>

የፍትህ ጩኸት!  (ቅዱስ ማህሉ)

የፍትህ ጩኸት! 
ቅዱስ ማህሉ
 
1. የዶክተር አምባቸው መኮንን ቤተሰቦች፡-
2. የአቶ እዘዝ ዋሴ ቤተሰቦች፡-
3. የአቶ ምግባሩ ከበደ ቤተሰቦች፡-
በጋራ በሰጡት መግለጫ መንግስት በቤተሰቦቻቸው ላይ የተካሄደውን የግድያ ዘመቻ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቀዋል።
 
 የባለስልጣናቱ ግድያ ምርመራ እየተካሄደ ያለው ግድያውን ባስተባበሩ እና በመሩ ሰዎች ስለሆነ ስለ ፍትህ ሲባል በገለልተኛ አካል ይጣራልን ብለዋል። አዎ! ይህ ጉዳይ በገለልተኛ አካል መጣራት አለበት። በወቅቱ የተቀረጹ የደህንነት ካሜራዎች ቅጅዎች በቴሌቪዥን ከገለልተኛ ባለሙያ ማብራሪያ ጋር ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት። እኔ ምለው የፌደራል እና የአዴፓ መሪዎች ገዳዩ ጄነራል አሳምነው ጽጌ መሆኑን እንድናምን የወተወቱንን ያህል እነዚህን ቪዲዮዎች ለምን አሳይተውን እኛም እነሱን ከመጠርጠር አናርፍም።
በነገራችን ላይ በመጽሃፍ ውስጥ ስሜ ጠፋ ብሎ (ለዚያውም መጽሃፍ እሚባል እኔ አላሳታምኩም የሚልን ሰው) በእስር ቤት አስገብቶ በግድ እመን እያለ ማሰቃየት ከጀመረ በገለልተኛ ቡድን አብይ አመድ በግድያው ውስጥ እጁ እንዳለበት ቢረጋገጥ ምን ሊያደርግ እንደሚችል አስባችሁታል። እውነተኛ መንግስት እና ፍትህ ቢኖር የኢንጅነር ስመኘው በቀለም ገዳዮች ለፍትህ ቀርበው እናይ ነበር። ግድያዎቹ ሁሉ ላይ አንድ ሰው አለ። በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር ሰዎች ገለልተኛ ቡድን ቢቋቋም እኮ መረጃዎች ታፍነው አይቀሩም ነበር።  ቤተሰቦቻቸውም ፍትህን ፍለጋ እርማቸውን ሳያወጡ በሰቀቀን ለመኖር አይገደዱም ነበር። ብዙዎችም ሃቁን ለመደበቅ በየቦታው ባልተሳደዱ እና ያለ ጥፋታቸው በእስር ባልማቀቁ ነበር። የሁሉም ሟች ቤተሰቦች ፍትህ ይፈልጋሉ። ያ ፍትህ ግን ከእቡይ አህመድ ይገኛል ማለት ሰዎቹን ሙተውም እንኳ እረፍት እንዳያገኙ የማድረግ ያህል ከባድ ነው። ከኔ ጽሁፍ ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ከአብይ ፍትህ የሚፈልግ በፎቶው እንደሚታየው ዓይነት “የመደመር ፍትህ” ይሰጠዋል። የሟች ቤተሰቦች የሰኔ 15ቱን የግድያ ዘመቻ የሚያጣራ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ያቀረቡትን ጥሪ እደግፋለሁ።
Filed in: Amharic