>

ግዞተኛ ሆነን ስለማንችለው የታገሉትን ያህል ታግለን ሰውነታችንን ማስመለስ አለብን!!! (መስከረም አበራ)

ግዞተኛ ሆነን ስለማንችለው የታገሉትን ያህል ታግለን ሰውነታችንን ማስመለስ አለብን!!!
መስከረም አበራ
“ሃገሪቱ ውስጥ ያለሁ ጀግና እኔ ብቻ ነበርኩ፤ እኔም ስልጣን ይዣለሁ፤ ከዚህ በሃላ የሆንኩትን ብሆን ማንም ምንም አያመጣም” የሚል እሳቤ በመላው ኦሮሞ ፖለቲከኞች ዘንድ ሳይኖር አይቀርም።
 ይህ እሳቤ ውሎ አድሮ “ሰው እኔ ብቻ ነኝ” ወደ ሚል የተሟላ ውድቅ እሳቤ እያደገ ነው።ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚያደርገው ደግሞ ሰው ብቻ ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍን የመሰለ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚያደርገው ኦሮሞ ብቻ ነው ማለት ነው።
 ኦሮሞ ከአርሲ፣ባሌ፣ቦረና፣ኤሉ አባቡራ በመኪና መጥቶ አዲስ አበባ ላይ ሲፈልግ ተሰልፎ ፣ ሲያሻው በአል አክብሮ፣ ውሎ አድሮ ወደ መጣበት ይመለሳል።ሌላው ደግሞ ለግል ጉዳዩም አዲስ አበባ መግባት አይችልም።
 ለዚህ ሁሉ ያበቃን የስምንት ወሩ ትግል ነው! ይህን ትግል ለብቻው የታገለ ባይኖርም የኦሮሞ ቄሮ የበለጠ ስለታገለ ሰውነታችንን ተቀምተን ሰውነታቸው ላይ እንዲደረብ ሆነ፤ለጀግንነታቸው ማስታወሻ ዜግነታችን ተቀምቶ የነሱ ዜግነት ላይ ሲደመር እነሱ ጌታ እኛ ባሪያ ሆነናል። የዛሬው የሰላማዊ ሰልፍ እገዳ የሚያስረዳው ይሄን ነው።
ሰውን ሰው የሚያደርገው ትግል ነው።ስለዚህ ግዞተኛ ሆነን ስለማንችለው የታገሉትን ያህል ታግለን ሰውነታችንን ማስመለስ አለብን። ታጋይ የምትወልድ የአንድ ዘር እናት ብቻ አይደለችም። ስልጣን ላይ የተቀመጠው አካል ያላሰበላት ሃገር በእኔ ቢጤ ተራ ዜጋ ጥንቃቄ እና ስጋት የትም አትደርስም። የሽንፈት ሰላም በአፍንጫችን ይውጣ!
በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ የሚደረገው አፈና፤ ጫና እና መድሎ እጅግ አሳፋሪ እና የሚወገዝ ነው!!!
ያሬድ ሀይለማርያም
የዜጎችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ በአደባባይ የመሰብሰብ እና ተቃውሞን የመግለጽ መብት የአብይ አስተዳደር ሊያከብር ይገባል። ለጥቅምት ፪ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በባለአደራ የተጠራው ሰልፍ ሕጋዊ ሂደቱን የተከተለ ቢሆንም በአዲስ አበባ ፖሊስ መከልከሉን አሁን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ይሄ ግልጽ አፈና ነው። ኦዴፓ ከትላንት ጀምሮ እያደረጋቸው ያሉት ሕገ ወጥ ተግባራት አገሪቱን ወደ ቀውስ ውስጥ የሚከቱ ናቸው። ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚወስዱ መንገዶችን በድንጋይ በመዝጋት የዜጎችን በነጻነት የመዘዋወር መብት ጥሷል።
መንግስት አንዱ ወገን ፈቃድ እንኳ መጠየቅ ሳያስፈልገው ብድግ ብሎ ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ የሚያደርግበት፤ ሌላው ዜጋ ደግሞ ተገቢውን ሕጋዊ ሂደት አክብሮና አሳውቆ ስብሰባና ሰልፍ እንዳያደርግ የሚከለክልበት ወገንተኝነት የተሞላው አካሄድ ሊቆም ይገባል። በተለይም በአዲስ አበባ ነዋሪ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና እና መድሎ እጅግ አሳፋሪ እና የሚወገዝ ነው።
ፍትሕ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤
Filed in: Amharic