>
5:13 pm - Sunday April 19, 2314

ፖሊሲ እና አቃቤ ሕግ፤ መቼ ይሆን የሚታደሱት? ፍርድ ቤቱም ከእጅ አይሻል ... መሆኑ ለምን ይሆን?!?  (ያሬድ ሀይለማርያም)

ፖሊሲ እና አቃቤ ሕግ፤ መቼ ይሆን የሚታደሱት? ፍርድ ቤቱም ከእጅ አይሻል … መሆኑ ለምን ይሆን?!?
 ያሬድ ሀይለማርያም
በዛሬው ዕለት ፍ/ቤት የቀረቡት እነኤልያስ ገብሩ(አምስት ሰዎች ያሉበት መዝገብ) በጠበቃ ተማም አባቡልጉ አማካይነት ላቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውሳኔ ለመስጠት አራዳ ምድብ የመጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤት ለዛሬ ሳምንት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ከኤልያስ ገብሩ ጋር በተያያዘ ዓቃቤ ሕግ የሰኔ 15ቱን ክስተት አስመልክቶ መልዕክት ተጻጽፏል የሚልና በማሕበራዊ ሚዲያ የገለጻቸው ነገሮች አሉ የሚል ሃሳብ ያነሳ ሲሆን ጠበቃ ተማም የተባሉት ነገሮች ያለመቅረባቸውንና ደንበኛቸው ያለአግባብ እየተንገላቱ እንደሆነ በአጽንኦት ገልጸዋል።
+ ፖሊስ ተጨማሪ 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ጠየቀ፤
+ ፍርድቤት እስከዛሬ ባሉት ጊዜያት ምርመራህን ለምን አላጠናቀቅክም? እስከ አሁን ምንስ መረጃ አገኘህ ብሎ ፖሊስን ጠየቀ፤
+ ፖሊስ ከብሔራዊ ደህንነት ቢሮ አገኙሁት ባለው ማስረጃ ኤሊያስ ገብሩ በሚያዚያ 15ቱ የባህዳር እና የአዲስ አበባ የባለስልጣናት ግድያ ላየ የዶ/ር አብይ እጅ አለበት ብሎ በስልኩ እና በማህበራዊ ድህረገጾች የጻፈው እና ሃሳቡን የገለጸበት ማስረጃ አግኝተናል፤ ይሄ ደግሞ የሃሰት ወሬ ማራባት ነው አለ፤
+ የተከሳሽ ጠበቆች ታዲያ ይህ ጉዳይ ከኤሊያስ ገብሩ ክስ ጋር ምን አገናኘው፤ ፖሊስ ኤሊያስን የከሰሰው በግድያው ላይ እጁ አለበት በሚል እና በሽብር ወንጀል ነው ብለው ሞገቱ፤
+ ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን አድምጦ ለውሳኔ ለቀጣዩ ሃሙስ ቀጠረ።
የጉድ አገር ማለት ታዲያ ይሄኔ አይደለም ወይ?
ዶ/ር አብይን መተቸት፣ በሃሰት ስማቸውን ማጥፋት እና እሳቸውን መንቀፍ በምን ሂሳብ ነው በሽብር የሚያስጠረጥረው? በምንስ ሂሳብ ነው ከግድያው ጋር የሚያያዘው?
ፍርድ ቤቱስ ይሄን ሁሉ ጊዜ ያለ በቂ ምክንያት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እየሰጤ በአሰት ውንጀላ ዜጎችን የሚያጉላላው ለምንድን ነው? ስለ እነዚህ ተቋማት በዜና የሚቀርበው የታህድሶ ጋጋታ እና ማሻሻያ መሬት ላይ ለምን አይታይም? ነው ወይስ ከገጽታ ግንባታ መዝለል አልቻለም?
ፍትሕ ለኤሊያስ ገብሩ እና በተመሳሳይ ሁኔታ በግፍ ታስረው ለሚማቅቁ ዜጎች ሁሉ!
Filed in: Amharic