>

የቅማንት የማንነት ጥያቄ ወይንስ የሕወሓት ግልጽ ወረራ? (ብሥራት ደረሰ - ከአዲስ አበባ)

የቅማንት የማንነት ጥያቄ ወይንስ የሕወሓት ግልጽ ወረራ?

ብሥራት ደረሰ  (አዲስ አበባ)

አኞ አኞ የሚል ቀልድ ዘወትር መስማት ይሰለቻል፡፡ ወያኔ ላለፉት 40 ዓመታት ብዙ እጅ እጅ የሚሉ ቀልዶችን አለውድ በግዳችን ሲቀልድብን ቆይቷል፡፡ በመሆኑም የወያኔ ቀልድ ሁሉ እንጨት እንጨትና ጋዝ ጋዝ ብሎኛል፡፡ ቀልድ የሚጥመው ወዝ ሲኖረውና ሳይደጋገም በመጠን ሲሆን ነው፡፡

ወያኔ አሁን ጨዋታው ሁሉ አልቆበት መቀሌ በከተተበት ወቅትም ያንኑ ያረጀ ያፈጀ ቀልዱን በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ ቀጥሏል፡፡ ወያኔዎች ሰሚ እስካገኙ ድረስም ይሄው የጠነዛ ቀልዳቸው የሚቆም አይመስልም፡፡ ትግራይ ውስጥ ሆኖ የአማራን ክልል እየበጠበጠ “የቅማንት ማንነት” ይባልልኛል፡፡ ይህን ቀልድ ወያኔ መቀለዱ አይፈረድበትም፡፡ ውኃ እያሰመጠው የሚገኝ ሰው የሚድን እየመሰለው የውኃ አረፋና ሣርን እንደሚጨብጥ ሁሉ ወያኔዎችም የማያደርጉት ነገር እንደሌለና እንደማይኖርም ለማንም ግልጽ ነው፡፡ እባብ ተፈጥሮውን አይለውጥም፡፡

ችግሩ ለወያኔዎች ቀልድ ምቹ የሆነ የፌዴራልና የአማራ ክልል ተብዬዎቹ መዋቅሮችም አብረውና ተባብረው ቀልዱን የሚያጅቡና እውነት ለማስመሰል የሚጥሩ መሆናቸው ነው፡፡ ብአዴን ውስጥ የተሰገሰጉ ወያኔዎችና አማራን ለማጥቃት በፌዴራሉ ውስጥ የቤት ሥራ የተሰጣቸው ከፍተኛና ዝቅተኛ ሹማምንት ለወያኔው አድረው ይህን እግር እግር የሚል “የቅማንት የማንነት ጥያቄ” ቀልድ ሲያራግቡ ስናይ እጅግ ያማል፡፡

ቅማንት ማለት እንደሚገባኝ የአማራው ወገን ነው፡፡ ከአማራው ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ከጥንት ጀምሮ በአንድ አካባቢ የሚኖር በቋንቋም ሆነ በአኗኗር ዘይቤም ከአማራው ብዙም ልዩነት የሌለው ነገድ ነው፡፡ አማራ አካባቢ የሚኖር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ደግሞ በማንነቱ የሚደርስበት አንድም በደል እንደሌለ የአማራን ሥነ ልቦናና ሃይማኖት የሚረዳ ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ነገሩ አህያዋ “ሳታመካኝ ብላኝ” እንዳለችው ነው፡፡ ሌላ ሰበብ ቢፈለግ ይሻል ነበር፡፡ ይህ ሕዝብ ከአማራው በተለዬ ሊያውም በአማራው ወገኑ የሚደርስበት አንዳችም ችግር እንደማይኖር በአሥር ጣቴ እፈርማለሁ፡፡ ጥቂት ሰዎችን ከዚህ ነገድ በማደራጀት በስሙ ሊነግዱ የሚፈልጉ የሰይጣን ቁራጮች ግን አሉ – በዚህም በዚያም ወገን፡፡ ከመነሻው ቅማንት የሚባል ሕዝብ አብሮ ኗሪውን ሰፊውን የአማራ ወገኑን ሊዋጋ የሚያስችለው የሞራልም ሆነ ማናቸውም ዓይነት አመክንዮና ተነሳሽነት እንደማይኖረው የሁላችንም ግንዛቤ ነው፡፡ የማንነት ችግር ችግር ባልሆነበት ሁኔታ፣ ችግሩ በሁሉም ወገን ላይ የወደቀ ወያኔ ወለድ አገራዊ የዘረኝነት በሽታ መሆኑ የሁሉም የጋራ ዕውቀት ሆኖ ሳለ በዚህ ደረጃ ወርዶ “የቅማንት የማንነት ጥያቄ” እያሉ በወገኖቻችን ላይ ማፌዝ እጅግ የሚመርና ሥርየት የሌለው ኃጢኣት ነው፡፡ ቀልደኞች እባካችሁን በቅጡ ቀልዱ፡፡ ወያኔዎችም እባካችሁን ወገኖቻችንን በከንቱ አታስጨርሱ፡፡ የትግራይንም ሕዝብ በቀጣይ ትውልዶች ጥርስ ውስጥ አታስገቡት፡፡ እስኪ ይብቃችሁ፡፡ እስኪ አሁን እንኳን አማራውና ትግሬው ትንሽ ዕረፍት ያግኙ፡፡ እስኪ እናንተም ዐረፍ በሉና ወደ ኅሊናችሁ ተመልሳችሁ ከሞት ወዲያ ማዶ ስላለው ሕይወትም አስቡ፡፡ ምን ዓይነት የመርገምት ፍሬዎች ናችሁ? በገሃነምም እኮ አንዳንዴ ምናልባትም እሁድ እሁድ ከእሳት ግርፋትና ከዕቶን ወላፈን ይታረፋል አሉ የሚያውቁ ሲናገሩ፡፡ በምታምኑት በዲያብሎስ ይሁንባቸሁ ትንሽ ዕረፍት ስጡን፡፡ እናንተም ዕረፉ፤ እኛም ዕንረፍ፡፡ ከሀዘን አምላኪነት ወጣ ብላችሁ አዲስ ሕይወት ለማጣጣም ሞክሩ፡፡ በስመ አብ!….

ወያኔን ከጥፋት መንገዱ መመለስ ባለመቻሉ ሀገራችን መቅኖ እንዳጣች መኖሯ ነውና ሰው ዝም ቢል እግዚአብሔር ሆይ እባክህን ፍርድህን በአስቸኳይ ስጠን!!
መጽሐፈ ምሣሌ 6፡16-19 16 እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤
17 ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
18 ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
19 በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

Filed in: Amharic