>
5:13 pm - Saturday April 19, 5236

የተንኮለኛው ከበደ ትርክት ተመልሶ መጣ!!!  (አላማየሁ መንገሻ የቀድሞዉ ጠ/ዐቃቤ ህግ )

የተንኮለኛው ከበደ ትርክት ተመልሶ መጣ!!!
አላማየሁ መንገሻ የቀድሞዉ ጠ/ዐቃቤ ህግ
ድሮ ልዑል  ራስ ስዩም የሚባል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበርኩበት ወቅት የአማርኛ መማሪያ መጽሀፍ ላይ የተንኮለኛው ከበደ እና የስንዝሮ ታሪክ በጣፈጠ አማርኛ የስላቅ ወግ በተከተለ ምንባብ በተረት መልክ ይቀርብልን ነበር ።
ከዚሁ ተረት አንዱ በአንድ አገር ውስጥ እጅግ በሞያው የተከበረ አንድ ሌባ ነበር አንድ ቀን በእኩለ ሌሉት  የስርቆት ስራውን ለማከናወን መንደር ውስጥ ወደሚኖር  ወደ አንድ ሰው ቤት ሄዶ ቤቱን እየሰረሰረ እያለ በድንጋይ የተሰራው ቤት ከግድግዳው ላይ አንድ ድንጋይ ተፈንቅሎ ሌባውን ፈንክቶ በአካሉ ላይ ጉዳት አደረሰበት ።ሌባው ህክምና እርዳታ ተደርጎለት ከጉዳቱ ሲያገግም ጉዳት ያደረሰበትን ቤት ባለቤት ፍርድ ቤት ዳኞች ዘንድ ከሰሰው ።የክሱ ይዘትም “ክቡራን ዳኞች በዚህ አገር አንድ ብርቅዬ ሌባ እኔ ብገኝ ይህ ሰው ቤቱን ባግባቡ ሳይስራ ቀርቶ ልሰርቅ ሄጄ  የቤቱ ግድግዳ ድንጋይ ተፈንቅሎ አናቴን ፈንክቶ ጉዳት አድርሶብኛል”ብሎ የክሱን ጭብጥ አስመዘገበ ።
ዳኞቹም” ተከሳሽ ምን መልስ  አለህ ለክሱ” ተብሎ ሲጠየቅ “ክቡር ዳኞች በደረሰው ጉዳት እጅግ አዝኛለሁ የቤቱ ባለቤት እኔ ልሁን እንጂ ጥፋተኛው ቤቱን የገነባው ስለሆነ ተጠርቶ ይጠየቅልኝ “ብሎ ምላሽ ሰጠ።
ፍርድ ቤቱም ቤቱን የሰራው ግንበኛ እንዲቀርብ አዘዘ።
ግንበኛውም በችሎት ቀርቦ ክሱ ተነቦለት “ለቀረበብህ ክስ ምን ትላለህ” ተብሎ ሲጠየቅ “የለም እኔ ሳልሆን ሲሚንቶውን አሸዋውን ያቦኩት ባልሞያዎች ናቸው “የሚል ምላሽ ሰጠ ።
ሲሚንቶ እና አሸዋውን ያቦኩት ባለሞያዎች ተጠርተው ሲጠየቁ “የችግሩ ምንጭ እኛ ሳንሆን አሸዋ እና ሲሚንቶውን ያቀረበልን ነው “የሚል ምላሽ ሰጡ ።
በመጨረሻ አሸዋ እና ሲሚንቶውን ያቀረበው ሰረተኛ ራሱን መከላከል ባለመቻሉ ችሎቱ ሌባው ላይ በደረሰበት የአካል ጉዳት “ጥፋተኛ ነህ ብሎ በሞት ቅጣት በስቅላት እንዲቀጣ ወሰነበት ።ቅጣቱ ሊፈጸም ወደመስቀያው ማማ ሲጠጋ ረጅም በመሆኑ የመስቀያው ማማ በመርዘሙ ስቅላቱን ማስፈጸም ባለመቻሉ አጭር የሆኑ የቅርብ  ዘመዱ ተፈልገው አጎቱ በመገኘታቸው የስቅላት ቅጣቱ በአጎቱ ላይ እንዲፈጸም ተደረገ።
ይህንን መሰል ፍርደ ገምድል ዳኝነት ሰሞኑን በኢተዮጵያ ውስጥ ተፈጽሞ በገሀድ አይተናል ።
ባለፈው ሳምንት 78(ይህ መንግስት በይፋ የጠቀሰው ቁጥር ነው ) ወገኖቻችን በተለያየ የአገራችን ክፍል በሀያኛው ክፍል ዘመን ፍጹም ይፈጸማል ተብሎ በማይታመን ዘግናኝ ሁኔታ በድንጋይ ተቀጥቅጠው ፣በተለያየ ስለት ታርደው፣ቤት ውስጥ በእሳት እንዲጋዩ ተደርጎ ተገድለዋል።በርካታ ዜጎች ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል ፣ለአመታት ያፈሩት ንብረት ወድሟል ፣ተዘርፏአል ።
ለዚህ ሁሉ ጥፋት  መንስኤው ዜግነቱ “አሜሪካዊ ነኝ ለኦሮሞ መብት መከበር ቆሜያለሁ  ”  የሚል ጁዋር መሀመድ የሚባል OMN የሚባል የቴሌቭዥን ሚዲያ ባለቤት “መንግስት የመደበልኝን ጥበቃ በሌሊት እንስቶ ህይወቴን ለአደጋ አጋልጧል “ብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ባሰራጨው ዜና መነሻ “ቄሮ “የሚባሉ ደጋፊዎቹ ናቸው ከላይ የዘረዘርኩትን ሰብአዊ ቀውስ ያስከተሉት።
የዚህ ለውጥ ሞተሮች ናቸው የሚባሉት እና አሁን በተረኝነት አገሪቱን እየመሩ ያሉት  ዶ/ር አብይ አህመድ ፣ለማ መገርሳ እና ሺመልስ አብዲሳ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ በሐረር ከተማ ከአባ ገዳዎች እና ከቢሮ ሀላፊዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ በጁዋር አህመድ በሚባል ግለሰብ ቅስቀሳ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደጎመን በግፍ ስለተጨፈጨፋት ወገኖቻችን ጉዳይ ከቁብም ሳይቆጥሩት  በሳቅ እየተፍነከነኩ “እንዴት ጁዋር ወንድማቸው እንደሆነ አብረውም እንደሚሰሩ  ፣የሚደረግለት ጥበቃ የማንሳት ሀሳብ እንደሌለ ፣ጥበቃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል”ሲናገሩ ሰማን::
ሁኔታቸውን ላየ የሚያስተዳድሩት ህዝብ በግፍ የተገደለባቸው አይመስልም።ለመሆኑ ከነሱ ዘመዶች አንዱ ቢገደል እንዲህ ይፍነከነኩ ነበር ።ለደረሰው ጉዳት የሰጡት ፍርደ ገምድል ዳኝነት ከላይ ከቀረበው ተረት ጋር አይመሳሰልም ?እነዚህ ናቸው ያሁኗን ኢትዮጵያ የሚመሯት።
ልዑል እግዛብሔር ምህረቱን ይስጠን!!
Filed in: Amharic