>

ታሪካዊው ቅርስ ለሀገርና ለታሪክ ጠሎች ሊሰጥ አይገባም!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ታሪካዊው ቅርስ ለሀገርና ለታሪክ ጠሎች ሊሰጥ አይገባም!!!
አቻምየለህ ታምሩ
የዐፄ ፋሲል ዘውድ የኢትዮጵያን አሻራዎች ማጥፋትን ለኦሮሞ ተቆርቋሪ መሆኑን እንደማሳያ አድርጎ ለያዘው ኦነጋዊ አገዛዝ ተላልፎ ሊሰጥ አይገባም!  
ከዛሬ 353  ዓመታት በፊት  በተወለዱ በ78 ዓመታቸው መስከረም 15 ቀን 1659 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ያለፉት ታሪካዊቷን ጎንደር ከተማን  የቆረቆሯት የዐፄ  ዘውድ በሀገረ ሆላንድ ተገኝቷል። ዘውዱ በኢትዮጵያ አቆጣጠር የተሰራበትን ዘመን  ፲፮፻፳፮  [1626] ዓመተ ምሕረት በመጥቀስ ዘውዱ የማን እንደሆነ ሲገልጽ «በዐፄ ፋሲል ዘመነ መንግሥት» የሚል በኢትዮጵያ ፊደል ታጽፎበታል።
ዐፄ ፋሲል እንደሌሎች የኢትዮጵያ ነገሥታት ሁሉ የተማሩ መራሄ መንግሥት ነበሩ። በወጣትነታቸው  በጣና ሐይቅ ላይ ባሉ ታላላቅ ገዳማት ውስጥ  መንፈሳዊና የአገር አስተዳደር ትምህርታቸውን ተከታትለው አጠናቀዋል። በቆይታቸውም  ስለመንግሥት አወቃቀር፣ ስለፍርድ አሰጣጥና  ስለሕዝብ አስተዳደር  በሚገባ አጥርተው ተምረዋል።
የዐፄ ፋሲልን ኢትዮጵያ የወሰን ልክ  ለማወቅ እንዲህ ተብሎ ከተገጠመላቸው ቅኔ መገንዘብ ይቻላል፤
ጎንደር ቢያጉረመርም ፋሲል ፈረስህ፣
ኑብያና ስናር ወርቁን ጫኑልህ፡፡
ሳሩን ተጠየፈ የፋሲል ፈረሱ፣
ክምር የሱዳን ወርቅ ገፈራው ነው ለሱ፡፡
ታላቁ የግዕዝ ሊቅ አለቃ ደስታ ተክለ ወልደ ባዘጋጁት መዝገበ ቃላት ገጽ 285 ላይ ዐፄ ፋሲል የመሰረቱትን ጎንደር ከተማ ፍቺ ሲተረጉሙ  ቃሉ ግዕዝ መሆኑን ይናገሩ ና  «ጉንደ ሀገር» ማለት ዋና የአገር፣ የሀገር ራስ፣ ያገር ግንድ፣ ያገር ቀንድ፣ የበጌምድር ራስ፣ መናገሻ፣ መዲና፣ ከተማ መሆኑን  አስተድተዋል።
ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የወደቀችው ከሀያ ባንክ በላይ ከሚዘርፍ ገዳይ ቡድን ጋር አብሮ ለመስራት በሬ አርዶ ሲታረቅ በሚውል የአፓርታይድ አገዛዝ ላይ ነው። የአገዛዙ ዋና አለማ የኢትዮጵያ አሻራዎችን፣ ታሪካዊ ቦታዎችንና ቅርሳ ቅርሶችን ሁሉ አጥፍቶና ደምስሶ በኦነጋውያን ዝባዝንኬ መተካት ነው። ለዚህ ነውረኛ  አገዛዝ ማንኛውንም የኢትዮጽያን ቅርስ ጠብቆ ብሎ አሳልፎ መስጠት   እንዲያጠፋውና እንዲያወድመው ማመቻቸት ነው።
ስለዚህ  በውጭ አገር የሚገኙ የኢትዮጵያ ቅርሶች፣ አሻራዎችና ማንኛውም የቆዩ የታሪክ ምልክቶቻችን ለኢትዮጵያ፣ ለታሪኳና ለሕዝቧ የሚቆረቆር እውነተኛ  ኢትዮጵያዊ መንግሥት እስኪመጣ ድረስ በያሉበት አገር ቢቆዩ ይሻላል። የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቦታዎችንና ቅርሳቅርሶችን እያደነ ማጥፋቱን ለኦሮሞ የመቆሙ ምልክት አድርጎ ለያዘው ኦነጋዊ አገዛዝ  ለታሪክና ለትውልድ ልናወርሳቸው የሚገቡ  እንደ ዐፄ ፋሲል  ዘውድ  አይነት  ብርቅዬ ቅርሳችንን ታሪክና ሃይማኖትን ሲያጠፋ ለሚውል አገዛዝ  ድምጥማጣቸውን እንዲያጠፋው ጠብቅ ብለን ልንሰጠው ከቶ አይገባም።
Filed in: Amharic