>
5:13 pm - Saturday April 19, 7755

"ቄሮ ከጨፈጨፋቸው መካከል ኦሮሞዎች ቢኖሩ እንኳ በሞታቸው አማሮች ሆነዋል!" (አቻምየለህ ታምሩ)

“ቄሮ ከጨፈጨፋቸው መካከል ኦሮሞዎች ቢኖሩ እንኳ በሞታቸው አማሮች ሆነዋል!”
አቻምየለህ ታምሩ
የሰላሌው ኦሮሞ ቄሮዎች ጥቃት ሲፈጽሙባቸው «ኦሮሞ ነኝ አትግደሉኝ» ሲሏቸው «ማተብ ያሰረ ኦሮሞ አናውቅም፤ አማራ ነህ» እያሉ እንደነበር ተናግረዋል። ጉራጌዋን ባለቤታቸውን ደግሞ ሲደበድቧቸው «ጉራጌ ነኝ» ሲሏቸው «ጉራጌ አይደለሽም መንዜ ነሽ» እያሉ ጥቃት እንደፈጸሙባቸው ተናግረዋል!!!
ዐቢይ አሕመድ ዐይኑን በጨው አጥቦ የነገረን በቄሮ በግፍ የተገደሉ ሰዎች ነገድ በሚገዛው አገር ውስጥ የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ እንዳልሆነ ለማሳየት ሆን ብሎ የቀቀለው ነጭ ውሸት ነው። ይህ ማለት ግን ኦሮሞ የሆኑ ሰዎች አልተገደሉም ለማለት አይደለም። እነዚህ ሰዎች ግን ቄሮ የገደላቸው አማራ ናችሁ  ኦሮሞ አይደላችሁም እያለ ነው። ለአስራት ቃለ መጠይቅ የሰጡት የሰላሌው ኦሮሞ ቄሮዎች ጥቃት ሲፈጽሙባቸው «ኦሮሞ ነኝ አትግደሉኝ» ሲሏቸው «ማተብ ያሰረ ኦሮሞ አናውቅም፤ አማራ ነህ» እያሉ እንደነበር ተናግረዋል። ጉራጌዋን ባለቤታቸውን ደግሞ ሲደበድቧቸው «ጉራጌ ነኝ» ሲሏቸው «ጉራጌ አይደለሽም መንዜ ነሽ» እያሉ ጥቃት እንደፈጸሙባቸው ተናግረዋል።
አይሲስ የሚባለው የቄሮ የጭካኔ አባት በ2015 ዓ.ም. ግብጻውያን ኮፕቲኮችን [ክርስቲያኖችን] መቅላቱን ያስታወቀው በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ እየተካሄደ ነበር። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ  ስብሰባውን እየተሳተፈ የዜጎቹን መቀላት  እንደሰማ የአዲስ አበባውን ስብሰባው አቋርጦ ከአዲስ አበባ ወደ ካይሮ በመብረር ብሔራዊ ሐዘን አውጆ  አፋጣኝ የአየር ጥቃት እርምጃ በአራጁ ቡድን ላይ ወስዷል።
ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ እነዚህ እርምጃዎች በፍጥነት የወሰደ የመሰለው አንድ የደህንነት ሰራተኛ የሆነ ምዕራባዊ ” አይሲስ ቀላኋቸው ያላቸው ሰዎች ግብጻውያን ስለመሆናቸው ምን ያህል እርግጠኛ ናችሁ?” ብሎ ሲጠይቀው  አልሲሲ በመልሱ “የተቀሉት ሰዎች ግብጻዊ ባይሆኑም እንኳ አራጁ ቡድን ግብጻውያንን አርጃለሁ በማለቱ ብቻ፡ ሟቶቹ ግብጻውያን ሆነዋል፤ ስለግብጽ ከመታረድ በላይ ግብዊነት ምን አለ? ቪዲዮውን አላየከውም እንዴ አራጁ ቡድንኮ ሰዎቹን  ሲያርድ ግብጻውያን አርጃለሁ እያለ ነው አንገታቸውን የቆረጠው፤ ማንም ይሁኑ ምን ግብጻውያን ተብለው በታረዱት ላይ ያረፈው ካራ የተቃጣው በግብጽ አንገት ላይ ጭምር ነው፤ በዚህም የተነሳ ግብጽ ታርዳለት፤ ስለሆነም በአጸፋዊ እርምጃየ እኮራለሁ እንጂ አልጸጸትም” ነበር ያሉት።
ቄሮ የቀላቸው ሰዎችም መታዬ ያለባቸው እንደዚያ ነው። ዐቢይ የቀቀለውን ቁጥር ትተን «ኦሮሞ ነን» እያሉ « ማተብ ያሰረ አማራ እንጂ ኦሮሞ አናውቅም»፣ «ኦሮሞ አይደላችሁም መንዜ ናችሁ» እያለ ቄሮ በግፍ  የገደላዎች ኦሮሞዎች የተገድሉት ስለ አማራ ነው። ቄሮ እነዚህ ሰዎች ሲቀላ  በጭካኔ እያረደ የነበረው « ነፍጠኛ፣ ሰፋሪ» ፣ «አማራ ናችሁ» ወዘተ እያለ ነበር። በመሆኑም ቄሮ ከቀላቸው ሰዎች መካከል  አማራ ያልሆኑ ኦሮሞዎች ቢኖሩ እንኳ  ቄሮ ሲቀላቸው ግን «አማራ ናችሁ» በማለት ነውና  «ኦሮሞ አይደላችሁም፤ አማራ ናችሁ» ተብለው የተቀሉት ሰማዕት ኦሮሞዎች አማሮች ሆነዋል።
የዐቢይ አሕመድ ማጭበርበር  በግፍ የተገደሉትን ሰዎች የነገድ ስብጥር በማጭበርበር ላይ ብቻ  አያበቃም። ጭፍጨፋውን ቄሮ የተባለው አሸባሪ ቡድን  መፈጸሙን ለመሸፈን ሲል  « እርስ በርስ ተቧድነው» የሚል ቃል   ተጠቅሟል። ይህ አገላለጽ  በመሪው ጃዋር መሐመድ  በተሰጠው ትዛዝ  መሰረት ትዕዛዝ ተቀባዩ ቄሮ በአማሮች ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ «እርስ በስርስ ተቧድነው» ወደሚል የአቻላቻ ጠብ ለማውረድና ግፉዓንንም ተጠያቂ ለማድረግ የታለመ ነው። ይህ  የዐቢይ ነውረኛነት መሪውን ጃዋርንና   መንጋውን ቄሮንም ነጻ ለማውጣት የተደረገ ሙከራ ቢሆንም ቅሉ የቄሮ የሰሞኑ  ጭፍጨፋ በአማሮች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ የመሆኑን እውነታ ግን ከቶ  ሊለውጠው አይችልም!
Filed in: Amharic