>

የብሄር አቃፊ የለውም! አትቀፈኝ!!! (ሙክታሮቪች) 

የብሄር አቃፊ የለውም! አትቀፈኝ!!!
ሙክታሮቪች
ማንም ማንንም አያቅፍም፤ ሁሉም በኢትዮጵያ ምድር እኩል የመኖር መብት አለው፡፡ መኖሪያ ቤትህና አጥር ግቢ ውጭ የአንተ አይደለም፡፡ የምን አቃፊ ነን ፉከራ ነው!!!
እየተንጣጣ ነው ሰውዬው ትክት ያለው ነገር አለ።
በአዳራሽ ውስጥ ካሉት አንዱ የሚከተለውን አስተያየት እየሰጠ እያለ ብድግ ብሎ አጠገቡ ያለውን ማይክ አንስቶ ነው የተንጣጣው።
ሰውዬው ምን እያሉ ነበር:—
“የኛ ብሄር አቃፊ ነው፣ ከጥንት አባቶቻችን የተረከብነው የአባቶቻችን እሴት ነው አቃፊነት” እያሉ በነበረበት ነው ሰውዬው የሚከተለውን አስተያየት በከረረ ድምፀት እየተንጣጣ የተናገረው:—
“ማንም ማንንም አያቅፍም፤ ሁሉም በኢትዮጵያ ምድር እኩል የመኖር መብት አለው፡፡ መኖሪያ ቤትህና አጥር ግቢ ውጭ የአንተ አይደለም፡፡ የምን አቃፊ ነን ፉከራ ነው!”
“እና ምን እንበል፣ ማቀፍ ነውር አይደልም መቼም!”
“የፈለገ በማህበር ይታቀፍ፣ የፈለገ በሚስቱ ይታቀፍ። በፖለቲካ ግን ተቃቃፊ ነን እንጂ ማንም አቃፊ ማንም ታቃፊ አይደለም ፣ እኔም እቅፈሃለው ፣ አንተም ታቅፈኛለህ። እርስበርስ ተቃቃፊ ነን። ብቻህን እንደበረደው ሰው ና ልቀፍ አትበለኝ። መብቴን አክብርልኝ። መብትህ አከብርልሃለው። የኔ መብት ላንተ ግዴታ ነው፣ ያንተ መብት እኔ ላይ ግዴታ ነው፣ በሚል መርህ እንተቃቀፍ። ብሄሬ አቃፊ ነው ስትለኝ አንድ ቀን ና ልቀፍህ ብሎ ጨምቆ አፍኖ እንደሚገለኝ እገምታለሁ። አትቀፈኝ!!” 
Filed in: Amharic