>

ጀነራል አሳምነው ፅጌ ለምን …ለምን ሞተ ? ኢንጂነር ስመኘውስ..? (ሀብታሙ አያሌው)

ጀነራል አሳምነው ፅጌ ለምን …ለምን ሞተ ?
ኢንጂነር ስመኘው ለምን…ለምን ሞተ ?
ሀብታሙ አያሌው
በሐረር ከተማ የሚገኘው ታሪካዊው የራስ መኮንን ቤተመንግስት ሸሪፍ ለሚባል ግለሰብ ተሰጥቶት ከፊሉን መኖሪያው ከፊሉን ሙዚየም አድርጎታል። ያ ታሪካዊ ቤተመንግስት ካለመኖር ወደ መኖር እየተቀየረ ነው።
በከተማው መካከል ያለውን የራስ መኮንን ሃውልት ለማፍረስም ለሁለተኛ ጊዜ ሙከራ ተደርጓል።ወዲህ ደግሞ የኦቶማን ኢምፓየር መሪ የነበረችው ቱርክ ያንን ሁሉ ሸፍጥ ሰርታ ላደረሰችው ውድመት የአብይ አስተዳደር ሐረርን እንደገና እንድታሴርበት አስረክቧል።
 ነፍጠኛን ሰበርነው ያሉት ሰዎች ቱርክን በእልልታ ተቀብለው ሐረርን አስረክበዋል።አብያተክርስቲያናትን አንድዶ ካህናትን አርዶ የዘር ማጥራት የሚሰራው አካል፤ ማን ከማን ጋር ተጋምዶ እንደሆነ ተመልከት።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እቺን አገር ወደምን አይነት ማጥ ውስጥ እየከተታት እንደሆነ ተመልከት።
ጀነራል አሳምነው ፅጌ …”ከ500 አመት በፊት የገጠመን ፈተና…” ጃንሆይ ጥላሁን ለምን… ለምን…ሞተ ይባሉ ነበር።
አሁን እያንዳንድህ እራስህን ጠይቅ ጀነራል አሳምነው ፅጌ ለምን ለምን ሞተ ?
ወደ ግብፅ ፊትህን ስትመልስ ኢንጂነር ስመኘው ለምን…ለምን ሞተ ? አጥብቀህ ጠይቅ !!
* * *
ዜናው እንዲህ ይላል
“የቀድሞ የኦቶማን (ኡስማኒያ) ቆንፅላ በሀረር በትላንትናው ዕለት የባሕል መአከል ሆኖ በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ‘ያፕራክ አልፕ’ ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች
በተገኙበት በድጋሚ ተከፈተ። ቱርክ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን የከፈተችው በሀረር በ 1912 ነበር።”
Filed in: Amharic