>

ለኢሬቻ ብለው አምጥተው  ኢሬቻ አበሏቸው (ዘመድኩን በቀለ)

ለኢሬቻ ብለው አምጥተው  ኢሬቻ አበሏቸው 
ዘመድኩን በቀለ
 * የዋሁን ኦሮሞ ተጫወቱበት! አንከራተቱት! ለበሽታም ዳረጉት!!! 
* በአንጻሩ እነሱ ሸቀሉበት! ፖለቲካዊ ግባቸውንም አሳኩበት!!!
•••
ጃዋርን አምነው ለኢሬቻ በኣል ብለው ከወለጋ ድረስ የመጡ የወለጋ ኦሮሞዎች በአዲስ አበባ እንዲህ በሚያሳዝን መልኩ በየሜዳው ተረፍርፈዋል። ደረቅ ሲሚንቶ ላይ ተኝተዋል። የሚበላ የለ። የሚጠጣም የለም።
•••
እነ ጃዋር ፖለቲካውን ከሸቀሉባቸው በኋላ እግርህን ብላ ብለዋቸው እነሱ ወደ ቅንጡ ሆቴላቸው ተመልሰዋል። ሲጀመር ጃዋር ኦሮሞ አይደለም። ኦሮሞ ግን የገቢ ምንጩ ነው። ያውም የማይነጥፍ የገቢ ምንጩ። አሩሲዎችም ባዶ ሆዳቸውን እያፋሸኩ ተመልሰዋል ተብሏል።
•••
አሁን እነዚህን ምስኪኖች አበል እንከፍላለን ብሎ አምጥቶ ማሰቃየቱ ምን ይባላል? ፌር ነው ወይ? ከያሉበት መኪና በነፃ ያቀረበው አካል ከቀረጻ በኋላ ስትፈልጉ ገደል ግቡ ማለቱም አይደል? ወንዝ ዳር ቄጤማ ውኃ ነክሮ ለመረጫጨት ጊቤን የሚያክል ወንዝ ተሻግሮ የግዮን ኩሬ ላይ እንዲህ መከራ መብላትን ምን ይሉታል። አይ ምስኪን።
•••
አሁን እርዳታም ለማድረግ አስቸገረ እኮ፤  ሽመልስ “የአዲስ አበባ ህዝብ ሰበርንህ” ሲለው  እነዚህ ደግሞ “ኤዬን ” ብለው በደስታ ሲያጨበጭቡ የነበሩ ናቸው። ማን እህል ውኃ እንኳ ያቅርብላቸው?
• ወለጋ ጴንጤ ነበር። ኢሬቻም አያውቅ። ምን ነክቷቸው ነው ግን እንዲህ ለስቃይ ለዋቃ ጉራቻ መከራ የሚያዩት?
ሻሎም !  ሰላም !  
መስከረም 25/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic