>
5:13 pm - Sunday April 18, 8613

"መደመርም  ፣አለመደመርም ዋጋ ያስከፍላሉ ...!!!" (በታምሩ ገዳ)

“መደመርም  ፣አለመደመርም ዋጋ ያስከፍላሉ …!!!”
ታምሩ ገዳ
የዶ/ር አብይ አህመድ አዲሱ የመደመር ፍልስፍና አዘል መጽሐፋቸው ገና ወደ እንባቢዎች እጅ  ሳይገባ ፣መጽሐፍን በሽፋኑ አትገምግመው እንዲሉ ዘንድ  ከአይምሯቸውም ገና  ሳይብላላ  ብዙ እየተባለለት ይገኛል።
 በሰለጠነው አለም ለአንድ ማህበረሰብ   መጽሐፍትን የማንበብ  ባህልን ማጉልበት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የመንግስታዊ ተቋማት  ዋንኛ ግዴታዎች መካከል አንዱ  እንደሆነ  ብዙዎች ይስማማሉ ፣ምክንያቱም በእውቀት እና በትክክለኛ  መረጃዎች ላይ  የተገነባ  ህዝብ የቱንም ያህል የፕሮፓጋንዳው   ፈላጻዎች ከየትም አቅጣጫዎች ቢወረወሩበትም በቀላሉ የጭፍን ድጋፍ እና  የጥላቻ  ምርኮኛ እና ሰለባ ስለ ማይ ሆን  ነው።
 አንድ ለትንሽ  ጊዜያት ተራራቅን  ይቆየን፣ ነገር ግን የመደመር መጽሐፍ ደራሲ  ለሆኑት ለዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር  ቅርበት ያላት  ወዳጄ ጋር በቀጭኑ ሽቦ አማካኝነት ሰላምታ ካደረግን በሁዋላ  በጨዋታችን መካከል  ” የመደመር መጽሐፍን እንዴት አገኘሽው?”ስል  ጠይቅኩት   ያቺ ወዳጄም ትንሽ ቅዝቅዝ  ባለ ድምጽ መጽሐፉን  ገና እንዳላነበበችው ነገር ግን ሰኞ ማለዳ   ከቢሮው ሰተት ብሎ እንደሚመጣለት  አረጋገጠችልኝ።
እኔም በወዳጄ ምላሽ ትንሽ ግራ በመጋባት ምነው ይሄን ሁሉ ብዙ የተባለለት፣ለሚሊዬኖች በነፍስ ወከፍ ሊዳረስ  ታቅዶ በአፋን ኦሮሞ፣በአማሪኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተጻፈ  የመደመር መጽሐፍን  ለማንበብ አልተቀዳደምሽም? ስል ወዳጄን አስከትዬ ጠየቅኳት።  ያቺ ወዳጄም የጠ/ሚ/ር  አብይ  አስተዳደር  ተቃዋሚ  ወይንም ጭልጥ ያለች  ደጋፊ ያለመሆኗን  በቅድሚያ በመግለጽ እርሷ የመደመር መጽሐፍን በመኮነን እንቅፋት ባትሆንም  መጽሀፉን ተሯርጠው ፣በጉጉት የማይገዙ ሰዎች  “ጸረ መደመሮች” እንደሚባሉ  ሁሉ በተቃራኒው ሶስት መቶ ብራቸውን (አስር የአሜሪካ  ዶላር) ከፍለው  በመግዛት ይሁን በተውሶ መልክ ባለ ሁለት መቶ ሰማኒያ ገጹ የመደመር መጽሐፉን የሚያነብቡ ወገኖች  ቢኖሩ “ሆድ አደሮች፣   ጸረ አብዮተኞች …ወዘተ ” የሚል ተቀጽላ ስያሜ እንደሚለጠፍባቸው  እና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ  መደመርም ይሁን አለመደመርም ዋጋ እንደሚያስከፍሉ ትዝ ብቷን አካፍላኛለች
 ውዳጄ አስተያየቷን ስታጠቃልል   አንዳንድ   ወገኖች መደመር የሚለው  መጽሐፍን ከመንግስታዊ ፖሊሲ ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ከቅዱስ ቁራን እና  ከቅዱስ ቶራህ ጋር በማመሳሰል  ለዶ/ር አብይ አህመድ ያላቸውን ፍጹም ደጋፊነትን  ሲገልጹበት፣ እንደ እጅ መንሻነት ሊጠቀሙበት ሲሯሯጡ ፣ሌሎች እንዲሁ  መደመር በመጽሐፍ ብቻ ሳይሆን ልብ ለልብ   መናበብን እና የተግባር አርበኝነትን ይጠይቃል ፣ያስቀድማል የሚል አቋም ይዘው መታየታቸውን መታዘቧን ያወጋችኝ ወዳጄ የሰሞኑ አዲስ  ነጠላ ዘፈን እና መፈክርም  “መደመር! መደመር!መደመር!” እንደሚሆን ቅድመ ግምቷን ሰነዘረችልኝ። እኔም ወዳጄን ስለ ግልጽ እና ቅን ትዝብቷ በማመስገን   ለጊዜው ተሰነባበትን።
Filed in: Amharic