>

ኢሬቻ በዶ/አብይና በአቶ ለማ አንደበት! (ዮሀንስ መኮንን)

ኢሬቻ በዶ/አብይና በአቶ ለማ አንደበት!
ዮሀንስ መኮንን
* Irreechi kenya irree keenyaa 
(ኢሬቻችን ክንዳችን ነው)
ኦቦ ለማ መገርሳ እና ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኢሬቻ በዓል አከባበርን አስመልክቶ በ OBN ላይ በአፋን ኦሮሞ የተናገሩትን ነገርና ያሳዩትን ወገንተኝነት ለማየት በአንጻሩም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባከበረችው  የመስቀል በአል አከባበር ላይ ከታየው የፖሊስ “ሕግ አስከባሪነት” ለሁሉም እኩል መሥራቱን ማነጻጸሪያም ይሆነናል::  ወዲህም ከመንግሥት ግልጽ አቋም ተቃርነው ከመሥመር የወጣ ወገንተኝነት ለሚያሳዩ ባለስልጣናት መሞገቻ ሠነድም ነው::
አቶ ለማ መገርሳ 
– ኢሬቻን የምናከብረው ስለተገደድን ሳይሆን ስለምንዋብበት ነው::
– ሌሎችም እንዲወዱልን እንዲያደንቁልን ነው ይምንፈልገው::
– ከዚህ ቀደም ኢሬቻ ላይ ሁላችንም ያፈርንበት እና ያዘንንበት ነገር ተከስቶ ነበር:: ያንን ችግር አንረሳውም::
– ይሁን እንጂ ከችግራችን የምንማር እንጂ ከችግራችን ጋር አብረን የምንኖር መሆን የለብንም:: ከችግሩ ጋር ሲያለቅስ የሚኖር ችግረኛ ነው::
– ከዚህ ቀደም ኢሬቻ ላይ ይገጥመን የነበረው ችግር ሊቀር ይገባዋል:: ይቅር::
– ኢሬቻ ላይ በገጠመን ችግር እኛ ነን የተጎዳነው:: የሚሳቅበት እና የሚታፈርበት ባህል ሆኖ በሌሎች እንዲታይ ነው ያደረገን::
– ኢሬቻ የመንግሥት በዓል አይደለም:: የዚህ ህዝብ በዓል ነው:: …መንግሥት ማገዝ ያለበትን ከመርዳት ያለፈ በዓሉ ላይ ድርሻ ወስዶ ወይንም ባለቤት ሆኖ ማጋፈር የለበትም::
– መንግሥት የበዓሉ ባለቤት ከሆነ ባህሉን ማበላሸት ነው:: …ባህል ከምንም ጋር መቀላቀል የለበትም::
– ታዲያ ኢሬቻን እንዴት አድርገን ነው የምናከብረው? ልክ ክስቲያኖች ጥምቀትን እንደሚያከብሩት, ልክ ሙስሊሞች ኢዳቸውን መስጊድ እና ስታዲየም ሄደው እንደሚያከብሩት ነው ህዝቡ በባለቤትነት ማክበር ያለበት::
– የጥምቀት በዓሉ ባለቤት ቀሳውስቱ፣ የኢዱም ሺኪው ወይንም ኢማሙ ነው:: እንደዚሁ ሁሉ የኢሬቻ ባለቤትም መንግሥት ሳይሆን የመልካው ባለቤቶች ነው::
– አባ ገዳ ስለሆነ የመንግሥት ባለስልጣን ስለሆነ ማንም ይህንን (የተለየ ነገር)  ሊያደርግ አይችልም::
– ቢሾፍቱ ላይም (ሆራ አርሰዴ) ሆነ በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚከናወነውን የኢሬቻ አከባበር ማከናወን ያለባቸው የቦታው ባለቤቶች ናቸው:: (መንግሥት አይደለም)
– ይህ በዓል ባህል የሚንጸባረቅበት እንጂ ከዚያ ውጪ ምንም ዓይነት ነገር መታየት የለበትም::
– በዓሉ ቢያምር እኔ ነኝ የማምርበት:: እያንዳንዳችን ነን የምንዋብበት:: ቢበላሽስ? እኔ ነኝ የምጠቁረው:: እያንዳንዳችን ነን የምንጠቁረው::
– እውነት ተነጋግረን የምንደማመጥ: ቃል ተገባብተን የምንተጋገዝ ከሆነ ዘንድሮ “ኢሬቻችን ወኔያችን ነው” ኢሬቻችን ምልክታችን ነው:: ብለን አንድነታችንን እና ውበታችንን በሚያሳይ መልኩ ልናከብር ይገባናል::
ዶ/ር ዐብይ አህመድ
– በባህል እና በታሪክ መድረክ ባህልና ታሪክን ማሳየት ልማት ቦታ ልማትን ማሳየት የሃሳብ ክርክር በሚደረግበት ቦታ ደግሞ በሃሳብ መሙዋገት (ይገባል)
– የኢሬቻ ምንጭ ሠላም ነው:: አንድነት ነው:: ፈጣሪን ማመስገን ነው::
– የበዓሉ በሠላም መጠናቀቅ ሌሎች ከዚህ ባህል ለመማር ለመካፈል እንዲመጡ ያደርጋቸዋል::
– ከሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከሀገር ውጪ ያሉ ሰዎችም በርካቶች በአንድ ጊዜ ተሰብስበው የማያከብሩትን ይህን መሰል በዓል ማየት ይፈልጋሉ::
– ባህላችንን ታሪካችንን ማንነታችንን ኦሮሞነታችንን ለዓለም  እንድናሳይ በሠላም ጀምረን በሠላም እንዲፈጸም መደማመጥ አለብን::
– ወጣትነት ማወክ (መረበሽ) ብቻ ሳይሆን ልማትም ጭምር ስለሆነ በዘዴ እና በጥንቃቄ ልንጠቀምበት ይገባል::
Filed in: Amharic