>
5:13 pm - Thursday April 19, 2210

ተረኞቹ የኦህዴድ/ኦነግ ጥምር መንግስት ምስራቅ አማራን የጠቀለሉበትን ካርታ እያለማመዱን ነው!!! (ውብሸት ሙላት)

ተረኞቹ የኦህዴድ/ኦነግ ጥምር መንግስት ምስራቅ አማራን የጠቀለሉበትን ካርታ እያለማመዱን ነው!!!
ውብሸት ሙላት
* “ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ!!!
(አለ እያዩ ፈንገስ)
* ትህነግ በጉርምስና ዘመኗ ሰሜን ምዕራብ አማራን የመጠቅለል አጀንዳዋን ልታለማምደን በተለያዩ አጋጣሚዎች ትግራይን ከቤኒሻንጉል የሚያገናኝ ካርታ ታሳየን ነበር። 
* ዛሬም ተረኞቹ ገና ከአፍላነታቸው ምስራቅ አማራን የመጠቅለል ቅዠታቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች እያሳዩን ነው። ትህነግ ከሰሜን ምዕራብ በፈነዳው እሳተጎመራ ተጠራርጋ መቀሌ እንደገባችው፣ ምስራቅ አማራን መነሻው ያደረገ ሱናሚ  እንዳይጠራርጋችሁ።
ምስሉ ላይ የሚታየው ሜዳሊያ እሁድ፣ (መስከረም 11) ቀን እሬቻን ለማክበር አዲስ አበባ ላይ ይደረጋል ለተባለው ሩጫ ተሳታፊዎች ለመስጠት ተብሎ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና በኦዲፒ የተዘጋጀና እውነትም ከሆነ ‘አስቸጋሪ ነው’ ነገሩ። ይህ ሜዳሊያ እውነት ከሆነ፤ በሜዳሊያው ላይ የሚታየው ካርታ ሸዋን የለ ወሎን ሁሉንም “ኬኛ” ብሏል። ከእዚህ ካርታ የበለጠ ምን ተንኳሽ ይምጣ? ከዚህ ካርታ የባሰ ምን በሕዝብ መካከል ጥርጣሬ የሚፈጥር ነገር ሊኖር ነው?
ያለ ክልሉ መንግሥት ዕውቅናና ውሳኔ ሊሠራ አይችልም። የኦዲፒ ሊቀመንበር (ጠቅላይ ሚኒስትሩ) ቀድመው አላወቁም ቢባል እንኳን ይህን እንዳዩና እንዳወቁ ማስቆም አለባቸው፤ እንዲህ ዓይነት እኩይ ተግባር ውስጥ የተሰማራ የመንግሥት ሹመኛ ላይ ፖለቲካዊ እርምጃ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። ይህን ካላደረጉ፣ ቢያንስ በዝምታ ድርጊቱን እሳቸውም እንደደገፉት ያስቆጥራል።
እንዲህ ዓይነት ሜዳሊያ የሚሰጥበት ሩጫ አዲስ አበባ ላይ ማዘጋጀት እንዴት ነው የደኅንነት ስጋት የማይፈጥረው? ግጭት ቢነሳስ? ምክንያቱም በዓደባባይ ‘ሸዋና ወሎ’ የኦሮሞ ነው የሚል ካርታ ያለበት ሜዳሊያ በመንግሥት እውቅናና ውሳኔ ለሯጮች ሊታደል ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ካልነሆም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአስቸኳይ ይህ ሜዳሊያ እንዳይሰጥ ማድረግ የሚገባቸው ይመስለልኛ።  ካልሆነ፣ የፌደራል ፖሊስም የደኅንነት መሥሪያ ቤትም ካልሆነም የመከላከያ ሰራዊቱም ቢሆን ሊያስቆመው ይገባል። ሩጫው  ከመደረጉ አስቀድሞም ለሕዝብ ሜዳሊያው ጥቅም ላይ እንደማይውል ይፋ  ማድረግ አስፈላጊ ነው።
Filed in: Amharic