>

የሐረሩ ጉባኤ ጥያቄና በተግባር እየተሰጠ ያለ መልስ!!!  ( ዘመድኩን በቀለ)

የሐረሩ ጉባኤ ጥያቄና በተግባር እየተሰጠ ያለ መልስ!!!

  ዘመድኩን በቀለ
 
 ይሄ ወደፊት ሊሆን ላለው ምልክት ነው!!!
 

• ድል ለዲሞክራሲ  !! 

•••
ባለፈው ሳሞን በሐረሩ የደጅ ጥናት ጉባኤ ላይ ለዐቢይ አሕመድና ለለማ መገርሳ ሁለት ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎችን የጃዋር ወኪሎች ማቅረባቸው ይታወሳል?
፩ኛ፦ የቅማንት ጉዳይ ጉዳያችን ነው። የቅማንቶች ጥያቄ ለምን በአስቸኳይ አይመለስላቸውም? በማለት የቅማንት ጉዳይ ከዐማራው በላይ አስጨንቋቸው ስቅስቅ ብለው ሲጠይቁ ነበር የዋሉት።
፪ኛ፦ ባለአደራ የሚባለው ቡድን በአስቸኳይ ከፊንፊኔ ካልወጣ ትልቅ ችግር ይፈጠራል። ደም ሁላ እንፋሰሳለን። እናም ባለ አደራውን በቶሎ ከሸገር  አስወግዱልን። የሚል ጥያቄ ነበር ቄሮና ቀሬ ለእነ ታሬ አቅርበው የነበረው።
የጥያቄዎቹ ምላሽ ፦
ዐቢይ አሕመድ ሲመልስም እንዲህ አላቸው። አትቸኩሉ። አትጣደፉ። ሁሉን ነገር በጥበብ እያስኬድነው ነው። ሁሉም ነገር በአደባባይ አይወራም። እስቲ እንታገስ። የምለው ገባችሁ አይደል? ይላቸዋል።  ባይገባቸውም። ኤየን አሉ የሀገሬ ቆቱዎች። አዎን እንደማለት ነው።
ከዚያ ከስብሰባው መልስ ብአዴን ታዘዘች። ገረዷ ብአዴን ታዘዘች። ሰው የገደሉ። የሰለቡ። በወገናቸው ላይ የጅምላ እልቂት የፈጸሙ በሙሉ በነጻ እንዲለቀቁ ተደረጉ። ህወሓትና ኦነግ ሲፎክሩ ዋሉ። ሲሸልሉ፣ ሲያሽካኩ። አመሹ ዋሉም።
የሚቀረው የባለአደራው የመወገድ ጥያቄ:-
የባለአደራ ምክር ቤቱ አመራሮች በቢሮ ስብሰባ አድርገው ሲወጡ የተወሰኑ ሰዎች ከበባ አድርገው ጉዳት ሊያደርሱባቸው ሞከሩ።
ከበባ ካደረጉባቸው መካከል አንድ ሰው በፖሊስ አስይዘው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ይገኛሉ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የተያዘው ሰው ምርመራ እንዲደረግበት እየጠየቀ እንደሆነና ፖሊስ ግን ሰውየውን ሊለቀው እንደሆነ ታውቋል። የተያዘው ተጠርጣሪ ፖሊስ ሆኖ ተገኝቷል።
እነ እስክንድር ነጋ ሁኔታውን ለፖሊስ እያስረዱ ነው። ከበባ አድርገው ጉዳት ሊያደርሱብን ነበር ካሏቸው መካከል የተያዘው ላይ ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግ እየጠየቁ ነው። ሰዎቹ የተናበቡና ከፖሊስ እገዛ ያላቸው እንደሆኑ ለመጠርጠር በቂ ማሳያ አለን ብለዋል እነ እስክንድር። ከበባ ካደረጉት መካከል አንዱ ከመያዙ ውጭ ሌሎች መኪና ይዟቸው ተሰውሯል።
እናም  ዛሬ በኦሮሚያ ፖሊስ እየተመራ የተሰነዘረው ጥቃት ለጥቂት ሳይሳካ ቀርቷል። ዛሬ አልተሳካም ማለት ግን ነገ አይስካም ማለት እንዳይደለ ይታወቅ። አስክንድር አንድ ሰው ነው። በትንታም፣ በቴስታም፣ በሜንጫም ሊያልፍ ይችላል። አዲስ አበባ ግን ሳትደራጅ ተዘናግተህ ተቀምጠህ መጪው አውሬው እንዳይበላህ ተጠንቀቅ። ልብ አድርግ። [ በእስክንድርም፣ በእነ አቢይም መሃል የሲአይኤ ሚና ምን ያህል እንደሆነ የግሸኗ ማርያም ትወቅ ] የሆነው ሆኖ ግን።
በእስክንድር በኩል እንደ ከበቡሽ ከበቡኝ የለ። መንገድ ዝጉ የለ፣ ድረሱልኝ የለ። ጠብቁኝ የለ።

• ድል ለዲሞክራሲ !!

• ኃይል የእግዚአብሔር ነው  !!

• ወደ ሕግ ቦታ  !!

•••  አከተመ።
ሻሎም  !!   ሰላም  !!
ጥቅምት 23/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic