>
5:13 pm - Tuesday April 19, 0692

ኦሮማራ ጥምረት ኦሮማይ ሆኗል! ቀጣዩ አሰላለፍስ...!?!  ( አንተነህ ሙሉጌታ)


ኦሮማራ ጥምረት ኦሮማይ ሆኗል! ቀጣዩ አሰላለፍስ…!?!
   አንተነህ ሙሉጌታ
ተረኛ ባለስልጣን ነን ባዮች ወደ ስልጣን ለመምጣት ያበቃቸው አንድም ብዓዴንና ኦህዴድ በጥምረት በህዎሃት ላይ መነሳታቸው; አንድም የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ ትግል መቀናጀቱ ህዎሃትን ከአራት ኪሎ መንቨሯ አፈናቅሎ ወደ መቀሌ በመባረሯ ምክንያት ነው።
እንዳለመታደል ሁኖ ከዚህ ጥምረት ውስጥ አንደኛው ወገን በሌላኛው ላይ ክህደት ፈጽሟል። ኦህዴድ በብዓዴን ላይ; የኦሮሞ ትግል መሪዎች በአማራ ሕዝብ ላይ ክህደት ፈጽመዋል። ክህደት መፈጸም ብቻም አይደለም ; የበላይ ሁነናል በሚል የጅል እብሪት ታውረው ጦርነት እየጎሰሙ ነው።
ክህደት የተፈጸመበት ወገን የወያኔ ጉዳይ ገና ስላልተቋጨ በአንድ ጊዜ በሁለት ግንባር ውጊያ መክፈት አዋጭ አይደለም ብሎ ለጊዜው አይቶ እንዳላየ ቢያልፋቸው እነሱ ግን ከምር የበላይ የሆኑ መስሏቸው እየተጃጃሉ ተከታዮቻቸውንም እያጃጃሉ ነው።
ተረኛ ነን ባዮች እንዲህ የሚጃጃሉት በእነሱ ቤት የፌደራሉንም ሆነ የአዲስ አበባን ስልጣን በበላይነት ተቆጣጥረው ልባቸው ውልቅ ብሏል።
እነዚህ ጅሎች አይገባቸውም እንጅ ቢገባቸው እንዲህ ሲጃጃሉ ሁሉም ሰው አይቶ እንዳላየ የሚያልፋቸው በአንድ ጊዜ በሁለት ግንባር ጦርነት መክፈት ብልህነት አይደለም ብሎ  ለጊዜው ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እንስጥ ብሎ ለጊዜው አውቆ ቢተዋቸው በእነሱ ቤት የአማራን ሕዝብም ሆነ የአዲስ አበባን ነዋሪ አሸንፈውና ሰባብረው አዲስ አበባ ከተማን ተቆጣጥረው የግላቸው ያደረጉ መስሏቸው ነው የሚጃጃሉት። ነገ ከወያኔ ጋር ያለው ፋይል ሲዘጋ የዛሬዋን አይነት ሽለላ ፈጽሞ አይደግሟትም።
ሌላው ቢቀር አዴፓ ለኦዴፓ የሚሰጠውን ድጋፍ እርግፍ አድርጎ ቢተው ወያኔ ወደ ኋላ ተመልሳ በካልቹ እየጠለዘች እንደምታሯሩጣቸው ማስታወስ የማይችሉ ዝንጉዎች ናቸው።
የኦሮማራ ጥምረትም እዚህ ላይ ካቆመ የአማራ ሕዝብም በሬ ካራጁ አይሆንም። ክህደት ብልጠት አይደለም። እምነትም ጅልነት አይደለም። የእስካሁኑ ጥምረት ቢያንስ ወያኔን ከአራት ኪሎ አባሯል። ስለዚህ በአማራና ኦሮሞ ሕዝብ የትግል ጥምረትም ሆነ በአዴፓና ኦዴፓ ጥምረት የሚቆጭ አይኖርም። አሁን ግን ሁሉንም ነገር ያበቃለት መስሏል። ኦሮማይ! “ኦሮማይ” አበቃ ማለት መሰለኝ።
ተረኛ ገዥ ነን ባዮች ገና ለገና የኢትዮጵያን ሕዝብ በተረኝነት ረግጠው የመግዛት  ሕልማቸውን ያደናቅፍብናል ብለው የሚፈሩትን የአማራን ሕዝብ ለመሰባበር “ውሻ ወደ ትፋቱ” እንዲሉ ወደቀድሞ ገዥዎቻቸው መቀሌ ሂደው ከትህነግ/ህዎሃት ጋር ፀረ-አማራ ግንባር መስርተው በመጡ ወር ባልሞላ ጊዜ ነው በአደባባይ እንሰባብራችኋለን ብለው መደንፋት የጀመሩት።
ለማንኛውም እስካሁን ድረስ በእናንተ ድንፋታ የሰበራችሁት ሕዝብ የለም እንጅ ይሄ የሚያጃጅላችሁ የድንፋታ ዛር ደም ፈሶ ካልተገበረለት ሰከን የማይል ከሆነና መስበርና  መሰባበር የግድ ከሆነ የምትደሰኩሩለት የጦርነት ፋይል ገና ወደፊት  የሚከፈት እንጅ አሁን እንደምትለፋደዱት ተዋግታችሁ የዘጋችሁት የጦርነት ፋይል የላችሁም።
እነዚህ ለእምነት የማይበቁ ከሀዲዎች በተረኛ ነን መንፈስ አጎንብሱ እንጋልባችሁ ሲሉ ትናንት ወያኔን ሲታገሉ ከጎናቸው ሁኖ መከታ የሆናቸው ሀይል ዛሬም እስከነ ትጥቁና ሙሉ ሀይሉ ዝግጁ ሁኖ ያለ መሆኑን ረስተውታል።
ነገ ቁርጥ ሁኖ የተመኛችሁት መስበር መሰባበር የማይቀር ከሆነ ጦርነታችሁ ከአማራ ሕዝብ ጋር ብቻ አይደለም። ይሄ እልቂት ሲጀመር አማራ ብቻውን ይገጥመናል ብላችሁ በማሰብ እንዳትጃጃሉ ልምከራችሁ።
የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይም ሆነ የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄ የአማራ ብቻ ሳይሆን የአፋሩ; የሶማሌው; የጉራጌው; የወላይታው; የጋምቤላው; የከፋው; የጋሞው; የዶርዜው ወዘተ ወዘተ የጋራ ጉዳይ ነው። የትኛውም ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ከአዲስ አበባም ሆነ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ሀብት ሲገለል ዝም ብሎ ጥቅሙን አሳልፎ የሚሰጥ አይኖርም።
የአማራ ሕዝብ ከአፋሩ; ሶማሌው; ጉራጌው; ወላይታው; ጋምቤላው; ከፋው; ጋሞው; ዶርዜው; በእኩልነትና ፍትሃዊነት የሚያምነው ኦሮሞ ወዘተ ወዘተ ጋራ በአንድነት በመቆም በኢትዮጵያ እኩልነትና ፍትሀዊነት እንዲሰፍን የሚደረገውን ትግል የማስተባበሩን ሀላፊነት ይወጣል።
የአማራ ሕዝብ ከቁጥሩ ግዙፍነትና በመላው ኢትዮጵያ ከገነባው ማህበረሰባዊ መዋቅር አንጻር በኢትዮጵያ እኩልነትና ፍትሀዊነት እንዲሰፍን የሚደረገውን ትግል የማስተባበር ሀላፊነት አለበት።
 በአማራ ሕዝብ አስተባባሪነት የሚመሰረተው የእኩልነትና የፍትህ ግንባር በአንድ ወገን ሲቆም በእነ ጃዋር መሃመድ; ሽመልስ አብዲሳ እና በቀለ ገርባ  የሚመራው አክራሪው የኦነግ ቡድን ከትህነግ/ ወያኔ ጋር በመቀናጀት እየመሰረቱት ያለው የፀረ- እኩልነትና የፀረ-ፍትህ ግንባር በተጻራሪነት ይሰለፋሉ። ይህ አሰላለፍ መታየትም ጀምሯል።
እነ ጃዋርና በቀለ ገርባ ከትህነግ/ ወያኔ ጋር የጋራ ጥቅምና የጋራ እስትራቴጅ ስላላቸው የቁርጡ ቀን አንድ ላይ እንደሚቆሙ  አስቀድሞም ይታወቃል።
 እነ ጃዋር መሃመድና በቀለ ገርባ እንደ ከብት የሚነዱት መንጋ አይገባውም እንጅ የሚገባው ከሆነ አንድ ነገር ግልጽ ላድርግለት። ይኸ መንጋ ሜንጫ ይዞ ሲንጋጋ የማይረዳው ነገር ቢኖር የእነሱ ሜንጫ የሌሎችን አንገት የሚቀላውን ያክል ተጻራሪው ሀይልም የሚተኩሰው ጥይት የመንጋውን ጭንቅላት ዱቄት የሚያደርግ  እንደሆነ ላስታውሰው እወዳለሁ። ጃዋርና በቀለ ገርባ እናንተ አትሞቱም ብለዋቸው እንደሁ አላውቅም።
እስካሁን ድረስ መልስ ያላገኘሁላቸው ሁለት ጥያቄዎች አሉኝ።
1. አዴፓ በዝምታ የሚጓዘው እስከመቸ ነው? የኦርቶዶክስ ሕዝበ ክርስትያን በአዲስ አበባ: በደብረ ዘይትና ሌሎች አካባቢዎች  በመስቀል በዓል እለት የፌደራል ፓሊስና የኦሮሚያ ፓሊስ የኢትዮያን ሰንደቅ አላማ ከንዋየ ቅድሳት; ከከበሮና ከመዘምራን ልብስ ላይ እየገነጠለ በመጣል ክርስትያኑ ሕዝብ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን እንዳይፈጽም ሲከለክል ነበር። በዚህ ምክንያት በደብረ ዘይት በኪዳነ ምህረት ቤተክርስትያን የመስቀል በዓል ጭራሹኑ አልተከበረም።
 በሌላ በኩል ይኸው ሀይል የኢሬቻ በዓል ላይ የኦነግ ሰንደቅ አላማ በነጻነት እንዲውለበለብ ፈቅዷል። በዚህ መንግስት ኦሮሞ ከሆንህ የፈለግኸውን ወንጀል መፈጸም ትችላለህ። ንጹሃንን በጅምላ ትጨፈጭፋለህ: ለፍርድ አትቀርብም (በቡራዩ ምስኪን ጋሞዎች በጅምላ መጨፍጨፋቸውን ልብ ይሏል)። ኦሮሞ ከሆንክ የፈለግኸውን ያክል ገንዘብ ከባንክ ትዘርፋለህ: የዘረፍኸውን ገንዘብ በነጻነት እንድትጠቀም ይፈቀድልሀል (በወለጋ 18 ባንኮች ተዘርፈው ዘራፊዎቹ በሕግ ሳይጠየቁ በነጻነት ይፏልላሉ)።
በተቃራኒው ደግሞ ኦሮሞ ካልሆን ሀይማኖታዊ ስርዓትህን የቤተ ክርስትያንህን አርማ ይዘህ እንዳታከበር ፌደራል ፓሊስ
ይከለክልሀል።  ኦሮሞ ከሆንህ ግን የኦነግንም ሆነ ሌላ የፈለግኸውን ባንዲራ በነጻነት እያውለበለብህ በሌሎች ላይ እንድትዝት ይፈቀድልሀል። ለስሙ የፌደራል ፓሊስ አዛዥነት የአዴፓ ድርሻ ነው። (የፌደራል ፓሊስ አዛዥ የአዴፓ አመራር ነው)።
እንዲህ አይነት ግልጽ የወጣ የአፓርታይድ ስርዓት በወያኔ ጊዜም አልነበረም። ይኸ ሁሉን ሲሆን አዴፓ በዝምታ የምትመለከተው እስከ መቸ ነው? ከዶ/ር አብይ ጋራ ያላችሁ ስምምነት ምንድን ነው? ዶ/ር አብይ እስከ መቸ ነው በዝምታ ተመልከቱ ያላችሁ? ዝምታችሁ የሚሰበረው መቸ ነው?
 አዴፓ ትናንት ለህዎሃት አገልጋኝ ሎሌ የነበረውን ያክል አሁንም ለኦነግ/ጃዋር መሃመድ አገልጋይ ሎሌ ሁኖ የሚቀጥል ከሆነ ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለሌላው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ከባድ ፈተና ይሆንበታል።
በተቃራኒው አዴፓ በእውነት ተለውጦ ከሆነ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ድርጅቶችን (አንድ ላይ ሆኑም ተከፋፈሉ ); የሶማሌን; የአፋርን; የጋንቤላን ወዘተ ወዘተ የፓለቲካ ድርጅቶች አስተባብሮ የጋራ ግንባር መስርቶ ከተነሳ  በትህነግ/ ወያኔና እነ ጃዋር-በቀለ ገርባ ግንባር ላይ ታላቁን የአድዋ ድል በመድገም ነፍጠኝነት ምን እንደሁ ለዘመኑ ባንዳዎች በተግባር አሳይቶ ታሪክ ይጽፋል። በኢትዮጵያም ወደኋላ የማይቀለበስ ፍትህ, ዲሞክራሲንና እኩልነትን ያሰፍናል።
አዴፓ ለህዎሃት እንዳደረገው ሁሉ ለተረኞች አገልጋይ ሎሌ ሁኖ ከቀጠለ እኛም “ብዓዴን ሆዳም ባንዳ” እያልን ስንጮህ ልንኖር ማለት ነው።
2. ሁለተኛው ጥያቄየ የዶ/ር አብይ ጉዳይ ነው። የዶ/ር አብይ አቋም  እስካሁን ግራ እንዳጋባኝ ነው። እሱ የሚያወራውና እሱ የሚሾማቸው ሰዎች የሚፈጽሙት ነገር አራምባና ቆቦ ነው። እሱ ሌትና ቀን ከሚሰብከን ተቃራኒውን እየፈጸሙ ያሉ ባለስልጣኖቹን እስከ መቸ በዝምታ እንደሚመለከታቸው ግራ አጋቢ ነው።
ዶ/ር አብይ ለይቶለት አሰላለፉን ግልጽ ቢያደርግልን ለሁለቱም ወገን ጠቃሚ ነበር።
Filed in: Amharic