>

የኦሮሞ ልሂቃን!... የባርነት ስነልቦና እና የስነልቦና ባርነት!!! (ሀይለገብርኤል አያሌው)

የኦሮሞ ልሂቃን!…
የባርነት ስነልቦና እና የስነልቦና ባርነት!!!
ሀይለገብርኤል አያሌው
     እኚህ ሰው ፤ የጃዋር፣ የሕዝቅኤል እና የመሳሰሉት የ”እውቀት” አባት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ዶክተር ገመቹ ይባላሉ ፤  በኤል ቲቪ ላይ ቀርበው እንዲህ ብለዋል ፦
    ” ክርስቲያን ማለት አማራ ማለት ነው፣ ጥምቀት የሚያጠምቁትም ከኦሮሞነት ለማንፃት ነው ፤  ኦሮሞ ክርስትና ከተቀበለ አማራ ይሆናል !!! ብለዋል ፤ሃሃ… ግብጽ ፣ ሶሪያ ፣ ግሪክ፣ ርልሽያ፣ እስራኤል ፣ … ወዘተ… አገራት ውስጥ የሚገኙ ክርስትና የተቀበሉ የየአገራቱ ዜጎች ፤ ” ዐማራ “ይሆናሉ ማለት ነው ¡¡ አይ ዱክትርና¡¡
       እኚው ሰው እንዲህ ሲሉም ተናገሩ። ፦ ” ዓይናቸዉን በጨዉ ኣጥበዉ “በጎሳ በዘር መከፋፈል ያመጣብን ኢህኣዴግ ነዉ የሚሉት አሳፋሪ ተረት ተረት እና ዉሸት ነዉ!” ይላሉ ኦቦ ገመቺስ በአንድ ” ዋቃ” ይሁንቦት እና ሃቁ’ን ይነገሩን ፤ እሩቅ ሳንሄድ አሁን ላይ በአገራችን ኢትዮጵያ የሚታየው በጎሳ በዘር መከፋፈል እና በዚህም ምክንያት እየደረሰ ያለው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የአገር ውስጥ መፈናቀልና ስደት በደርግ ጊዜ ነበር ?! አሁን ላይ የሚታየው አደገኛ ዘረኝነት የማን እጅ ስራ ሆነና ነው በዘር መከፋፈል ኢህአዴግ  ያመጣብን አይደለም የሚሉት ?! እድሜ ሲጨምር አለማዊ እውቅት በእርስዎ ዘንድ ምንም ነው ማለት ነው ¿¡
   ♦እኚህ ሰው  አፍቅሮተ መለስ ዜናዊ እንዳለባቸው ፤ ለዚህም እጅ መንሻ ሟቹ መለስ ዜናዊ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር አድርጎት በነበረው ስብሰባ ላይ ፤   ዘ-ፕሬስ ለተሰኘች ጋዜጣ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ፦“እዚህ የተሰበሰቡት ሃምሳ ፕሮፌሰሮች ጭንቅላት ቢጨፈለቅ አንድ መለስ ዜናዊን አያክልም” ብለው ነበር። ለዚህም ድልብ ስድባቸው ሟቹ ሰውዬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንትነትን ቦታ ሰጥቷቸው  ነበር ፤ የኢህአዴግ ስልጣን የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነውና ብዙም ሳይቆዩ በመሳደብ ያገኙትን ስልጣን/ቦታ እንዲለቁ ተደርገዋል ።
በርእሰ ጉዳይነት ወደ ተነሳሁበት ነጥቤ ልግባ፦
ይህ ሰው ጡቁሮች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊት በማስረጃና በተግባር እራሱ እያሳየ የሚያደርገው ገለጻ ልብ ይነካል:: በአሜሪካ የተፈነገሉ ባሮች የማንነት ምንጫቸው የቤተሰብ ቋንቋቸው ባህልና ወጋቸው አይደለም ወላጆቻቸውን እንኳ የማወቅ እድል አልነበራቸው:: ስለዚህም ልጅ ከእናቱ አባት ከልጁ ባለማወቅ እንደ ከብት እንዲዋለዱ ተደርገዋል ይለናል ይህ ሰው::
ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነው በእርሻ ስራ የሚሰማሩ ጥቁሮች የታሰሩበት ሰንሰለትና እግር ብረት አንሶ በጫካ ውስጥ ተሽሎኩልከው እንዳያመልጡ ይህ ፎቶው ላይ የሚታይ ከባድ የብረት ፍርግርግ አንገታቸው ላይ ይታሰር ነበር::
ባርነት ማንነትህን ደምስሶ ሰብዐዊነትን የሚገፍ መርገም ነው:: በጭቆና ስርአት ውስጥ ያለፈ የእኔ የሚለው ትላንት የለው:: ሊኮራበት የሚችል በሕል ሊያወራብት የሚችል ቋንቋና የኔ የሚለው ወግና ትውፊት የለውም ::ከአፍሪካ የተጋዙ ጥቁር አሜሪካውያን ከየትኛው የመሬት ጥግ ደቡብ ይሁን ምዕራብ  እንደተጋዙ የየትኛው ሃገር እርሾ እንደሆኑ እንኳን አያውቁም:: እውቋ ተዋናይና በሴት ሚሊየንሮች የአለማችን ቁጥር አንድ ሃብታም የሆነችው ኦፕራ ዊንፍሬ የዘር ስሪቷ ከየት እንደሆን በዲኤንኤ ምርመራ አረጋግጣ የዘሮቿን ምድር ማየቷን ከዚህ በፊት ሰምተናል::
ኢትዮጵያን አፍሪካውያን ሲሸጡና ሲለወጡ ክብሯን አስጠብቃ በነጻነትና በልዐላዊነት እንድትኖር ጀግኖች ልጆቿ ውደር የሌለው ዋጋ ከፍለው የክብርን ታሪክ አውርሰውናል::
ባርነት ቀረብን ጭቆና ተጠማን የሚል መንፈስ የተጫናቸው የኦሮሞ ልሂቃን በየግዜው በየሚዲያው የሚያዝረከርኩት እረብ የለሽ ጩሕት ሕዝባችንን በተለይ የኦሮሞ ተውላጆችን እጅግ እያሳቀቀ ነው:: በአጼው ዘመን ከፍየል እረኝነት በግድ እየተጎተተና ማርና ወተት እየተመገበ ተምሮ ዛሬ ለትልቅ ደረጃ የበቃው ምሁር ተረግጬ ተንቄ ቋንቋዬ ስሜ ወዘተርፈ የሚል አሰቃቂ የድንቁናና የባርነት እሰጣገባ የገባው አብዛኛው ኤሊት የተጣባው የበታችነት የስነልቦና ደዌ መፍትሄ ካልተፈልገለት በሃገርና በሕዝብ ላይ ሂትለራዊ ጭፍጨፉ እንዳይፈጽም ሊታሰብበት ይገባል::
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ብዙ መልካም ነገሮች እንዳሉ ሁሉ በጎ ያልሆነም ገጽታ መኖሩ አይካድም:: ምንም ይሁን ምን ማንም የማይክደው በሃገራችን የብሄሮች ብዝሃነት ተጠብቆ ለመኖሩ ከ80 በላይ ማህበረሰቦችና ቋንቋዎች ምስክር ናቸው:: በአማራ ጥላቻ ያበዱት የኦሮሞ ልሂቃን ዛሬ የሚናገሩበት ቋንቋና አለን የሚሉት ባህል ከመሬት ውስጥ ቆፍረው ያገኙት ሳይሆን በክብር ተጠብቆላቸው ስለቆየ ነው:: እውነት እንነጋገር ከተባለ የሚጠሉት ሚኒሊክ ለሰው ልጆች ባህል ቋንቋና ልማድ ክብር ስላለው እንጂ አጠቃላዩን ኦሮሞ አማርኛ ተናጋሪ ማድረግ የሚያቅተው አልነበረም:: እሱ ግን አማራ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ በመሆኑ በቧለሟልነትም በጋብቻም ከኦሮሞ ጎሳዎች ጋር አንድነቱን ለማጥበቅ ሞክሯል::
በነፃነት ምድር እየኖሩ የባርነት ቀንበር ያጎበጣቸው :: በብርሃን ላይ ቁጭ ብለው ጭለማ የዋጣቸው :: አካላቸው ጤናማ የሚመስል ሕሊናችው ግን የታወከ መማር ያደነቆራቸው የጥላቻና የበቀል ጥማት ያናወዛቸው::
አውራዎቹ የሕሊና ባሪያ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ገመቹ መገርሳ : እዝቄል ጋቢሳ በቀለ ገርባ ዳውድ ኢብሳ እና ሌሎችም ግልገል ጠባቦች ወይ በጸበል : አለያም በዋቄፈታ : ድግምት ካልሆነም በኬሚካል : ማጥመቅ ካልተቻለ በዚህ የጥላቻ ስሜትከሚዲያ ቅርሻት ወደ እንገት ቅላት ላለመሸጋገራቸው ማረጋገጫ የለንም::
ልክ ዛሬ እንደታየው ገመቹ መገርሳ የበታችነት ስነልቦናው ሕሊናቸውን አጫጭቶ ወደ አውሬነት ሳይለውጣቸው ኦሮሞ ወገኖቻችን በተለይ ለነዚህ የሕሊና በሽተኞች መላ ቢፈልግ መልካም ነው::
በታሪክ ሚዛን ሂሳብ እናወራርድ ከተባለ ሁሉም የሚመዘው ድርሻ አለው:: የህሊና ባርነት እንቅልፍ የነሳው ሁላ እየተነሳ የሚያቀረሽ ከሆነ ድርሳናት እየተመዘዙ ታሪክ እየተበለተ እንደ ሰማይ ክዋክብት ከበዛው የኢትዮጵያ ታሪክ ሊነሳ የሚችለውን ሙግት በእርግጠኝነት የኦሮሞ ልሂቃን ሊወጡት አይችሉም:: ትላንትን ለታሪክ ትቶ ነገን ማበጀት የተሻለ መሆኑን ምክር ካልገባቸው መከራ እንደሚያስተምራቸው ማረጋገጥ ግድ ይላል::
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
አሜን!!
Filed in: Amharic