>

አላዋቂነታቸውን ለማወቅ የማይፈልጉት የኦሮሞ ሊሂቃን!!! (ታደለ ጥበቡ)

አላዋቂነታቸውን ለማወቅ የማይፈልጉት የኦሮሞ ሊሂቃን!!!
ታደለ ጥበቡ
*የኦሮሞ ሊሂቃን ድንቁርና ሁሌም ይገርመኛል።በታሪክ እንደ ኦሮሞ ሊሂቃን ሆነው ምርምር፣ታሪክ የማያውቁ ማህይማን ይኖራሉ ለማለት ይከብደኛል።ለሚናገሩት ማስረጃ፣ለ ሚጽፉት ዋቢ የላቸውም።ቢቻል መድረክ ተመቻችቶ ብንከራከር ደስ ይለኝ ነበረ።ግን የታሪክ አጭበርባሪዎች ስለሆኑ ደፍረው አይቀርቡም።
1.ሆራ ፊኒፊኔ በአዲስከበባ ከተከለከለና ከቆመ  150 ዓመት ሆነው ይላሉ ነገርግን አዲስአበባ እንደገና ከተቆረቆረች 133 ዓመቷ ነው ሲባሉ ማስረጃ የላቸውም።
2.ዳግማዊ ዓጤ ምኒልክ 5 ሚሊዮን ኦሮሞወችን ጨፈጨፈ ይላሉ ነገርግን በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከ5 ሚሊዮን በታች ነበረ’ኮ ሲባሉ አሁንም ማስረጃ አያቀርቡም?
3.እኛ አዲስአበባ “በረራ”ትባል እንደነበረ በካርታ ላይ የተሳለ፣ ብራና ላይ የተጻፈ፣ በምዕራባዊያንና ዐረብ የመካከለኛው ዘመን ምሁራን መጻሕፍት ምስክርነት ያለው ማስረጃ ስናቀርብ እነሱ አዲስአበባ ፊንፊኔ ትባል እንደነበረች ማስረጃ አያቀርቡም።ነገርግን ያልነበርች፣የሌለች፣ወደፊትም የማትፈጠር ፊንፊኔን በተረት ተረት ይነግሩናል።
4.ሌላውን ሰፋሪ ይላሉ ነገርግን ኦሮሞዎች አሁን የሰፈሩበትን መሬት ነባሩን ሕዝብ እየደመሰሱ በወረራ እንደያዙ ተአማኒነት ያላቸው ጥንታዊ ሰነዶችን፣የምርምር ውጤቶችን በማስረጃነት ስናቀርብ በአንጻሩ እነሱ አንድም ማስረጃ አለን አይሉም።እንዲያውም የራሳቸው የኦሮሞ ምሁራን ኦሮሞ በወረራ እንደተስፋፋ የጻፉትን ማስረጃ አይቀበሉትም።
እንዲህ የፊንፊኔ የቄጤማ ተረት በበረራ የእውነት ሰይፍ ስንቆርጠው፤የፊንፊኔን ተረት ተረት በማስረጃ ስናጋልጠው እስከዛሬ አንድም የኦሮሞ ምሁር በሰነድ፣በማስረጃ ሲሞግት፣ሲከራከር አላየሁም።ነገርግን ያለማስረጃ ያልተፈጠረውን እንደተፈጠረ አድርገው ሲከራከሩ ይውላሉ።ለዚህም ነው የምሁራን ማህይም ናቸው የምለው።ዛሬም በተስፋዬ ገብረአብ “የቡርቃ ዝምታ”መጽሐፍ በምናብ በተፈጠረው የአኖሌ የውሸት ሐውልት ስር ላይ ቆመው ነጠላቸውን ዘቅዝቀው ባልተፈጠረ ነገር ላይ እንደተፈጠረ አድርገው ሲያለቅሱ ውለዋል።
ነገርግን ዐፄ ምኒልክ 5 ሚሊዮን ኦሮሞ እንደጨፈጨፉ፤በወቅቱም ዐፄ ምኒልክ ወደ አርሲ ስለመዝመታቸው ማስረጃም የላቸውም።
በአንጻሩ ግን ኦነግ በአርባጉጉ፣በጉራፈርዳ፣በጅማና በሌሎች አካባቢዎች በአማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን የዘር ማጽዳት ወንጀል በማስረጃ፣በመረጃ፣በፎቶ፣በምስል ማቅረብ ይቻላል።
Filed in: Amharic