>

ይሄ መንግሥታዊ የዘር ማጥራት ነው፤ ኦርቶዶክስና አማራ በኢትዮጵያ ምድር እንዳይኖር ተፈርዶበታል!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ይሄ መንግሥታዊ የዘር ማጥራት ነው፤ ኦርቶዶክስና አማራ በኢትዮጵያ ምድር እንዳይኖር ተፈርዶበታል!!!
ዘመድኩን በቀለ
….መሃል አስፋልት ላይ አረጋዊውን እንደ እባብ ቀጥቅጠው ገደሉ። የእሳቸውን መሞት ካረጋገጡ በኋላ ቀጥሎ ከአዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የተመረቀውን ልጃቸውን አቢቲ ታምራትን እየጎተቱ አምጥተው የአባትየውን አስከሬን ካሳዩ በኋላ እሱንም በተመሳሳይ መንገድ እዚያው ቀጥቅጠው ገደሉት!!!
                 
••••
በምዕራብ አሩሲ የኮፈሌ ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ አባል ናቸው። እዚያው ተወልደው ያደጉም ናቸው። አረጋዊ አቶ ተምራት ፀጋዬ። አቶ ታምራት ፀጋዬ ዐማራና ኦርቶዶክስ ከመሆናቸው በቀር ከአንድም ሰው ጋር ጠብ የሌላቸው ለፍቶ አዳሪ ነበሩ። የእነ ዐቢይ አህመድ መንግሥት ከኦሮሚያ ኦርቶዶክሶችንና ዐማሮችን፣ ጉራጌና ወላይታዎችን፣ ለማጽዳት ጃዋርንና ሠራዊቱን ይጠቀማል። በዚሁ መሠረት የዘር ማጽዳቱ እጣ አቶ ታምራት ቤተሰብ ላይ ወደቀ። ክፉ ቀን።
•••
ገዳዮቹ አክራሪው የኦሮሞ ወሃቢያ መንጋ በመጀመሪያ አቶ ታምራትን ከቤታቸው አውጥተው መሃል አስፋልት ላይ አረጋዊውን እንደ እባብ ቀጥቅጠው ገደሉ። የእሳቸውን መሞት ካረጋገጡ በኋላ ቀጥሎ አባትየው አስከሬን አጠገብ በቅርቡ ከአዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የተመረቀውን ልጃቸውን አቢቲ ታምራትን እየጎተቱ አምጥተው የአባትየውን አስከሬን ካሳዩ በኋላ እሱንም በተመሳሳይ መንገድ እዚያው ቀጥቅጠው ገደሉት። አባትና ልጅን ከገደሉ በኋላ ቀጥለው እንደ ልጃቸው ያሳደጉትን የሱቃቸውን ሠራተኛ በሁለቱ አስከሬን አጠገብ አርደው ገደሉ። መኪናዎቻቸውን፣ ንብረታቸውን በእሳት አቃጠሉ።
•••
በመጨረሻም የሟቹን አረጋዊና የልጆቻቸው አስከሬን ላይ ገመድ በአስከሬኑ አንገት ላይ አስረው ከተማው ላይ እየጎተቱ ሲጨፍሩ ዋሉ።
 ዐማራና ነፍጠኛን ሰባብረው ጣሉ ማለት ነው። የኦሮሞው ፕሬዘዳንት የአቶ ሽመልስ አብዲሳን ትእዛዝ ፈጸሙ ማለት ነው። ይሄ ሁሉ ሲሆን የኦሮሚያ ፖሊስና መከላከያ ቆሞ ከማየት ውጪ ምንም አያደርግም ነበር። ይሄ ድርጊት እጅግ በተጠና መንገድ በተጠና መልኩ በከተማዋ የሚገኙ የክርስቲያኖቹ ንብረትና ቤት በሙሉ በእሳት እንዲወድም ተደረገ።
•••
ይሄ ቀደም ብለው የተዘጋጁበት የዘር ማጥፋት ድርጊት ነው። የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ይገመታል። ኦርቶዶክስ ኦሮሚያን ይልቀቅ ነው ፉከራቸው። ለማ መገርሳ ጴንጤ ነው። በዚህ ላይ የመከላከያ ሠራዊቱ አዛዥ ነው። የሚሞተው ዐማራ፣ ወላይታ፣ ትግሬና ጉራጌ ስለሆነ ፈጽሞ አያገባውም። ዐቢይ አህመድ ጴንጤም እስላምም ነው። በዚህ ላይ የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች አዛዥም ነው። የሚሞተው ኦርቶዶክሱ ስለሆነ አያገባውም።
•••
እንዲህም ሆኖ ጃዋር በሕግ አይጠየቅም። ጭራሽ በእሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎችን ዜና እነ ቢቢሲ ሲሠሩለት እንደ ጀብዱ ሼር ያደርጋል። መንግሥቱም ፀረ ኦርቶዶክስ ነው። ኦርቶዶክስን ለማጥፋት በድብቅ በምክርቤት ያጸደቁት ሁላ ነው የሚመስለው። እጅግ የተጠና ነገር ነው እየተካሄደ ያለው። ይሄ የሚቆም አይደለም። አንድም እስላም ድርጊቱን ሲያወግዝ አታይም። ከጥቂቶች በቀር በአብዛኛው ጮቤ ሲረግጥ ነው የምታየው።
•••★ ይሄን አሳቃቂ ድርጊት የፈጸሙት ኢትዮጵያውያን ናቸው ለማለት ይቸግረኛል። ጣልያንም እንዲህ አላደረገ። የመንግሥት እጅ አለበት። የተጠና ድርጊት ነው። አዳሜ እርምህን አውጣ። ይኸው ነው። የሚያሳዝነው የትግራይ ልጆችም እየሞቱ የትግሬ አክቲቪስቶች እየተፈጠረ ባለው ነገር ደስተኛ መሆናቸው ነው። እነ ናሁሰናይ፣ እነ አሉላ ሰሎሞን ቄሮን ግፋ በለው ማለታቸውም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው። ነገን ደግሞ እናያለን።
••• የሞቱትን ነፍሳቸውን ይማርልን። የሰማዕታት በረከት ያድርግላቸው። አሜን።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ጥቅምት 14/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic