>

አያቶቻችን «ነፍጠኛ» እየተባሉ በአረመኔነት እየተከሰሱ ያሉት ሰብዓዊነት የነበራቸው ሰዎች በመሆናቸው ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

አያቶቻችን «ነፍጠኛ» እየተባሉ በአረመኔነት እየተከሰሱ ያሉት ሰብዓዊነት የነበራቸው ሰዎች በመሆናቸው ነው!
አቻምየለህ ታምሩ
የኦሮሞ ብሔርተኞች እያራመዱት ያለው ፖለቲካ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ እንድንረሳው ያደረጉንን ከ1514 ዓ.ም. — 1881 ዓ.ም. ድረስ ከባሌ በታች የተነሱ የኦሮሞ ሉባዎች ያደረሱትን የአራት መቶ ዓመታት ጥፋት፣ ግፍና በደል እንድናስታውሰው እያደረገን ነው።
የኢትዮጵያ መሬት በነገድ ይከፋፈል ከተባለው በዛሬዋ ኢትዮጵያ አንዲት ጋት መሬት የማይኖረው ኦሮሞ ብቻ ነው። ኦሮሞ ዛሬ ተስፋፍቶ የያዘው የኢትዮጵያ ክፍል በ1514 ዓ.ም. ወረራ ከጀመረው ከመጀመሪያው ሉባ መልባ እስከ አምስተኛው ሉባ ምችሌ ድረስ ከባሌ በታት ተነስቶ ነበሮቹን የኢትዮጵያ ነገዶች ድምጥማጣቸውን እያጠፋ፣ ማንነታቸውን እየቀየረ፣ ቋንቋቸውን እየደመሰሰ፣ በመሬታቸው ላይ ጭሰኛ እያደረገ፣ የነበራቸውን ቁሳዊና መንፈሳዊ ሥልጣኔ እያወደመ፣ የኢትዮጵያን ምድር የሰው ልጅ ግዳይ ክምርና የደም ጎርፍ የሚፈስበት ገሀነም በማድረግ  እንደ ዋርካ የተንሰራፋበት የአባቶቻችን ባድማ ነው።
ይህን ሁሉ የአራት መቶ ዓመታት ግፍና መከራ ረስተን የኖርነው ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ «ጥጃ ጠባ፤ ሆድ ገባ» በማለት የኦሮሞ ሉባዎች ነባሮቹን የኢትዮጵያ ነገዶች ወረው በመደምሰስ በያዙት የነባሮቹ ርስት ላይ የሰፈሩትን ስለተዋቸውና  እንደ ተቀረው ሕዝባቸው ሁሉ የራሳቸው ሕዝብ አድርገው በመቁጠራቸው የሳቸው መንፈስ ተጋብቶብን እንጂ ከመልባ እስከ ምችሌ ድረስ ያሉት ሉባዎች በወረሩት የአገራችን ክፍልና ሕዝብ ላይ ያደረሱትን ጥፋት ስለማናውቅ አይደለም።
ታላላቆቹን አባቶቻችንን «ነፍጠኛ» በማለት የሰደብን የሚመስላቸው የዛሬዎቹ ሉባዎች ቢያውቁት ኖሮ ሉባዎቹ  ዘሮቻቸው  ከባሌ በታች ተነስተው በወረራ በያዙት የሌሎች ርስት ላይ ባለመሬት የሆኑት ነፍጠኛ እያሉ የሚከሷቸው የኢትዮጵያ ታላላቆች ሰብዓዊ ስለሆኑ ወራሪዎቹን ሉባዎችን፣ አባቢያዎችንና አንጋፋዎችን ወደመጡበት እንዲመለሱ ባለማድረጋቸው ነበር። ነፍጠኛ እየተባሉ በጭካኔ የሚከሰሱት የኢትዮጵያ አገልጋዮች  ጨካኝ ቢሆኑ ኖሮ ወራሪዎቹ  ሉባዎችን  በወረራ ከያዙት መሬት ላይ አፈላማ አስከፍለው በወረራ የያዙትን መሬት አስለቅቀው ወደመጡበት ከባሌ በታች ወዳለው  አገራቸው ያባርሯቸው ነበር። ሰብዓዊ ሆነው ይህን ባለማድረጋቸው ግን ungrateful የሆኑት  የሉባ ልጆች ዛሬ ላይ «ነፍጠኛ» እያሉ  ሰብዓዊነት ሞልቶ የፈሰሳቸውን አያቶቻችን እንደ ኢሰብአዊ ፍጡር ሊቆጥሯቸው ይፈልጋሉ።
Ungrateful  ለሆኑት የሉባ ዘሮች ዘሮቻቸው የሆኑት ሉባዎች  ወደምኒልክ አገር መጡ እንጂ ዳግማዊ ምኒልክ ወደነሱ አገር እንዳልሄዱ  ልናስታውሳቸው ያስፈልጋል። እንኳን በደል ያልደረሰውን በደል ቢደርስ እንኳ ተጠያቂው ወደ ሰው ቤት ሄዶ  የተጎዳው ሌባው  እንጂ  ባለቤቱ በሌባው ላይ በደረሰው ጉዳት  ተጠያቂ ሊሆን አይችልም። ከባሌ በታች የተነሱት የሉባ ዘሮች ዛሬ ላይ  በደል ደረሰብን ካሉ  ተበደልን ለሚሉት ተጠያቂ ማድረግ ያለባቸው ባለቤቱን ዳግማዊ ምኒልክን ሳይሆን ወደ ምኒልክ አገር  የገቡትን ሉባዎች ነው።
ስለዚህ ነፍጠኛ እያሉ በሚዘልፏቸው አያቶቻችን ተበድለናል እያሉ ሒሳብ እናወራርድ የሚሉንን ungrateful የሆኑ የሉባ ልጆችን «ተው ማነህ ተው ማነህ የተኛ ሰው አለ ትቀሰቅሳለህ» ልንላቸው ይገባል። በሉባ በተመራው የአራት መቶ ዓመታት ወረራ በጣም ከፍተኛ  ግፍና በደል የደረሰበት ሕዝብ አለ፤ እና ተዉ የተኛ ሰው አለ አትቀስቅሱ በሏቸውም። የመሬቱን ባለቤቶች ወረሩን፣ በደል አደረሱብን  ብላችሁ ስለካሳ ካወራችሁ፤ ማነው በደል ያደረሰው? ማነው በሰው ርሥት ላይ የሰፈረው? ማነው በታሪክ ሂደት በደል የደረሰበት? ማነው ካሳ የሚያስፈልገው? ማነውስ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት? የሚሉት ጉዳዮች ውስጥ ለመግባት እንገደዳለን በሏቸው። ቢፈልጉ  አለማቀፍ ደረጃ ዳኝነት ይቋቋምና ይግባኝ የሌለው ፍርድ ይሰጥ!  በሚሰጠው አለማቀፍ ብይን  አማራው ኦሮሞ መሬት ላይ ሠፍሮ ከተገኘ አፈላማ ከፍሎ ይለቃል! በሌሎች ርሥት ላይ ሰፍሮ የተገኘው ኦሮሞው ከሆነም አፈላማውን ከፍሎ  ላደረሰው በደል ካሳ ከፍሎ የሠፈረበትን የሌሎችን ርሥት ይለቃል! ያኔ   ፍትሕ ይሰፍናል! አበቃ!!!
Filed in: Amharic