>

ባላደራ ምክር ቤት አባላት ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ከነበሩት መካከል የፖሊስ አባላት ይገኙበታል!!! (የባላደራው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ስንታየሁ  ቸኮል)

ባላደራ ምክር ቤት አባላት ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ከነበሩት መካከል የፖሊስ አባላት ይገኙበታል!!!
የባላደራው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ስንታየሁ  ቸኮል
(ኢትዮ 360 – ጥቅምት 22/2012)የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ባልደራስ አባላት ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ከነበሩት መካከል የፖሊስ አባላት እንደሚገኙበት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ገለጸ።
አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከኢትዮ 360 ጋር ባደረገው ቆይታ እንዳለው ጥቃቱ ሊሰነዘር የነበረው የባላደራው አባላት መደበኛ ስብሰባቸውን ጨርሰው ከቢሮ በመውጣት ላይ እያሉ ነው።
በቁጥር 10 የሚሆኑና አንድ ላይ የተሰባሰቡ ወጣቶች በኦሮምኛ ቋንቋ መረጃ ይለዋወጣሉ።
በዛው ቅጽበት ደግሞ ሙሉ የፖሊስ ልብስ የለበሰ ሰው ጭለማን ተገን አድርጎ የስልክ መልዕክት እየተለዋውጠ መመልከታቸውንም አቶ ስንታየሁ ይናገራል።
ይህው ቡድን መንገዳቸውን ሲጀምሩ ከኋላ እንደተከተላቸውም ይገልጻሉ።
ሁኔታው ያላማራቸው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፡የህግ ባለሙያው ሔኖክ አክሊሉ፡ሰናይት ታደገ፡ጌታቸው ተስፋዬና እራሱ ስንታየሁ ቸኮል የሚከተሏቸው ሰዎች ምን እንደሚፈልጉ እንደጠየቋቸው ይገልጻል።
ምን እንደፈለጉ እየጠየቅን ባለበት ሰአት ግን ከመሃከላቸው አንዱ እስር ቤት ከቦታ ቦታ ሲወስዱን ያጅቡን ከነበሩት ፖሊሶች መካከል አንዱ መሆኑን ስላወቅን አንተ ፖሊስ አይደለህም አብረሃቸው ምን ትሰራለህ የሚል ጥያቄ እንዳቀረቡለት ገልጿል።
እነሱ ያንን ጥያቄ ባቀረቡበት ሰአት ግን መልስ ከመስጠት ይልቅ ሁሉም በድንጋጤ ሩጫ መጀመራቸውን ነው የሚናገረው።
ከሯጮቹ መካከል አንዱን ይዘው ቢያስቀሩትም ሌሎቹ ግን ተዘጋጅቶ ይጠብቃቸው በነበረው ኮድ 35 የእርዳታ ሰጪ ድርጅት ተሽከርካሪ ተሳፍረው ማምለጣቸውን ገልጿል።
ጭለማ ውስጥ ቆሞ ከነሱ ጋ መረጃ ሲለዋወጥ የነበረውና ሙሉ የፖሊስ ልብስ የለበሰው ግለሰብም ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በር ላይ ተረኛ መስሎ መቀላቀሉን ተናግሯል።
በእጃችው የገባውን ግለሰብ ይዘው ወደ አካባቢው ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም ከእነዚሁ ሃይሎች ጋር በኦሮምኛ ቋንቋ መረጃ ሲለዋወጥ ያገኙት የእለቱ ተረኛ ኮማንደር ክሳችውን ሊሰማ ፍቃደኛ አልሆነም።
ምን አጥፍቶ ነው የሚታሰረው፡ወንጀል ሳይሰራ እንዴት ይጠየቃል በሚል ከኮማንደሩ ጋር ክርክር እንደገጠሙም ይናገራሉ።
አቶ ስንታየሁ እንደሚለው የሆነውንና በአጠቃላይ የተፈጠረው ነገር ለህይወታቸው አስጊ እንደነበር እንዲመዘገብላቸው ወንጀለኞችም እንዲጠየቁ ኮማንደሩን ረጅም ሰአት በማናገር ቆይተዋል።
በስተመጨረሻ ግን ይህንን ጉዳይ የሰሙ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፖሊስ ጣቢያውን መክበብ ሲጀምሩ ኮማንደሩ ምርመራውን እናካሂዳለን ውጤቱም ሲደርስ እናሳውቃችኋለን የሚል ምላሽ መስጠቱን ገልጿል።
የሚገርመው ይላል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል የያዝነው ወጣት በእለት ወንጀል ላይ ስሙ ሲመዘገብ ምክትል ሳጅን መሆኑንና ስሙም ምህረቱ ያደታ እንደሚባል ለማወቅ መቻላቸውን ከኢትዮ 360 ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።
Filed in: Amharic