>

ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ 7 ዓመት ተፈረደበት!!! (ግዮን መጽሄት)

ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ 7 ዓመት ተፈረደበት!!!
ግዮን መጽሄት
 
የዕንቁ መጽሔት አሳታሚ አቶ አለማየሁ ማኅተመወርቅ በ25 አመት እስራት እንዲቀጣም ፍርድ ቤቱ ወስኗል!!!
ከአምስት ዓመታት በፊት በዕንቁ መጽሔት በተመሠረተ ክስ መዝገቡ ሲንከባለል ቆይቶ ባሳለፍነው ሳምንት የጥፋተኝነት ውሣኔ የተላለፈበት የግዮን መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ዛሬ ማክሰኞ 18/2012 ዓ.ም  የልደታ ፍ/ቤት ስምንተኛ ወንጀል በዋለው ችሎት “ጥፋተኛ” ባለበት ክስ የ7 ዓመት እስርና የ7000 ብር ቅጣት ተወስኖበታል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ መዝገብ አንደኛ ተከሳሽ የነበረው የዕንቁ መጽሔት አሳታሚ አቶ አለማየሁ ማኅተመወርቅ በ25 አመት እስራት እንዲቀጣም ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡ ጋዜጠኛው በሀገሪቱ “ለውጥ መጣ” ከተባለበት ጊዜ በኋላ ከነፃው ፕሬስ ጋር በተያያዘ በቀደመው የህወሓት/ኢህአዴግ የክስ መዝገብ ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት የመጀመሪያው ሠው ነው፡፡
Filed in: Amharic