>

ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ በለውጥ ጎዳና (ክፍል 2) ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ

ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ በለውጥ ጎዳና (ክፍል 2)

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ
ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ

ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ በለውጥ ጎዳና በሚለው መስከረም 09/2012 ‘’Ethioreference’’ ላይ ባወጣሁት ፅሁፍ በዩኒቨርስቲ የተለያየ እርከን ላይ የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ቅር እንደተሰኙ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ የፅሁፉ ዋና ዓላማ ለአገራችን የመምህራን ዘርፍ ዕድገት ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኘው ተቋማችን መዋቅሩ እና አሰራሮቹ ተስተካክለው አሁን ያለበት የለውጥ ጎዳና እና ወደፊት እንዲራመድ ከቅን ልቦና በመነጨ ሁኔታ ከማሰብ እንጅ ባልተመቻቸ ሁኔታ ተቋሙን ለማሳደግ ቀን ተሌት የሚለፉ የስራ ባልደርቦቸን ለማሳዘን አልነበረም፡፡

ስለዚህ ለተፈጠረባቸው ቅሬታ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ እኔ በተረዳሁበት መንገድ አልተረዱትም፣ የተለየ አረዳድ በመያዛቸው አልገረመኝም ምክንያቱም በአንድ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ግንዛቤዎች መኖሩ የሚጠበቅ ስለሆነ ዳሩ ግን የፅሁፉ ዋና ዓላማ የማከብራቸውን የስራ ባልደርቦቸን ማሳዘን ሳይሆን የተሻለ ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት ገንቢ ሀሳቦችን ለመሰንዘር እንጅ ከበስተጀርባው ያነገበው ምንም ነገር እንደሌለ በድጋሜ እየገለፅሁ ባላሰብሁት መንገድ ለተፈጠረው ቅሬታ በድጋሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡

 

 

Bekalu Atnafu Taye (PhD)

Associate Professor of English Education
(B.Ed., MA in SNE, MA in TEFL, PhD in TEFL)

Director for Centers of Excellence in Research
Kotebe Metropolitan University

Filed in: Amharic