>
5:13 pm - Tuesday April 20, 7193

"ቄሮ ኢትዮጵያ ነፃ ትውጣ ብሎ የታገለበትን ጊዜ እስኪ ንገሩኝ?  (ታድዮስ ታንቱ የታሪክ ጸሀፊ)

“ቄሮ ኢትዮጵያ ነፃ ትውጣ ብሎ የታገለበትን ጊዜ እስኪ ንገሩኝ? 
ታድዮስ ታንቱ የታሪክ ጸሀፊ
 
* አይደለም ነፃ ሊያወጣን፣ ኢትዮጵያን በስሟ ለመጥራትም የሚፀየፍ ቡድን ነው ቄሮ የሚባለው ስብስብ!!!”
ቄሮ የታገለው ለኦሮሞ መሬት ብቻ ነው። የለውጡ ባለቤት ቄሮ ነው የሚሉ አካላትም ተረኝነትን ለመጀመር እንዲያመቻቸው ነው። ለኢትዮጵያ የታገለው ልሙጡን ባንዲራ ይዘው ባህርዳር ላይ 50 ሰው በአንድ ጀንበር የሞቱት ናቸው። ጎንደር፣ ወሎ፣ ጉራጌ፣ እኔ ራሴ ሽዋሮቢት የታሰርኩት አቶ ታዲዮስ ነን ለኢትዮጵያ የታገልነው። የኢትዮጵያን ስም ለመጥራት በማያፍሩት ታጋዮች ነው ለውጥ የመጣው።
እሬቻ ከ150 አመት በፊት አዲስ አበባ ይከበር ነበር የሚባለው ከታሪክ ውጭ ነው። የኦሮሞን ታሪክ ከውልደትና ከግርዛት እስከ የቀብር ስነ ስርዓት ያጠኑና የፃፉ ጠበብት ይህንን አልፃፉም። ደብረዘይት ላይ በአንዲት ኩሬ እንደሚካሄድ ነው የጠቆሙን።
ዘንድሮ ይህንን በዓል በማጠናከር አዲስ አበባ የሚከበረውም፣ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ለማለት ዳር ዳር እየተባለ ነው። ለዚህም ነው ባህላዊውን የእሬቻ በዓል ሀይማኖታዊና ፖለቲካዊ ቅርፅ አስይዘው እያከበሩት ያለው።
ቄሮ ኢትዮጵያ ነፃ ትውጣ ብሎ የታገለበትን ጊዜ እስኪ ንገሩኝ? አይደለም ነፃ ሊያወጣን፣ ኢትዮጵያን በስሟ ለመጥራትም የሚፀየፍ ቡድን ነው ቄሮ የሚባለው ስብስብ።
(አቶ ታዲዮስ ታንቱ – ከኢትዮ ታየምስ ጋር ካደረጉት ቆይታ የተወሰደ)
Filed in: Amharic