>

ውህደታችን የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ወደ ላቀ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል! [መኢአድና - አንድነት ፓርቲ]

ውህደታችን የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ወደ ላቀ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል!

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ 2የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንደነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የውህደት ድርድራቸውን አጠናቀው ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት መግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወቃል፡፡ የሁለቱም ፓርቲዎች ከፍተኛ የአመራር ተቋሞች የጋራ የውህደት አመቻችና ጠቅላ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ በማቋቋም መመሪያ በመስጠት ስራቸውን ጀምረዋል፡፡ የጋራ ኮሚቴው የራሱ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ፀሓፊ በተጨማሪ የሰነድ ዝግጅት፣ የጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ ፣ የሕዝብ ግንኝነት፣ የመድረክ ዝግጅት እና መስተንግዶ፣ የህግና ፀጥታ እንዲሁም የፋይናንስ ንዑስ ኮሚቴዎችን በማቋቋም በሳምንት 3 ቀን ስብሰባ በማድረግ መሰረታዊ እና ዋናዋና ስራዎችን በማጠናቀቅ የጉባኤውን ቀን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

የፓርቲያችን ውህደት የኢትዮጵያ ህዝብ ለረዥም ግዚያት ሲጠይቅና ሲመኘው እንደ ነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ይህንኑ ጥያቄ ለመመለስና ገዢውን ፓርቲ የሚፎካከር ፓርቲ ለመመስረት ብቻ ሳይሆን ትግሉ በይዘትም በቅርፅም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያስችለን ቁመና ላይ ለመገኘት ተግተን በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡ የሁለቱም ፓርቲዎች ውህደት ለማደናቀፍ ከፍተኛ ሴራ እንደሚኖር በመገመትም ነቅተን በመጠበቅ ላይ ነን፡፡ በኛ በኩል ሥራዎቻችንን ብናጠናቅቅም ጉባኤያችንን ለማድረግ የገጠመን መሠረታዊ ችግር ወይም እንቅፋት የገንዘብ እጠረት ነው፡፡
አሁን ባላው ሁኔታ ከ1997 ዓም አገር አቀፍ ምርጫ በኂላ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለማዳከም ተጠንተው የተሰሩ ጉዳዮች ፓርቲዎችን በአዋጅ የፋይናናንስ አቅማቸውን ማዳከም ነው፡፡ ለዚህም የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ማቋቋማያ አዋጅ እና የመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አዋጅ መጥቀሱ በቂ ማሳያ ነው፡፡ አሁን ፓርቲዎቻችን ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ የባንክ አካውንት በመክፈት ለሕዝቡ ይፋ አድርገናል በዚህም አንፃር አፋጣኝ ድጋፍንም እንጠብቃለን፡፡

ዛሬ በአገራችን ኢትዮጵያ መጭውን የ2ዐዐ7 አገር አቀፍ ምርጫና ውህደታችን ታሳቢ ያደረገ እስር በፓርቲያችን ከፍተኛ አመራር አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ላይ የተካሄደውን እስር ከማውገዛችንም በላይ ለውህደታችን መሰናክል የሆነብን የገንዘብ እጥረት ጉዳይ ከሕዝቡ ጋር በመወጣት ውህደታችን ለመጨረሻ ጊዜ በተቀመጠለት የጊዜ ሠሌዳ እውን ይሆናል፡፡ ውህዱ ፓርቲ የአሸናፊነት መንፈስ ተላብሶ ከፍ ባለ የሞራል ልእልና ትግሉን ይመራል ለዚህም አንጠራጠርም ፡፡

SP 235 ቦሌ ቅርንጫፍ አቢሲኒያ ባንክ
A/C 47 ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ አቢሲኒያ ባንክ

ድል የሕዝብ ነው!
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ( አንድነት)
ሐምሌ 24 ቀን 2ዐዐ6 ዓም አዲስ አበባ
ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ 1ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

Filed in: Amharic