>

ከዚህ በላይ ምን ክህደት  አለ ? (ሀብታሙ አያሌው)

ከዚህ በላይ ምን ክህደት  አለ ?
ሀብታሙ አያሌው
የኦዴፓ መራሹ ቡድን (ቄሮ ) ዘመቻ!
 
የዶክተር አብይ ኦዴፓ ምን ይዞብህ እየመጣ እንደሆነ ተመልከት፤ እስክንድር ነጋ በፅ/ቤቱ መግለጫ እንዳይሰጥ መጥቶ በኃይል ያስቆመው ኢ-መደበኛ ቡድን ዛሬ የኢሬቻ ፀጥታ አስከባሪ ነው ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴ ይጠቀማል በማለት ይፋ ተደርጓል።
አዲስ አበባ የሁላችንም ናት የኢትዮጵያ አንድነት ይጠበቅ የሚለው የባለአደራው ምክር ቤት አባላት ግን እየተሳደዱ ታስረዋል።
እረ ባላደራውን ተወው ኃይል የእግዚአብሔር ነው ብለው የሚያምኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች መስከረም 4 ሰልፍ ለማደራጀት ቢንቀሳቀሱ አደረጃጀት ቢፈጥሩ  ጠቅላይ ሚንስትሩ ብርክ ይዞት ሲጮህ ከረመ።  ሊቃነ ጳጳሳቱን ጠርቶ ዛተ፤ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳን ልኮ ለማስፈራራት ሞከረ፤ ኮሚቴውን ቤተመንግስት አስጠርቶ በግልፅ አስጠነቀቀ።
ይህ ሁሉ ሲሆን ቄሮ የሚባለው መዋቅር ሲፈልግ ገጀራና ዱላ ይዞ ይወጣል፤ ኮንደሚኒየም ቤቶችን እየሰበረ ገብቶ ይቆጣጠራል፤  የመስቀል በዓል እንዳይከበር በይፋ ይከለክላል።  በግልፅ እየዛቱ በጠራራ ፀሓይ የሰው ቢሮ ጥሰው ገብተው ለድብደባ ሲሰናዱ የነበሩ ወጣቶች ዛሬ እንዴትና በማን ሲታገዙ እንደነበር ይህው ተመልከት።
በጃዋር በኩል ተጠርተው የኮንደሚኒየሙን እጣ ለማስተጓጎል ገጀራና ዱላ ይዘው የወጡት ወጣቶች፣ የቡራዩን ጭፍጨፋ የከወኑ ገዳዮች…ጠቅላይ ሚኒስትሩ አላየሁም አልሰማሁም ሲል እንደነበር እናስታውሳልን፤ ይመዝገብ።
የኦዴፓ መራሹ ቡድን (ቄሮ ) ዘመቻ
ወደ ግሸን ማርያም ለንግስ የሚሄድ መኪና እያስቆመ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሚቀማ፤ ከመኪና ላይ  ቀለም የሚልጥ በኦሮሚያ ክልል መንግስት የሚደገፈው የወንበዴ ቡድን  በአዲስ አበባ የኢሬቻ ፀጥታ አስከባሪ በመባል ተመድቧል።
ይህ ቡድን የብሔራዊ ደህንነት ተቋምን እንዲመራ በዶክተር አብይ አህመድ ከተሾመው  አቶ ደመላሽ ወ/ሚካል ከጥተኛ ትዕዛዝ የሚቀበል አካል ነው።  የፌደራልና የክልል ፖሊሶች በይፋ ከዚህ ቡድን ጋር ተቀናጅተው በኢሬቻ በዓል ፀጥታ ለማስከበር በሚል ዘመናዊ የመገናኛ መሳሪያዎች አጠቃቀም ሰልጥነው እንዲሰማሩ ተደርጓል።
የተደራጀው ወንበዴ ቡድን በይፋ እንደምንመለከተው ኢትዮጵያዊነትን በኦሮሙማ ዘመቻ ለመለወጥ ግልፅ ተልዕኮ ወስዶ እየተንቀሳቀሰ ነው።
አዴፓ = ዛሬም አልተገለጠልህ ይሆን ?   ዛሬም ፋኖን  ማረቅ ወይስ ማሳደድ እና  መበታተን ይሻላል ? (የተሰራውን ጥፋት  አልዘነጋሁም ማረቅ ያልኩት ከዛ በመነሳት ነው)
Filed in: Amharic