>

ጃዋር ብቻ ለምን ይጠይቅ ይባላል!? (ታምሩ ገዳ)

ጃዋር ብቻ ለምን ይጠይቅ ይባላል!?
ታምሩ ገዳ
በአገር ቤት ጃዋር መሐመድ ለደጋፊዎቹ መንግሥት ጥበቃዎቼን ሊያነሳ ነው ብሎ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በተነሳ ግጭት በትንሹ ከ53 በላይ ንጹሃን ተገድለዋል። መንግሥት ከሳሳተ ስጋት ተነስቶ የተደረገ ጥሪ ነው ብሉዋል።
የድርጊቱ ፈጻሚ መንግስት ነው ብሎ ጃዋርም ሆነ የእሱ ተከታዮች የሚያምኑት የጨለማ ድራማ የተደረገው ጥቃቱ መንግስት ላይ ብቻ ያነጣጠረ ለምን አልሆነም? ብሄር እና ሀይማኖት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ይፕተፈጸመ ሲሆን አንዳንድ ቦታ አይ ሲስ በሊቢያ በክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ የፈጸመው ድርጊት መፈጸሙ፣ቤተ ክርስቲያናት ዳግም የጥቃት ሰለባ ሆነዋል።
ይህ ድርጊት የሚያሳየው ተቃውሞው በመንግስት ላይ ያነጣጠረ አልነበረም።ይልቅ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ ሐረር እና ድሬዳዋ ብሎም በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች ለዓላማችን እንቅፋት ይሆናል ብለው ጽንፈኞች በጉዋሮ ሞት የፈረዱበት ወገን አለ። ስለዚህ ጃዋር ፊሽካ ሲነፋ መንግስት ላይ በቀጥታ ያነጣጠረ ብቻ እንዳልሆነ በሚያሳይ መልኩ የጥቃት ሰለባ ተደርገው የተነጣጠሩት ንጹሃን በብሄራቸው እና በሀይማኖታቸው ጭምር ተለይተው የተፈረጁ ናቸው ።
በጃዋር ጥሪ የተቀሰቀሱ ወጣቶችን ሙሉ ለሙሉ ድጋፍ ከመስጠት ጀምሮ በተቀናጀ መንገድ ታላቅ የተቀደሰ ተግባር እንደፈጸሙ ሰንጋ ጥሎ እስከ ማብላት የተደረሰበት አለሁ ባይነት በኦሮሚያ ባለስልጣናት የተቀነባበረ ጭምር ነው።የኦሮሚያ ፖሊስ ለጽንፈኞቹ ሽፋን ከመስጠት ጀምሮ ከአቅም በላይ ሀይል ለመጠቀም የዘመቱባቸውን ዱለኞች ለመመከት ለመከላከል የሞከሩት ላይ ጥይት እየተኮሰ ገድሏል።ይህ ግድያ እና አጠቃላይ የአመጽ ጥሪውን የፈጸሙ ወገኖች ለህግ ሊቀርቡ ይገባል።
የጥበቃ መነሳት እና አለመነሳት ከሆነ ለወጣቶቹ ጥሪ ማቅረብ ያስፈለገው እግረ መንገድ ማንም ብሄር ሆነ ሀይማኖት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዳይሆን አስቀድሞ መግለጽ ይገባል።ብዙዎቹ የኦሮሚያ ባለስልጣናት የሰኔ 15/2011 ዛሬም ድረስ ግልጽ ያልሆነ ግድያን ለማውገዝ በብርሃን ፍጥረት ለአማራ ሕዝብ እና መሪዎች ተቆርቁዋሪ መስለው አስቸኩዋይ መግለጫ ሲሰጡ አሁን ግን ጃዋር በጠራው አመጽ ንጹሃን እንመራዋለን በሚሉት ክልል በማንነት ጭምር በማያውቁት ጉዳይ የጥቃት ዒላማ ሲሆኑ አደባባይ ወጥተው ለማስቆም አልሞከሩም።የሚፈልጉትን ግዳይ ካገኙ በሁዋላ የሰራችሁትን ሰርታችሁዋል በቃ የተባለው መግለጫም ከተጠያቂነት አያድንም።
የዚህ ሁሉ ሽብር ማጠንጠኛው መሰረታዊ ችግር ግልጽ  ነው። የአዲስ አበባ፣የድሬዳዋ እና የሐረር ጉዳይ ዋነኛው ሲሆን ሁለተኛው ጉዳይ የኦዴፓ ባለስልጣናት የውስጥ የስልጣን  ሽኩቻ እና በአብይ እና በጀዋር ጀርባ የተቧደነው ቡድን ግብግብ ነው።
የአዲስ አበባ ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ከተማ መሆኑዋን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን ሰሞኑን ያስነሱት አመጽ አይነት አስነስተው ይቃወመናል ብለው የሚያስቡት ሀይል ላይ የዘር ማጥፋት ጭምር እንዳቀዱ ከዚህ ቀደም በልዩ ልዩ መንገድ የሰጡዋቸውን መግለጫዎች፣ፉከራዎች፣ምክንያት እየፈለጉ ሊያጠቁት የፈለጉት ማንን እንደሆነ ሲጋልጹ ቆይተዋል። ይህን ዓላማቸውን ለማሳካት ትላንት ሲያወርዳቸው የነበረው ህወሓት ጋር ጭምር እስከ ማበር ደርሰዋል።
እነ ጃዋር እና ሕወሓት ለለውጥ አብሮ በተናሳው፣አብሮ ሞቶ ለስልጣን ላበቃቸው ህዝብ  ጭምር ባጋራ ጉድጉዋድ እስከ መቆፈር ደርሰዋል።ሰሞኑን የጃዋር ተከታዮች ንጹሃንን ሲጨፈጭፉ የህወሃት ሰዎች ከበሮ መምታት ተልዕኮው የጋራ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።ይህን የሚደግፉ መረጃዎች ወጥተዋል ።
ይህ ሀይል ህጋዊ አመራር መስሎ ግማሽ ኦዴፓ ግማሽ  ቄሮ ሆኖ አሸባሪ እየሆነ ራሱን እንደ እስስት እየለዋወጠ አንዴ ጨፍጭፍፉ፣ቆይቶ ደግሞ በቃ የሚለው ጃዋር ያደራጀው ወይ በሱ ጥሪ ብቻ የወጣ ሳይሆን ራሱ ጃዋር ሰሞኑን በሰጠው ቃለ ምልልስ እንደገለጸው ከአብይ ጋር ሲሆን መደመር የሚል ለጃዋር ደውሎ አንደግፈውም ይላል።ስለዚህ የሰሞኑን ሽብር ጃዋር እና ይሄ ቡድን በጋራ ያቀነባበሩት እና የፈጸሙት በመሆኑ በወንጀሉ ነጥሎ ጃዋርን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ በቂ አይደለም።
በዚህ አጋጣሚ ይህ ቡድን የጠራውን ብሄር እና ሀይማኖት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዳይሰፋ ትልቅ አስተዋጽዎ በተለያዩ ከተሞች ያደረጉ ወገኖች ፣መንግስት ውስጥ ያሉ ጥቂት ማጅራት መቺዎች ከጃዋር ቡድን ጋር አብረው አስተባባሪ ፣ገዳይ እና አስገዳይ መሆናቸውን በማየት ሕዝብ ራሱን አስተባብሮ ራሱን የመከላከል የተፈጥሮ ግዴታውን ተግባራዊ ለማድረግ ሞክሯል። ይህም ጥረት ሊደርስ የሚችለውን ጥፋት ከዚህ እንዳይከፋ ለመቀነስ የራሱን አስተዋጽዎ በማድረጉ በየትኛውም ስፍራ ያለ ወገን ሊኮራባት የሚገባ ተግባር ነው።
ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ስንጠይቅ ሁሉንም እንጂ አንድ ጃዋርን ብቻ ነጥሎ ተጠያቂ ለማድረግ መሞከር ትርጉም የለውም። የድርጊቱ አስተባባሪዎች በሙሉ ለፍርድ ይቅረቡ ማለት እንወዳለን! ክብር በግፍ ለተገደሉ ሰማዕታት ይሁን!
Filed in: Amharic