>

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጭምር መነጋገሪያ ሆኗል (ታምሩ ገዳ)

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጭምር መነጋገሪያ ሆኗል
ታምሩ ገዳ
ጃዋር እና ሕወሓት ያቀነባበሩት ድራማ ነው በሚባለው “ጠባቂዎች ሊነሱ ነው” እና አስከትሎ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ማንነት እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ቢያንስ ከ67 በላይ ንጹሃን ተገድለዋል።ይህ ግድያ የተፈጸመው ጥሪ ሲጠባበቁ በነበሩ ጽንፈኛ ወጣቶች እና በኦሮሚያ ክልል በልዩ ልዩ ደረጃ ባሉ ከጃዋር ጋር በወገኑ ባለስልጣናት እና የክልሉ ፖሊስ በጋራ የፈጸሙት ነው። ፖሊስ ጽንፈኞችን ለህግ ከማቅረብ እና ቢያንስ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ሀላፊነቱን መወጣት ሲገባው ለነውጠኞቹ ሽፋን እና ከለላ ከመስጠት አልፎ ራሱ በህገ ወጥ ግድያ ተሳትፉዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱ በዚያ መሰል አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆና ባሉበት ጭምር ዝምታ መምረጣቸው ብቻ ሳይሆን ከመጡም በሁዋላ ስለ ሽብር ድርጊቱ አለመናገራቸው የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ጭምር ስቦዋል።
ዛሬም ድረስ ግልጽ ባልሆነው የሰኔ 15/2011 የባህር ዳር እና የአዲስ አበባ ግድያ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣የኦሮሚያ ክልል ም/ፕ/ት ሽመልስ አብዲሳ፣የአዲስ አበባ ም/ል ከንቲባ ታከለ ኡማ ፈጥነው መግለጫ በመስጠት ሐዘን ገላጮች፣ለሞቱ ደግሞ ከእነሱ በላይ አዛኝ እንደሌለ ለማሳየት ሞክረዋል ።ዛሬስ ?
ወታደራዊ ልብስ ለብሰው በወቅቱ በሌሊት መግለጫ የሰጡት አብይ አህመድ(ዶ/ር) የሰሞኑ ዝምታ ብቻ ሳይሆን ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ ላይ ያላቸውን ግልጽ አቁዋም ሕዝቡ ማወቅ ይፈልጋል።ተድበስብሶ ሌላ ሞት የሚጠብቅ የለም።
ሕዝብ ፍትሕን ይሻል!
Filed in: Amharic