>

"ፊንፊኔ ላይ ቤት እንሰራላችኋለን ብለው ሜዳ ላይ ጥለውናል!!! "  የጅጅጋዋ ተፈናቃይ አሚና

“ፊንፊኔ ላይ ቤት እንሰራላችኋለን ብለው ሜዳ ላይ ጥለውናል!!! ” የጅጅጋዋ ተፈናቃይ አሚና
ሉሉ ከበደ
 ከአስር ቀን በፊት አልጀዚራ ያናገራት አንዲት ቀድሞ የጂጂጋ ነዋሪ የነበረችና አብዲ ኢሌ ያፈናቀላት እናት ኦሮሞ። “ነገር ግን እዚህ ካመጡን በሁዋላ ሞራላችን ነው የደቀቀው። የጠበቅነውን ነገር አላገኘንም። ተቸግረናል። ተርበናል። የደረሰልን የለም። እናም እኔ በመንግስት ተስፋ የለኝም ” አሚና ነበረች አዲስ አበባ ሱሉልታ ላይ በቆርቆሮ ከተሰራ መጠለያ ውስጥ ለአልጀዚራ ጋዜጠኛ ሮሮዋን የነገረችው። ሰላሳ የሚሆኑ ቤተሰቦች አንድ አካባቢ ሰፍረዋል።
አልጀዚራ እንዳተተው ባለፈው አመት የአሚና ታሪክ ከመላው ኢትዮጵያ የሚስተጋባ ነበር የመሬት የሀብትና የማንነት ግጭቶች በመላ ሃገሪቱ በተፋፋሙበትና ባገር ውስጥ መፈናቀል ኢትዮጵያ ከአለም ቀድማ በተገኘችበት ወቅት።ቁጥሩ ሶስት ሚሊየን የሚደርስ ህዝብ ባገሩ ውስጥ የተፈናቀለ  በየትም የአለም ክፍል አልነበረም። እስካሁንም የለም።
ለደረሰው ሰባዊ ቀውስ የአብይ መንግስት የሰጠው ደካማ ምላሽ በሰፊው ትችት አዝንቧል እንደ አልጀዚራ አባባል።ተፈናቃዮች ነፍስ አድን የምግብ እርዳታ እንዳይደርሳቸው ተደርጎ ነበር። ወደመጡበት እንዲመለሱ ለማድረግ የተወሰደ እርምጃ መሆኑ ነው። አንዳንድ እካባቢዎችም ለደህንነታችን እንሰጋለን እያሉ በግድ መልሰዋቸዋል።
እንደ አሚና አይነት ኦሮሞዎች ግን የተሟላ ቤት አዲስ አበባ ዙሪያ ተሰርቶላቸው እንደሚስፍሩ ቃል ተገብቶላቸው ነበር ባውቶብስ ተጋግዘው የመጡት። ሁለት አመት እየሆነ ነው ። አሚናና ጎረቤቶቿ በመንግስት እንደተከዱ ይሰማቸዋል። አሚና የአብይን መንግስት ጥሩና መጥፎ የተቀላቀለበት አድርጋ ነው የምትመለከተው። እንዲህ ትላለች “አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ነገር እየተደረገ ያለ ይመላል ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች ይሰቃያሉ።ስለዚህ በዚህ መንግስት ላይ እኔ ተስፋ የለኝም።”
“የትም ቦታ በየትም አቅጣጫ ሄደን መኖርና መስራት መቻል ነበረብን ። በየትኛውም አቅጣጫ ኢትዮጵያ ሀገራን ነች ብለን የምናምን ነን ። እዚህ የጣሉን ሆን ብለው እንድንሰቃይ ነው።” አሚና ዩያ ጂጂጋ የነበረች ጊዜ የራሷ ምግብ ቤት ነበራት።
ሱሉልታ – አዲስ አበባ።
ይህን ጽሁፍ የቀነጨብኩት ኦክቶበር 5 አልጀዚራ
 ” In Ethiopia, a forgotten refugee in her own land” ብሎ ካወጣው ጽሁፍ ነው።
Filed in: Amharic