>
5:13 pm - Friday April 19, 2667

ኦቦ ጃዋር "ጥበቃዎቼ በሌሊት እንዲነሱ ታዘዘ! ተከብቤያለሁ " ማለቱን ተከትሎ የተነሳው ሁከት!!! (ታምሩ ገዳ)

ኦቦ ጃዋር “ጥበቃዎቼ በሌሊት እንዲነሱ ታዘዘ! ተከብቤያለሁ ” ማለቱን ተከትሎ የተነሳው ሁከት!!!
 
ታምሩ ገዳ
መንግሥት ያቆማቸው የጃዋር ጠባቂዎች እንዲነሱ ተወሰነ!!!
ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ በፓርላማ ማክሰኞ ጥቅምት 11/2012 ተገኝተው የዓመቱን የአስፈጻሚውን አካል እቅድ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ማብራሪያ ላይ የውጭ ዜግነት እያላቸው ሚዲያ ከፍተው የሚንቀሳቀሱ ምህዳሩን ለማስፋት በሚል በትዕግስት ጉዳዩን ማየት የሚቻለው ለአገር አስጊ እስካልሆነ ድረስ ብቻ መሆኑን መግለጻቸውን ተከትሎ ጃዋር መሐመድ ፈጥኖ ምላሽ ከሰጠ በሁዋላ መንግስት ያቆመለት ጠባቂዎቹ እንዲነሱ መደረጋቸውን የመረጃ ምንጮች ይገልጻሉ።ጃዋር ጠባቂዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ የተጠየቀው ከመንግስት ወገን መሆኑን የአንድ  ጠባቂውን እና ትዕዛዝ ያስተላለፉ ኮሚሽነር የስልክ ልውውጥ ይፋ አድርጎ አሰምቷል።ጠባቂዎቹ ትዕዛዙን ባለመቀበል ከጃዋር ጋር ናቸው ተብሉዌ።እሱም ይህን አረጋግጡዋል።
ትዕዛዙ ከመንግስት መጥቱዋል ወይም የጃዋርን ምላሽ ተከትሎ በጸጥታ ውስጥ የሚሰሩ ባለስልጣናት ያስተላለፉት ትዕዛዝ ነው የሚለውን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልተቻለም።
ጃዋር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያ በቀጥታ ለራሱ ወስዶ በሰጠው እኛም አውቀናል ጉድጉዋድ ምሰናል አለች አይጥ ከዚህ በሁዋላ ኑራችንም ሞታችንም ኦሮሚያ ውስጥ ነው የሚል መስጠቱ አነጋጋሪ ሆኖ ውሉዋል።በዚህ  ምላሽ ሳቢያ አላስፈላጊ ግጭት እንዳይነሳ በሚል አንዳንድ ወገኖች ሰከን በል የሚል ምክር በቀጥታ ቀርበው ለጃዋር እንደ ሰጡት እና ምክራቸውን እንዳልተቀበለ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይገልጻሉ።
የአባገዳ ልጆች ዛሬም አንድ ላይ ናቸው ጃዋርም ሆነ ጠቅላይ ሚ/ር አብይ ለአንድ ዓላማ ቆመዋል ብለው የሚያምኑ ወገኖች በቅርቡ ጃዋር ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርቦ በሰጠው ምላሽ “አሁን ያለነው የኦሮሞ አመራሮች ሶስት ነን አብይ አለ ለማ አለ እኔ አለሁ” እኛ አንድ ነን ሲል መግለጹን በማስታወስ ምንም የፖለቲካ ልዩነት የለም ብለው የሚገልጹም አሉ።መከራከሪያቸው ነገ በአዳባባይ አንድ ላይ ታዩዋቸዋላችሁ የሚል ጭምር ሲሆን የጃዋርን ምላሽ አግባብ ነው ብለው ያልተቀበሉም አሉ።
ሁኔታውን እንደ ፍጥጫ የቆጠሩት ግጭት እንዳይነሳ ስጋታቸውን በልዩ ልዩ መንገድ በመግለጽ የፖለቲካ ልሂቃኑም ሆኑ ተከታዮች ከብሽሽቅ እና ግጭት ቀስቃሽ መንገድ እንዲወጡ በማበራዊ ሚዲያ የጠየቁ ወገኖችም ነበሩ።
ጠቅላይ ሚ/ሩ በፓርላማ ያደረጉት ንግግር ውስጥ ጃዋር እኔን ይመለከታል ያለው  የሚከተለው ነው።
<<በተለይ የዉጭ ሀገር ዜግነት ያለችሁ እና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላችሁ እዚህ ሚዲያ ከፍታችሁ የምትንቀሳቀሱ ተጠንቀቁ። ነገ ችግር ቢፈጠር እናንተ ትሄዳላችሁ እኛ ግን መሄጃ የለንም፣ የምንታገሳችሁ ምህዳሩን ለማስፋት ብለን ነዉ። በሀገር ሕልዉና ከመጣችሁ ግን ኦሮሚኛም ይሁን አማርኛ ብትናገሩ እርምጃ እንደምንወስድ ማወቅ አለባችሁ።>> ጠሚ ዓቢይ አህመድ
መንግሥት በግልጽ ይናገር የፖለቲካ አሻጥር እና ድራማ ለአገር አይጠቅምም!!
የዛሬው የፓርላማን ውሎ ተከትሎ ብዙ ጉዳዮች ተነስተዋል።ከዚህ ሁሉ በላይ ገኖ እና ጎልቶ የወጣው ደግሞ የውጭ ዜግነት ያላቸው የሚዲያ ባለቤቶችን ያስጠነቀቁበት አግባብ ነው። ይህን ጃዋር እኔን ይመለከታል ብሎ ምላሽ ሰጥቱዋል። ማምሻውን የጥበቃ ሰራተኞች እንዲነሱ ተጠይቀዋል ብሉዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሩሲያ መድህን ተገን አድርጎ ጃዋርን ማንገስ የፈለገ ሀይል ጋር በቅንጅት የሚሰራ የፖለቲካ ድራማ ነው የሚሉ ድምጾች ከአገር ቤት እየተሰሙ ነው።
አሳሳቢው በዚህ ድራማ ሳቢያ ሁኔታውን ግራ ቀኝ ብሎ ሳያጣራ ጃዋር ላይ አደጋ እንዳለ አድርጎ ጦር ግጭት እንዲነሳ እየቀሰቀሰ ያለ ሀይል አለ።ይህ የሰው ሕይወት የሚቀጥፍ በቅርብ ይሁን በሩቅ የትኛውንም ሕዝብ የማይጠቅም የተወሰነ የፖለቲካ ጉልበት እና ስልጣን ለማግኘት ተብሎ የሚደረግ የፖለቲካ ሴራ ከሆነ በእርግጥም ካለፋው የኢትዮጵያ ፓለቲካ ዛሬም ትምህርት አልተገኘም ማለት ነው።ከግጭት ጥፋት እና ውድነት፣ብልጭ ያለው ከሚጠፋበት የጨለማ ስርዓት መውለድ ካልሆነ የተሻለ እና ፍትሃዊ አስተዳደር ማምጣት አይቻልም። መጠንቀቅ ይገባል።
መንግሥት በዚህ ምሽት የሚባለው እና ዜጎችን ለእርስ በእርስ ግጭት ለመዳረግ እየቀሰቀስ ያለው ሀይል የሚያቀርባቸውን ክሶች ቀርቦ የማብራራት ሆነ ምላሽ መስጠት አለበት። የፖለቲካ አሻጥር እና ግጭትን ዓላማ አድርጎ ግጭት ለመቀስቀስ የሚሞክሩ ወገኖች የትም ቢሆን  በሀላፊነት የሚጠየቁበት መሆኑን መገንዘብ ይገባል።የዘር ግጭት ቀስቅሶ የትም ቢኖሩ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም።ሁኔታውን በእርጋታ ማየት ይገባል።
የእነ ጃዋር በሰዓታት ልዩነት በተከታታይብእየቀረበ ያለ ጥሪ ጉዳት ከማድረሱ እና በሁዋላ ጣት ከመጠቋቆም በፊት በብርሃን መነጋገር ይገባል ።ወጣቶችን ከፊት አስቀድመው ግጭት ማስነሳት የሚፈልጉ ወገኖችም ይህ አካሄድ የታየውን  እና በችግር እየተወለካከፈ ያለውን የለውጥ ተስፋ ሙሉ ለሙሉ የሚቀለብስ፣የተከፈቱ በሮችን የሚዘጋ፣እንቆምለታለን ለሚሉት ማንኛውም ወገን ጥቅም በጊዜያዊነት ሆነ በዘላቂነት የሚጎዳ መሆኑን ሁሉም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ሁኔታውን በሰከነ መንገድ ማየት ይገባቸዋል። ዛሬም እንደ ትላንቱ ሰከን በሉ ብለናል።
ጃዋር ከኦሮሚያ ባለ ስልጣናት ጋር እየተነጋገረ ነው ምንም ችግር አልደረሰበትም
“ለማንኛውም አሁን #የጃዋር_መሐመድ መኖሪያ ቤት አከባቢ ያለው ሁኔታ ይህን ይመስላል። የኦሮሚያ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከጃዋር ጋር አብረው እንዳሉና ለደህንነቱም ጥበቃ ተገቢ እየተደረገለት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።”
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጃዋር አስቀድሞ ሲጽፋቸው የነበሩ ጉዳዮች ግጭት እንዳያስነሱ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ አላስፈላጊ ግጭት እንዳይከሰት ዜጎች የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ እየተጠየቀ ሲሆን መንገዶች በተለያዩ አቅጣጫዎች ሊዘጉ ስለሚችሉ ጉዞ ያልጀመሩ ሁኔታውን እንዲያጤኑ እየተገለጸ ሲሆን ይህን መሰሉን የሚያስጠይቅ ግጭት ቀስቃሽ መንገድ እንደማያዋጣ በአደባባይ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እንዲገልጹ የሚጠይቁ ወገኖችም አሉ።
ወጣቶቹን በተቀናጀ ሁኔታ ማንቀሳቀሱም ሆነ ለጃዋር ጋር ጠባቂዎቹ ሊነሱ ነው ተብሎ የሚወሰደው እርምጃ የፖለቲካ ስልጣን ማግኘት እና የፈለጋቸውን መፈጸም የፈለጉ ወገኖች እየፈጠቱት ያለ ድራማ የንጹሃን ሕይወት እንዳይቀጥፍ አስግቱዋል።
Filed in: Amharic