም።
(ይህ፡ግጥም፡የተገጠመው፥የዐፄ፡ምኒልክ፡መሞት፡ተደብቆ፡ሳለ፥ባ፲፱፻፯፡ዓ.ም.፡ነው።)
ሰው በቁም ይሞኛል አለሁኝ እያለ፤
ሞት እንቅ አድርጎት በ
ተስፋ እየሳለ። ዐ/ዒ/ሥ/ወ

መቼም በተራው አነጋገር ስንመለከት አቀፈም አዘለም ሁለቱም ተሸከመ ቢሆንም በጣም ቀርበን ስንመረመረው፣በሕግ እይታ፦ከፊት ነው ከኋላ የሚል መጠይቅ ያስነሳል።ፖለቲካም ከውስብስብነቱ ብዛት ለመፍታት ሺህ ችግሮችን ይነካካል፤ ይጠላልፋል።ብልህነት እና አስተዋይነት ሊኖረን የሚገባውም፤ የፖለቲካን ባሕርይ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ነው።
ድንግርግሮሽ Equivocation/ስርቅ/ድብልቅልቅ ማለት የሌላን ሰው ሀሳብ አጣሞ በመወከል፣ ይህን የተጣመመ ሀሳብ በማጥቃት፣ ዋናውን ሀሳብ ያጠቁ ማስመሰል ነው።
የወፍ-ማስፈራሪያ Strawman/፤ ከአንድ ሰው ሀሳብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር ግን በቀላሉ ሊሸነፍ የሚችል ሀሳብ ማቅረብ ነው።

ይህን ጦማር በምፅፍበት ወቅት በጉጉት ስንጠብቀው የነበረውን የኢትዮጵያ መሪ የእርስዎን መግለጫ በጥሞና ደጋግሜ ከሰማሁዎት በኋላ ነገሮችን ማጣፋቱን ተያያዝኩት ብዙዎችን ነገሮች አላካተቱም ምን አማራጭ አልኩና ይሁና ብዬ አንዲት ጥያቄ ብቻ ላቀርብልዎት ወደድኩ፤የሰው ተስፋስ ቢሆን አንድዬ አይደለም፤ተጨባጭ ሁኔታዎችን ባገናዝብም ልቦናዎትን እንዲያስፋልዎት እፀልይሎታለሁ።
ክቡር ዶ/ር ጠ/ሚ ሆይ ምንም ይሁን ምን ኢያጎን ለምንድነው የማያጋልጡት ሌሊት ጭምብል አድርጎም ይሁን አስደርጎ ጁዋርን ሊገድለው የመጣውም ሆነ፣ያልተፈጠረ ሽብር ነው ቢባል እንኳን ስለ እነዚህ ጉዳዮች አንዳቺም ሳያነሱ እንደገና ዛሬም ሰማኒያ ሁለት ዜጎቻችንን በአፅማቸው እንዲቀሩ አስደረግን።የእነ ዶክተር አምባቸውን ግድያ ሆይ ሆይ ብለን፣ቆስቋሾቹን ሳናውቃቸው አዘናግተውን ሞታቸው በወረት ቀረ፤እንኳን ከትግሬዎችም ሰው አልሞተ፤እንደሚባለውና በሕዝብ መገናኛ እራሳቸው እንደሚነግሩን የሸፈተው ኦነግ እና ሕውሃት ተስማምተናል ብለዋል፤ምንም እንኳን ስምምነታቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ ባያደርጉም።ክቡርነትዎ ዕውነት ከሕውሃትና ከሸፈተው ኦነግ ሌላ እርስዎ ብቻ የሚያውቁት ድብቅ ጠላት አለን ብለው ያምናሉ?በእኔ ይሁንብዎና የውጭ ጠላቶች የሉንም፤የፈለገውም ያህል ቢሆን የ እኛው እጀታ ከሌለው መጥረቢያ ምን ያህል የሳለ ቢሆንም ተራ ብረት ነው።ጀርባችን ላይ ቅማሏ ተደብቃ ደማችንን ስትመጥና መቆሚያ መቀመጪያ አሳጥታን ቡታንታችን ውስጥ ተለጥፋ ስትመገምገን፣ እጃችንን የምናክ ከሆነ ጭንቅላታችንን ታመናል ማለት ነው፤ሕጻናት እንኳ ሲመጠመጡ እሪ ብለው የለቅሶአቸውን መጠን አምርረው ያሰማሉ፣እናሳ?ሁሉንም ትተው ኢያጎዎችን ለሕዝቡ ይንገሩን ብዬ እለምንዎታለሁ።ምክንያቱም እስኪ ፖለቲካውንም እንደሚሆነው ይሁንና የነገውን የባሰውን ኢያጎዎች ሳያመጡ ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ ቢያደርግ እነዝናሽንም ሊያተርፏት ይችላሉና ነው።
መቼም ሰውን እንደጨው አሊያም እንደስኳር ቀምሰን የምናውቅበት ሁኔታ የለም፤ሆኖም የምናመዛዝንበት መንገድ ግን ከምንም ይሻላል ብለን የምንመርጥበት ዘዴ የሕይወት ልምድና ዕውቀት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሲሆኑ፤ግልፀኝነት ግን ይቋጥራቸዋል።እኔ በዕውቀቴም ሆነ በሽልንጓ የዕድሜዬ ተመክሮ የማውቃቸው ናቸው፤የእነዚህ መመዘኛዎች ልምድ የሚለኩበት አንዱ ዘዴ”ጌም ጨዋታ”ን በተለያየ መልኩ ማወቅ ነው፤ልምድ የሚለኩበት የአዕምሮ ስፖርት ነው።
የተከበሩ ጠ/ሚር ኮነሬልና ዶክተር ዐቢይ አህመድ እኔ አሁን የምነጋገረው በደጋፊዎችዎ አማካኝነት ከእርስዎ ጋር ነው፤በርዕሱ ላይ በመጠይቅ የቀረበው ተምሳሌታዊ ጥገኛ ሐረግ፣ግልፅና ቀጥተኛ ነው።መጀመሪያ በእሳት ለመፈተን እንዲያስችለን በስምምነት ወርቆቹን ከአርቴፊሲያሎቹ(ሰው ሠራዎቹ) እንለይ፤መለኪያችንን ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን እናድርግ፣ለምን ቢባል፣ሁላችንም ለኢትዮጵያዊነት ነውና የምንታገለው።እኔ የምታገለው ለዘሬ ነው የሚሉትም እራሳቸውን ይዘው ከሌሎች ዘሮች ጋር ሆነው የራሳችውን መመዘኛዎች ሊጠቀሙ ዲሞክራሲያዊ መብት አላቸው፤ሁላችንም ግን በኢትዮጵያ ሕዝብ የመዳኘት ግዴታ አለብን።
እንደው ለማስገንዘብ ነው፤የፓርቲዎ አባላት የነበሩትና ዛሬ ዛሬ የራሳቸውን ዋሻ ቆፍረው የሚንፈራገጡትን አይዘነጓቸውም፤እነርሱ እንግዲህ እንደሚያውቁት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መዝረፋቸውን ከኢትዮጵያ የብሊዮን ዕዳ መዝገብና ወደውጭ የሸሹባት ብሊዮን ምንዛሪዎች አይዘነጋዎትም።እንግዲያውስ ዕርምዎትን ያውጡ! ያ ሁሉ በአቁማዳ እየተቋጠረ የተዘረፈውን ገንዘብ አህያዋ ተሸክመዋለች፤ከእንግዲህ የማትከፍተው ዋሻ የለምና፣የተደበቁበት ጉድጓድ ብቻ ሳይሆን ቤተመንግሥትዎን ሳይቀር ለመክፈት ገንዘቡን እንደጉድ እየዘሩት ነው።
ወደ ጉዳያችን እንጀምር መለኪያችን ለምን ኢትዮጵያዊነት ሆነ? ኢትዮጵያ የምትባል ዓለም በሕግ የሚያውቃት አገር ውስጥ ስለተፈጠርንና ዜጋዎቿም ስለሆንን።ጥ/እያንዳንዳችንን በዚህ የኢትዮጵያዊነት መለኪያ መሠረት ለኢትዮጵያ አገራችን ትግል በወርቅነት የሚያሥቆጥረን ተግባር ምንድነው? መ/ ዘር አይደለም፤ገዳይነታችንም ሊሆን አይገባውም፤ በሰብዓዊነት ላይ ያለን የትግል ስልት ነው፣የዘመናችን ትክክለኛው መመዘኛችን ይህ ብቻ ነው።ይህን የወርቅ አስተሳሰብ ዘመናዊ መመዘኛ የማይቀበል እንደፈሪው”ጀግና ነኝ”ባይ አሁንኑ “የፈራ ይመለስ”እላለሁ፤ የመደመር ስሌት ተግባራዊነት ማጠቃለያም ይሄው ሊሆን ይገባል።
ወንድሞቼ እና እህቶቼ ኢትዮጵያዊ ናችሁ፤ኑና እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ተቀምጠን ችግራችንን እንፍታ።እንግዲህ አንድ በወንድሜ በኩል የመጡ አርባ አምስት ሰዎች አሉ፤እንዲሁም ሁለት በእህቴ ወገን ደግሞ ሃምሳ አራት ሰዎች መጥታችኋል።እግዲህ የውይይታችንን ሥርዓት ለመምራት በግልፅ ድምፅ ምርጫ እንመርጣለን።ማሳሰቢያ፦እነዚህ የሚባሉትን ዘመናዊ የምርጫ ስርዓቶች አልፈናቸዋል፤ ዛሬም ጠልፈው እንዳይጥሉን በዘዴ ልናልፋቸው የሚገቡት ሴራ፣ተንኮል፣ዘረኝነት፣ ቂም-በቀል፣ግልፀኝነት አለመኖር ናቸውና ተሰብሳቢው እነዚህ ጉድፎቻችን ብቅ ማለታቸውን ስታዩ እባካችሁ አሳውቁን።
በመሠረቱ ግልፀኝነት(ትራንስፓረንት ወይም ፕሮስትራይካ)የመደመር ዋናው ቅመም ነው፤ይህም ማለት ግልፀኝነት ጠላትን አያውቅም ማለት አይደለም፤በሚገባ ጠንቅቆ ያውቃል።ልዩነቱ ግን መደመር ሰብዓዊነትን አያስቀድም እንጂ ለግልፀኝነት ምንጊዜም ዝግጁ ነው፤ለዚህም ነው በተግባር መደመር ወደ ፖለቲካ የሚያመዝነው፤ሰብዓዊነት ግን ሰብዓዊነት ነው፣ግልፀኝነት ኖረውም አልኖረውም።ስለዚህም ነው መደመር የተወሰነውን ፐርሰንት ብቻ ወርቅ አስተሳሰብ ያለው፤አለበለዚያማ መደመር የፖለቲካ መሳሪያ አሆንም ነበር?ግልፀኝነት የዋሆችን ወደ ቂልነት ስለሚወስዳቸው፣ሊጠቀሙበት የሚገባ ሳይሆን፣ብልሆች በጥንቃቄ ሊመሩበት የሚገባ ዘመናዊ መሳሪያ ነው።እዚህ ላይ ነው የመደመር በጎ አስተሳሰብ ፖለቲካዊ አንድምታ መኖር መሰናክሎችን ለማለፍ የግድ ሰብዓዊነቶችን በመጣስ ከግልፀኝነት የሚያፈገፍገው።
ወደድንም ጠላንም የመደመር አስተሳሰብ በግልፀኝነት ካልታገዘ ሰብዓዊነትን የፖለቲካ ጎራ ውስጥ ይከተዋል፤ ምክንያቱም ስለተባሉ ሳይሆን በተግባር ሲፈተኑ መደመር ውስጥ ሳይሆን ነብስ ያለችው በሰብዓዊነት ሕይወት ውስጥ ብቻ በመሆኑ ነው።እነ ህሊና፣እነ ፍትህ እና ሰብዓዊ ፍጥረታት በሙሉ በሰብዓዊነት ውስጥ ተሟልተው ይገኛሉ፤ይህንን ለማረጋገጥ አሁንኑ ችግርዎን ያንሱና መፍትሔዎትን በመደመር እና በሰብዓዊነት መለኪያ ለመፍታት በአንፃራዊነት እስኪ ይሞክሩት፣እኔ እየሰማሁዎት ነው።
አሊያም የእኔን ላሰማሁዎት፦አሁን እኔ መጮህ እፈልጋለሁ እንዴት ላድርግ? መልስ/ከመደመር አስተሳሰብ አንፃር”የፖለቲካውን አካል(መንግሥት) ያስፈቅዱ፤”ከሰብዓዊነት አንፃር መንግሥትን አሳውቀው የሌሎችን መብት በማይነካ ሁኔታ፣መተርተር ይችላሉ፤”
ለእኛ ችግሩ የአቶ እንትና እና የእትዬ እንትና መዝረፍ አይደለም፤አቶ እንትና ሲዘርፍ የምናውቀው ነገር የለም፤ ከራሱም ሆነ ከሥራ ባልደርባዎቹዎ የተነገረ የለም፣እትዬ እንትና ሲሰርቁ ግን ሁሉም ሰው ያውቃል፦እንደሰረቁ ብቻም ሳይሆን እንደሚሰርቁም አገር በሙሉ ያውቃል፤ለምን ቢባል የሚተዳደሩት በዚሁ ሙያቸው ብቻ ነውና ነው።የአቶ እንትና ዘራፊነት ግን ከመሠረቱ በድንገት ሲነገረን፣ያ!ሁሉ ጨዋነት እንደዚያ ሰውመሳይ በሸንጎነት ሲረግፍ፣ለአንድ ሰሞን “ወይጉድ!!!” ከማለት በስተቀረ ለአቶ እንትና ሕዝቡ ምንም ነገር አያደርግለትም፤የዘረፈውን እንዲመልስ ከመጠየቅ አይመለስም።
እትዬ እንትና ግን እንድትሰራ ማን “ይሁንታ”?ሰጥቷት እንዳትለምን ከሰው ተራ ወጥታ የመጨረሻው ደረጃ ያወርዳታል፤እናስ ከነዚያ የመንግሥት የታሪክ ሕጋዊ ሌቦች እንደሚያደርጉት የሰማችውን ብትተገብርስ?እያዘናጋች መስረቅ ያዋጣታል፣መቼም የሚጠረጥራት የለም፣ተዘፍቃበታለች።ሴትነቷ የተዋጣላት ቢሆንም በተፈጥሮ ሥጦታዋ (በወርቋ)ነግዳ ለመኖር ካልፈለገችስ?ምን ተዕዳዋ!!! እትዬ አዜብ ጎላ እንኳ በሌብነቷ ቢሊዬርነር ሆናለች፤”በደም-ወዜ ነው እኔና ባሌ የምንተዳደረው” ስትል ሰምና ወርቁን ለይተን ሕብሩን ችላ ብለን ነበር፤ይሄው “ቦ ጊዜ ለኩሉ”ሆነና እንደአሻሮ አስፋልት ላይ ተሰጥቶ እንኳን እኛ ዓለም አወቀው፤ለካስ ደም-ወዝ የተባለው የስንቱን ሕፃናት እና ደሀ ደም ከነወዛቸው ምጥጥ ያደረገችበት ውስጠ ኑዛዜ ነበር።
አይዞሽ እትዬ እንትና “ስረቂ!!!እስካልተያዝሽ ድረስ ወንጀል ሰርቻለሁ ብለሽ አታስቢ፤”ይህ የባለራዕዩ ወቸገል ዜናዊ መመሪያ ነው።በሰላም እና መረጋጋት ሥም በየቀብሌው ሰው ቤት ዘው እያለ”ይፈለጋሉ”እያለ ሰላም ሲነሳን እንደነበረው፣አሊያም በካልቾ እና በጥፊ የተጫወተብን አጋዚ፤ካስፈለገሺም የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ፖሊስ፤የፌዴራል ተስፈንጣሪ ሲያሻውም ጨካኙ የጌም ጨዋታ ተጋጥሞ ደጋግሞ ሲሸነፍ ተጫውቶ ያልጠገበውና ዘርፈው ባሰሩት ሕንፃዎች ላይ እየተወራረዱ የሕፃን ጭንቅላት ሳይቀር በመቦርቀስ የሚቆምሩ ጠያቂ የሌላቸው፣ዛሬም በየሕንፃው ጫፍ ያሉ ሁሉ፣የፈለገው ቢመጣ አይነኩሽም።እነ ጋሼ እንትና እና እነ እትዬ እንትና ለንግድ ሥራ ብለው ወጥተው ክፍለሃገር ድረስ ሄደው አልቤርጎ ይዘው፣ሰርቀውም ሆነ ለምነው ገንዘብ ሸክፈው የሚመጡ ሞልተው የለም እንዴ! የልመና ዓይነቶች እና የሌብነትን ጥናት ይመለከቷል።
ያም ሆነ ይህ የምንፈልገው ወርቃዊ አስተሳሰብን እንጂ ባለአርተፌሻሉን አስተሳሰብ አይደለምና እንዴት ብለን መደመርንና ሰብዓዊ መብትን ልናጣጥማቸው እንደምችል ከማሰባችን በፊት ደግመን እንዳንሳሳት በ”ሰብአ ዐይን”ሳይሆን(ገንዘብ የተጫነች አህያ የማትከፍተው ዋሻ እንደሌለ ተገንዝበን)በንፁህ ልቦና(ከተንኮለኛው ተኩላ) ራሳችንን እንጠብቅ።
አለበለዚያ ግን በንግግር የሚያብረቀርቁትን ዓላማዎች ሳናጣራ፣”ወርቅ አስተሳሰቦ ናቸው፤”ያልናቸውን በጥንቃቄ አላገናዘብንምና ቆንጨራ እና ጠመንዣቸውን እስከሚያወጡብን ድረስ እንጠብቃለን።እናም አስገድደው እነርሱ የሚፈፅሙትን ርኩሰት እኛም እንድናደርገው ወደ ገደል ሊመሩን በዘረኝነት ይታጥቃሉና ከወዲሁ በሠለጠነ መንገድ እንደራጅ እንታጠቅ፤እናም የቅኝ ገዢዎችን በሐይማኖት፣በዘር፣በቋንቋ እና በጎጥ በመከፋፈል፣ እንደእንስሳ መሞከሪያ የዘረጉትን የኔትወርክ ረጅም ክንድ እንደአያቶቻችን በብልሃትና ዘዴ ለነፃነት ለመፋለም በልባችን እንቁም።በግልፅ በባሕላዊም ሆነ በዘመናዊ አሊያም በሐይማኖታዊ ሥርዓቶች በአደባባይ እንወያይ።ወርቃዊ-ሀሳብ ለማግኘት ዶክተር ዐቢይ አህመድ እርቅ እና ሰላማዊ ውይይት ከማድረግ የሚበልጥ መሳሪያ የለዎትም።
Filed in: Amharic