>

ጎንደርና አምቦ  -  መደመር  እና መቀነስ !!! (ዘመድኩን በቀለ)

ጎንደርና አምቦ  –  መደመር  እና መቀነስ !!!
ዘመድኩን በቀለ
ሀ፥ ፎቶ ፩
• ከላይ ነጭ የለበሱትና ሀጫ በረዶ መስለው የሚታዩት  ዘንድሮ ጎንደር ዩኒቨርስቲ የተመደቡ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ ወላይታ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላ ምን አለፋችሁ ሁሉም ቤርቤረሰቦች ናቸው።
• ተማሪዎቹ ከትምህርት ሰዓት ውጪ ጊዜአቸውን በአልባሌ ቦታ ከማሳለፍ በቃለ እግዚአብሔር እየረሰረሱ ደግሞም ቃሉን በመመገብ በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጠው የቃሉን ወተት በመጠጣት ላይ እንዳሉ የሚያሳይ ፎቶ ነው። ጎንደር ሄደህ ሊቅ ሆነህ ካልመጣህማ ጥፋቱ የራስህ ነው።
• ዘንድሮ ደግሞ እነ ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ ሁላ ጎንደር ነው የደረሳቸው አሉ። ጎንደሮችም የዘንድሮ ተማሪዎችን በነፍስ ወከፍ እንደ ወላጅ ተረክበዋቸዋል አሉ። አቤት ኢትዮጵያዊነት። ደስ ሲል። ተባረኩ አቦ። ዘር ይውጣላችሁ።
ሁ፥ ፎቶ ፪ 
• ዐማራ በመሆናቸው ብቻ የኦቦ ሽመልስ አብዲሳው አመራር ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ውጡልኝ ብሎ ያባረራቸው ተማሪዎች ወደ መጡበት ሀገር ለመመለስ መኪና አጥተው በአምቦ መነሃሪያ ተኮልኩለው የሚታዩ ናቸው። የአምቦ ህዝብ ድሮ ኢትዮጵያዊ ነበረ። አሁን ግን ምን እንደነካው መድኃኔዓለም ይወቅ። የሚገርመው የአምቦ ልጆች የኦሮሞ ልጆች በሙሉ በዐማራ ክልል ትምህርታቸውን በሰላም ጀምረዋል።
• ኦሮሞዎች በፈጠራችሁ ጀዋርና ሽመልስ አብዲሳን ሰምታችሁ ወንድሞቻችሁን አታስቀይሙ። ታዳጊዎች ናቸውና ሌላው ቢቀር እህል ውኃ ስጧቸው። ዳቦ ነገር ቆሎም ነገር ስጧቸው። ጡር ነው። በሸዋ ኦሮሞ ይሄ አያምርም። በፍፁም ጥሩ አይደለም። ግፍ በራስ ላይ መዓት ነው የሚያመጣው። ድሮ የማውቀው የሸዋ ኦሮሞ እርጎ ሲያጠጣ፣ ኢረዲባ ትኩስ እንጀራ በበርበሬ ለውሶ ሲያጎርስ ነው። ሰምታችኋል።
★ እናንት ዐማሮችም ብዙ አትጨነቁ። ሁሉም ያልፋል። የእነ ጃዋር ቦለጢቃ ሲከስር ሁሉም ወደ ነበረበት ይመለሳል። እናም አይዟችሁ። የዓሰሎጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ የመደመር ቀመር ዐማራን ስለማያካትት ነው። ተረስታችሁ ነው። እናም አንድ ቀን ሲያስታውሳችሁ ትማራላችሁ። እስከዚያው ኧረ በሰላም ወደ እናት አባታችሁ መመለሳችሁም ጥሩ ነው። መቆየት ደጉን ማን አየበት?
•••
ሻሎም !   ሰላም ! 
ጥቅምት 10/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic