>
5:13 pm - Monday April 18, 9261

«ጃዋር መሐመድ ተቀያሪ መንግሥታችን ነው» ዐቢይ አሕመድ በሐረር ከተናገረው. . .(አቻምየለህ ታምሩ)

«ጃዋር መሐመድ ተቀያሪ መንግሥታችን ነው» ዐቢይ አሕመድ በሐረር ከተናገረው. . . 
አቻምየለህ ታምሩ
ለውጥ ተብዮውን ቧልት እንደግፋለን የሚሉን ሰዎች እርማቸውን የሚያወጡት መቼ ይሆን? ለዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ የሰጡትን ያልተገደበ ድጋፍ  የሚገድቡትና በቃ ለማለት ቀይ መስመራቸው የቱ ይሆን?  እነዚህ «የለውጡ ደጋፊዎች»   ዲሲ ከሰሞኑ ባካሄዱት ሰፍል አሜሪካ ዐቢይ አሕመድን እንድትደግፍ በመጠየቅ ዐቢይ አሕመድን ደግሞ  ጃዋር መሐመድን ለፍርድ እንዲያቀርብላቸው  ሲጠይቁት ሰምተናቸው ነበር።
የሚያደርገውን የሚያውቀው  ዐቢይ  አሕመድ ግን በትናንትናው እለት  ሐረር ሄዶ በኦሮምኛ ባደረገው ንግግር  ከሰባ በላይ ንጹሐን ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን በግፍና ጭካኔ እንዲታደሩ ያደረገውን ጃዋር መሐመድን በማሞካሸት «ጃዋር መሐመድ ተቀያሪ መንግሥት ነው» በማለት  «ለፍርድ አቅርብልን» እያሉ ሲወተውቱት  የሰነበቱ ደጋፊዎችን ኩም አድርጓቸዋል። ሳስበው ቀይ መስመር የሌላቸውና ያልተገደበ ድጋይ የሚሰጡት «የለውጡ ደጋፊዎች» ይህ የዐቢይ አሕመድ ንግግር ሲሰሙ «ንግግሩ ዐቢይ አሕመድን አይወክልም» የሚሉ ይመስለኛል።
ዐቢይ አሕመድ ጃዋር መሐመድን «ተቀያሪ መንግሥታችን ነው» ሲል እውቅና የሰጠበት  የሐረሩ ንግግር  ጃዋር መሐመድ «በዚህ አገር ሁለት መንግሥት አለ፤ የቄሮ መንግሥትና ዐቢይ የሚመራው መንግሥት» በማለት የተናገረውን  ሕገ ወጥነት endorse የሚያደርግ ነው። ጃዋር መሐመድ «ሁለት መንግሥት አለ» ያለውን ወንጅላችሁ  የጃዋርን ሁለተኛ መንግሥትነት እውቅና የሰጠውን ዐቢይ አሕመድን ግን የምትደግፉ ሰዎች   ልታፍሩ ይገባል።
በእውነቱ ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ መሪ ቢሆን ኖሮ ሐረር ሄዶ ማናገር የነበረበት ኦሮሞን ሳይሆን « አገራችሁ አይደለም ውጡ» ተብለው የተጨፈጨፉትን ኦሮሞ ያልሆኑ የቄሮ ሜንጫ ሰለባ የሆኑ ግፉዓን ኢትዮጵያውያንን  ነበር። ሆኖም ግን ዐቢይ አሕመድ  «አገራችሁ አይደለም» ተብለው  የተጨፈጨፉትን ቢያናግር የኦሮሞ ብሔርተኞችን አንድነት  ይጎዳብኛል ብሎ ስላሰበ ያንን አላደረገውም። የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ  አንድነት የሚጸናው በእሴት ላይ በተመሰረተ እሳቤ ሳይሆን ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን በተለይም በአማራ ላይ በሚይዙት የጋራ አቋም ነው። ዐቢይ አሕመድ ሐረር ሄዶ የተገደሉትን ኦሮሞ ያልሆኑ ግፉዓንን ሳይሆን  የገደሏቸውን ቄሮዎችን ሰብስቦ የጃዋርን ተለዋጭ መንግሥትነት ያወጀው የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ አንድነት የሚጸናው ያን ሲያደርግ ብቻ እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው።
በመንግሥትነት የተሰየመው የዐቢይ የአፓርታይድ አገዛዝን  ጨምሮ የትኛውም የኦሮሞ ብሔርተኛ ድርጅት ወይም እንደ ቄሮ አይነት ሕቡዕ አደረጃጀቶች ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሱት የትኛውም አይነት ግፍና ጭካኔ እንዳያወግዙ በኦሮሞ ብሔርተኞች ዘንድ ስምምነት አለ። ሁሉም የኦሮሞ ብሔርተኞች  የኦሮሞ ብሔርተኞች እንቅስቃሴ ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሱትን ግፍና ጭካኔ ቢያወግዙ የኦሮሞ ብሔርተኞች አንድነት ችግር ላይ ይወድቃል ብለው ያስባሉ።  ባጭሩ የኦሮሞ ብሔርተኞች የፖለቲካ አንድነት የተመሰረተው  በሰዋዊ እሴቶች ላይ ሳይሆን ኦሮሞ ባልሆኑ  ኢትዮጵያውያን ላይ በሚፈጽሙት  ኢሰብኣዊ ጭካኔ ላይ ነው። ይህ የኦሮሞ ብሔርተኞች የአስተሳሰብ መሰረት የሚቀዳው  ከገዳ ሥርዓት  የኦሮሞ ገዢ መደብ እሳቤ ነው።
የኦሮሞ ገዢ መደብ   ኦሮሞ ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን የነበረው እሳቤ «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል ነበር። ይህ ማለት  የኦሮሞ  ገዢ መደብ  ኦሮሞ ስላልሆኑ ሰዎች ያራምደው የነበረው ፍልስፍና ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ» ማለት ነው። ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የኦሮሞ ብሔርተኞች ሁሉ ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን  ላይ ቄሮዎች የሚፈጽሙት ጭፍጨፋ  እንደሰው  የማይሰማቸው «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል  እምነት የነበራቸው የኦሮሞ ገዢ መደብ ሥርዓት አራማጆች በመሆናቸው ነው።
Filed in: Amharic