>

"የፈርጣጩም፣ የወፍ ዘራሹም፣ የተስፈኛውም  ኢላማው አማራ ነው! ለምን ይመስላችሗል?!?" -  (አቶ ዮሐንስ ቧያለው)

“የፈርጣጩም፣ የወፍ ዘራሹም፣ የተስፈኛውም  ኢላማው አማራ ነው! ለምን ይመስላችሗል?!?” 
 አቶ ዮሐንስ ቧያለው
“ፖለቲካ የትም ይቦካል፤ እየሩሳሌም ይጋገራል!” ይላሉ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች። በእርግጥ እየሩሳሌም ከፖለቲካውም በላይ የክርስትና፣ የእስልምና እና የአይሁድ እምነቶች ቅድስት ከተማቸው ናት።
በዚህ በእኛ ቀጠና እና ሀገርም አማራ ክልል የፖለቲካ መጋገሪያ ከሆነ ቆይቷል። ባለፉት አመታት የጥላቻ አባቶች በመርዝ የለወሱትን ትርክት የሚያቀረሹት በዚሁ ክልል ነበር። እነዚህ የጥላቻ ወላጆች ዛሬ በአደባባይ አያቀረሹም። ሚንሊክ ቤተ መንግስት እግራቸውን አንፈራጠው ያን ግደለው፤ ይህኛውን ቁረጠው ማለት የህልም ያህል እርቋቸዋል።
ያም ሆኖ በእየ ሆቴሉ መሽገው እና በየጉድጓዳቸው ተደብቀው ከአማራ ራስ ሊወርዱ አልቻሉም። በመሰረቱ የአማራ ጥላቻ ከውስጣቸው ከወጣ፣ የድርጅታቸው ህልውና ያከትምለታል። ለዚህም ነው ተደብቀው እና ፈርጥጠውም ቢሆን አማራን ለመከፋፈል የሚያሴሩት።
አንድ ነገር ግን መታወቅ አለበት። ትናንት በአማራ ክልል የሚጋገረው ፖለቲካ በአማራ ላይ የህልውና አደጋ የሚፈጥርና ቀን ሰጥቷቸው አማራን ለማጥፋት ቤተ መንግስት በመሸጉ ገዳዮች የሚዘወር ነው። ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ በጥቁር አማራዎች በኩል የሚፈፀም የጥፋት ተልዕኮም እንደ ነበር ይታወቃል።
ዛሬ ያ ሁኔታ የለም። የትም የተቦካው ፖለቲካ በአማራ የሚጋገረው፣ አማራ ቀና ባለበት ወቅት መሆኑ ነው። አማራ ላይ የሚጋገረው ፖለቲካ ለሀገሪቱም፣ ለቀጠናውም ትልቅ ፋይዳ አለው። ለዚህም ነው ፈርጣጩም፣ ወፍ ዘራሹም፣ ተስፈኛውም የያዘውን አንጠልጥሎ ወደ አማራ የሚመጣውና የሚወረውረው።
ይህንን የፀሐይ ፖለቲካ የማይረዳ፣ የአደባባይ ሚስጥር የማይገነዘብ ካለ ለጤናው እሰጋለሁ። ሁሉም አጀንዳ አማራ ላይ መሆኑ አማራ የሀገሪቱና የቀጠናው ወሳኝ መሆኑን እንጂ ሌላ አያሳይም።
ትናንት በህዝብ ትግል ከጥላቻ ማዘዣ ኮማንዳቸው የፈርጥጡት ግለሰቦች ከጀመሩት የሽብር ተግባር ለስድስት ወራት እጃቸውን ለመሰብሰብ የሞከሩት፣ በህዝብ ደም የተበላሸውን ኢህአዴግ በነበረበት አቋም ለምርጫ በማቅረብ እንዲሸነፍ እና እነሱም መሰሎቻቸውን አሰባስበው ወደ ስልጣን ለመመለስ ስለ አቀዱ ነው።
ዛሬ ያ ቅዠታቸው ውሃ በልቶታል። ኢህአዴግ “ስሜንም፣ ግብሬንም” ቀይሬ ለምርጫ እወዳደራለሁ ሲል ፈርጣጮቹ የቀራቸውን ብቸኛ አማራጭ አጠናክረው እየቀጠሉ ነው። የቀራቸው ብቸኛ አማራጭም “ሽብር” ብቻ ነው።
ፖለቲካ የትም ይቦካል፣ አማራ ምድር ይጋገራል ያልኳችሁም ለዚህ ነው። የፈርጣጩም፣ የተስፈኛውም ዋና ኢላማ አማራ ነው። አማራ ላይ ያልተጋገረ ፖለቲካ ህልውናም፣ ተሰሚነትም የለውም። ስለዚህ ይህንን ፖለቲካ እኛ እንዘውረው? ወይስ እንደ ትናንቱ የዘመን ጠላቶቻችን? የሚለው ሊሰመርበት የሚገባ ጥያቄ ነው።
እንደ እኔ ከሆነ በፍፁም ይህንን በእጃችን ያለ የፖለቲካ እሽክርክሪት(Political pivot) ለዘመን ጠላቶቻችን አሳልፈን አንሰጥም ነው መልሴ። ከዚህ ውጭ የሆነ አማራጭ ለአማራ የትናንቱን የህልውና ትግል መምረጥ ነው። የትናንቱን የሳይኮሎጅ ጦርነት መፈለግ ነው። በፍፁም ወደዚህ የዘመን ጠላቶች ወደ ሚመኙልን የጥፋት መንገድ አንመለስም!
የአማራ ተቆርቋሪ ነኝ የሚል “በግልም፣ በድርጅትም” ያለ ሁሉም ከዚህ መንገድ ውጭ የሚኖር ጠቃሚ ጉዳይ የለምና ኑ አብረን እንታገል። ወይ ደግሞ ሳትመጡ በራሳችሁ ሜዳ ይህንን መንገድ እንድትከተሉ ወንድማችሁ እመክራችሗለሁ።
(አቶ ዮሐንስ ቧያለው – በክልሉ የፀጥታ ጉዳይ የውይይት መድረክ ላይ የተናገረውና ቃል በቃል የተቀመጠ)
ፈለገ ግዮን
Filed in: Amharic