>

የአዲስ አበባ ህዝብ መንግስታዊ አድልዎ እየተደረገበት ነው!!! (ብርሀኑ ተክለአረጋይ)

የአዲስ አበባ ህዝብ መንግስታዊ አድልዎ እየተደረገበት ነው!!!
ብርሀኑ ተክለአረጋይ
ይህ አንድም ትንኮሳ ነው!
አንድም ተረኝነት ነው!
አንድም መንግስታዊ አድልዎ ነው!!!
 በባለአደራ ምክር ቤት መግለጫ ላይ በተገኘሁበት ወቅት የተመለከትኩትም ይህንኑ ነበር። መግለጫው እየተሰጠ በነበረበት ወቅት  ቄሮ ነን የሚሉ አካላት “ዳውን ዳውን እስክንድር”እያሉ ወደ ቢሮው መጡ። መንገድ ዘግተው ቆመውም “የአዲስ አበባ ዱርዬና ነፍጠኛ እኛን አይወክልም” “ቄሮ ያሸንፋል” እያሉ መጮህ ጀመሩ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊታቸው የሚገኝ ቢሆንም ፖሊሶቹ በዝምታ እየተመለከቷቸው ነበር። ይልቁኑ ለቅስቀሳ የተዘጋጁ የነ እስክንድርን መኪኖች አስረው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱ። ያለ ማንም ከልካይነት ሲረብሹና ሲቃወሙ የነበሩት ወጣቶች ሲደክማቸው በዝምታ በየጥጋጥጉ ቆሙ።
መግለጫው እንዳበቃም የአዲስ አበባ ወጣቶች እስክንድር ያለበትን መኪና ተከትለው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ከፅ/ቤቱ አካባቢ መውጣት ጀመሩ።ይኼኔ በዝምታ ተውጦ ከነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ እስከ አፍንጫው የታጠቀ የፖሊስ ሀይልና አድማ በታኝ ወጥቶ መንገዱን ሙሉ በሙሉ ዘጋ።
የአዲስ አበባ ወጣቶችም ይቺ ነገር ፍለጋ ናት ብለው ወደየቤታቸው በሰላም ተበታትነው ሄዱ። በመንገዴ ላይ በተለይም በአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት ውስጥ የታጠቀና ብዛት ያለው አድማ በታኝ ተዘጋጅቶ ይታይ ነበር።
አዲስ አበባ ላይ ኢሬቻ በሰላም የተከበረው ኢሬቻ  አዲስ አበቤን ሁሉ ስለሚወክል አይደለም። ጥቅምት ሁለት ጨዋው አዲስ አበቤ ድምፁን ለማሰማት የቆረጠው ቀን ነው።የዚህን ሰልፍ ዝግጅት መበጥበጥ ያስገምታል።ሁለት ቀን መንገድ ተዘግቶበት እንኳን በአክብሮት ቤቱ ተቀምጦ በአላችሁን እንድታከብሩ በጨዋነት ላያችሁ አዲስ አበቤ ይህ አይገባውም።ስነ-ስርዓት ያስፈልጋል! ይህ የአዲስ አበቤን ጥያቄ አያቆመውም ከንቱ አትልፉ፣ አትገመቱም!
Filed in: Amharic