>

አውዳሚ ተረኝነት - አውዳሚ ፈረቃ (ሀብታሙ አያሌው)

አውዳሚ ተረኝነት – አውዳሚ ፈረቃ
ሀብታሙ አያሌው
አዲስ አበቤ ጥቅምት 2 ላይ አተኩር!
 
የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የተገፈፈችው አዲስ አበባ ኢሬቻን ብቻ ሳይሆን የታከለ ዑማን የንግሥና በዓል የምታከብር መስላ ተሰናድታለች።  የኦሮሙማ (oromoization) ማስፋፊያ ባንዲራ የአዲስ አበባ ጌጥ ሆኗል፤  እጅግ አሰፋሪው ነገር ይህ ባንዲራ እንዲሰቀል መደረጉ ሳይሆን ይህንን ለመስቀል አስቀድሞ  የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በፌደራል ፖሊስ መግለጫ ታግዞ የማጥፋት የማዋረድ ስራ መሰራቱ ነው።
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ የድሮው  ሥርዓት የነገሥታቱ ምልክት ነው ሲሉ የከረሙት የኦሮሙማ አዝማቾች የግብፅ ምልክት የሆነውን ባንዲራ በኩራት ለመስቀል የተረኝነት ሥልጣኑን መጠቀሚያ አድርገዋል።
ደብረዘይት ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ይዛ የመስቀል ደመራን ማክበር ተከልክላለች፤ መከልከል ብቻ ሳይሆን ሊቀጳጳሱን አስራ ስታጉላላ ውላለች።
ከህወሓት በብዙ እጥፍ የሚከፉት አውዳሚ ተረኞች በእያንዳንዱ ቀን ስራቸው የክፋታቸውን እና የዘረኝነታቸውን ጥግ እያሳዩን ነው።
የኢትዮጵያ ቴሌ ኮሙኒኬሽን መስሪያቤት ለኢሬቻው ድምቀት መኪኖች መድቦ ዘመናዊ ካሜራዎች ሲሰቅል እንዲውል ሲደረግ – በመስቀል በዓል ፌደራል ፖሊስና ደህንነት መስሪያቤቱ – የታከለ ኡማ አዲስ አበባ አስተዳደርን ጨምሮ ተቀናጅተው  ከካህናት፤ ከውጭ ዜጎች ፤ ከንዋየ ቅድሳት ላይ ሳይቀር አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ሲነጥቁ ሲጥሉና ሲረግጡ እንደነበረ ይታወሳል።
አዲስ አበቤ ጥቅምት 2 ላይ አተኩር!
 
በቀደም አዴፓ መግለጫ አወጣ ሲባል አንዱ ልጅ “ምን አለ” በማለት ፋንታ “አሁንም አወጣ” አለ። ያ ልጅ አዴፓ ዛሬም መግለጫ ማውጣቱን ቢሰማ ምን እንደሚል አላውቅም። ግን አውጥቷል። በመግለጫውም “የፌደራል መንግስቱ ይድረስልኝ።” ብሏል። በርግጥ አዴፓ የተወከለው እና የሚሰራ ለአማራ ህዝብ ቢሆን ኑሮ ክልሉን ስፖንሰር አድርጎ እና በሚዲያ አቀናጅቶ በመከላከያ ድጋፍ የሽብር ስራ እኒሰራ ከፈቀደው አካል እርዳታ አይጠይቅም ነበር። አዴፓ በተግባርም ሆነ በመግለጫም የሚሰራው የወገን ስራ አይደለም። የፌደራል መንግስቱ እርዳታ ባያረግለት ምን ሊሆን ነው? ይልቅ እየሞተ ያለውን አማራ መቅበር አቁመህ መሞቱ እንዲያበቃ ህዝቡ በተጠንቀቅ እንዲቆም እና ራሱንም ከማንኛውም ጥቃት እንዲከላከል በቴሌቪዥን ጥሪ አድርግ። አዴፓ ጥሪ ያደረገለት የፌደራል መንግስት እኮ ከደመራ በዓል ተሳታፊዎች እና ዲያቆናቱ በያዙት ከበሮ ላይ ያደረጉትን የኢትዮጵያ ባንዲራ እየቀማ የቆሻሻ ትቦ ውስጥ ይጥል የነበረው የአብይ አመድ መንግስት ነው። ይሄው መንግስት ዛሬ ደግሞ እንደምታዩት የአዲስ አበባን መንገዶች ዘግቶ፣ ከቤታቸው ለስራ የወጡ ሰዎች ሳይቀር ወደቤታቸው በሚመለሱበት ወቅት የይለፍ መታወቂያ ከሌላችሁ ማለፍ አትችሉም ብሎ አግቶ የኦነግን ባንዲራ የያዙ ቄሮዎችን ለኢሬቻ እንዲህ እያስጨፈረ ነው። ከፖለቲካ በጣም ሩቅ የሆኑት የሃይማኖት አባቶች እና ያልተማረ ማንኛውም ጤነኛ ሰው በደመነፍስ የተረዳውን እና ሊረዳ የሚችለው  የአብይ አመድ አካይስታዊ መንገድ ያልተረዳ ብቸኛው ድርጅት እና ስብስብ አዴፓ ብቻ ነው። ለዚያም ነው አንድ እግሩ መቃብር ውስጥ ሆኖ እንኳ አይኑን መግለጥ ያልቻለው። ኦርቶዶክ ተዋህዶ እና አማኞቹ እንዲሁም  የሚይዙት የኢትዮጵያ ባንዲራ በአብይ አመድ ፊት ከኢሬቻ እና ከኦነግ ባንዲራ በታች ናቸው። ሁሉም ራሱን ማተለሉን አቁሞ እንደ ሰው ከዚህም በታች ውርደት ከመሸከሙ በፊት አይኑን ገልጦ ከፊቱ ያለው እውነታ ጋር መጋፈጥ ይሻለዋል።  የአዲስ አበባ ህዝብ ግን ጥቅምት 2ን በፍጹም መርሳት የለበትም። ጥቅምት ሁለት ዛሬ በይፋ በዓይንህ ያየኸውን የሁለተኛነት ከዚያም ተገፍተህ የምትጣልበትን አፓርታይዳዊ ስርዓት የምትቃወምበት ቀን ነው።
ተረኝነት (ፈረቃ) ብቻ ሳይሆን አውዳሚ ተረኝነት !!
Filed in: Amharic